(ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም .አዲስ አበባ LFSDP); የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በከንባታ ዞን በወተት ልማት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚነታቸው እያደገ መምጣቱን  ገለጸ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ በእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ  በከንባታ በቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ በዘና ቤናራ ላሎ ወተትና የወተት ተዋጽኦ ማሰባሰብና፣ ማቀናባበር ግብይት ህብረት ስራ ማህበር የታቀፉ ተጠቃሚዎች በየጊዜው በወተት ልማት የሚያገኙት ገቢ እያደገ መምጣቱን የክልሉ ግብርና ቢሮ ጠቅሷል።

በስሩ108 አባላት ያሉት ከዚህ ውስጥ 68ቱ ሴቶች ናቸው። ይህ የህብረት ሥራ ማህበር  ወተትን ፓስቸራይዝድ  አድርጎ እና እሴት በመጨመር ”የአምባርቾ የተፈጥሮ እርጎ” በሚል ስያሜ  ከ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሥራ መግባታቸው መረጃዎች ያስረዳሉ ።

በዚህ እንቅስቃሴውም  የህብረት ስራ ማህበሩ   አባላቱ የተሻለ ገቢ  እንዲያገኙ ከማድረጉም በላይ እንደ አገር ይፋ የተደረገውን  የሌማት ትሩፋት ግብን በማሳካት ረገድ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ይገኛል።

ማህበሩ  ለአካባቢው ህብረተሰብ ብሎም ለክልሉ ማህበረሰብ የአምበሪቾ የተፈጥሮ እርጎን ለማስተዋወቅ ያስችል ነው።

በሆሳዕና ከተማ ”የህብረት ስራ ማህበራት ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው ኤግዚቢሽ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመጀመርያ ምርቱን በማቅረብ የማስተዋወቅ ስራ በመስራት ምርቱን ለገበያ በማቅረብ ላይ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅትም ማህበሩ በቀን 210 የታሸገ ኩባያ ወተት ለተጠቃሚዎች እያቀረበ  ያሚገኝ ሲሆን  በቀን ከ500 እሰከ 750 ሊትር ወተት ከአባላቱ ይሰበስባል።

እንደ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት (LFSDP) መረጃ በአጠቃላይ ይሕ የህብረት ሥራ ማህበር ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ብር ማፍራት ችሏል።

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!