ጥር 13 ቀን 2012 ዓ.ም
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት ፕሮጄክት የአቅም ግንባታ ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡ /LFSDP/W.B/
*********************************************************************
በኦሮሚያ ክልል 2070 የጋራ ፍላጎት ያላቸው /CIG/ ወጣቶች እና ሴቶች በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ተደራጅቶ ወደ ሥራ መግባታቸው በክልሉ እንስሳት እና የዓሣ ሀብት ልማት ኤጀንሲ የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት የፕሮጄክቱ አስተባባሪ አስታወቀ፡፡
ሰሞኑን ከክልሉ ከ18 ዞኖች እና ፕሮጄክቱ በሚተገበርባቸው ከ 23 ወረዳዎች ለተውጣጡት ከ208 የተለያዩ ባለሙያዎች ከጥር 03 እስከ 08/2012 ዓ.ም ድረስ በቢሾፍቱ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡
ስልጠናው በቀጣይ ፕሮጄክቱ በሚተገበርባቸው በክልሉ በ23 ወረዳዎች፤ በ578 ቀበሌዎች ውስጥ የተደራጁ 2070 የጋራ ፍላጎት ያላቸው (CIG) ወጣቶች እና ሴቶች በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለቶች፤ በወተት ልማት፣ በዶሮ እርባታ፣ በቀይ ሥጋና በዓሣ ግብርና አርሶ አደሮቹን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል በከፍተኛ ደረጃ ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የእንስሳት ሀብት ልማት ኤጀንሲ የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ የፕሮጄክት አስተባበሪ የሆኑት ዶ/ር ደረጀ ጉዳታ በበኩላቸው የስልጠናው ዓላማን አስመልክተው በሰጡት አስተየያት በአሁን ጊዜ ፕሮጄክቱ በሚተገበርባቸው በክልሉ በ18 ዞኖች እና በ23 ወረዳዎች ውስጥ በጋራ ፍላጎት የተዳራጁ 578 አርሶ አዳሮች፣ ወጣቶች እና ሴቶች ተደራጅተው ወደ ሥራ ለመግባት ቅድመ ዝግጅት አጠናቀዋል ብለዋል፡፡ ስለዚህ ይህ ስልጠና እስከ ታች ድረስ ወርደው አርሶ አደሮቹ ያለባቸውን የክህሎት ክፍተት በመለየት በብቃት በማሰልጠን አርሶ አዶሮቹ ከዚህ በፊት ከሚጠቀሙት ከባህላዊ ወደ ዘመናዊነት እንዲቀየሩ ለማድረግ የተሻለ የአኗኗር ዘይቤ ለማድረግ እና ከእንስሳት ሀብታቸው ምርት እና ምርታማነት የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በእጅጉ እንደሚረዳቸው ዶ/ር ደረጀ ጨምረው አስረድተዋል፡፡
ከኦሮሚያ ክልል ከተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎች የመጡት ሰልጣኞች የስልጠና ቆይተን አስመልክተው በሰጡት አስተየያት ስልጠናው ወቅቱን የጠበቀ እና ከዚህ በፍት ሥራቸው ላይ እንቅፋት ሲፈጥሩ የነበሩትን ችግሮች በእጅጉ ይቀርፋል ተብሎ ይታመናል ብለዋል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሴክተር ልማት ፕሮጄክት ብሔራዊ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ባበኩለቸው በስልጠና ላይ ለቆዩት ለአስተባባሪዎች እንዲሁም ባለሙያዎች ባስተላለፉት መልዕክት በዚህ ለ6 ቀናት ያገኛችሁትን ክህሎት ወደየመጣችሁበት ዞንና ወረዳ ስትመለሱ ሳይማሩ ያስተማሩህ ህዝቦችን በቅንነት እና በታማኝነት ያላቸውን የክህሎት እና አመለካከት ልዩነታቸውን ለይታችሁ አርሶ አደሮቹን በመገዝ በማብቃት የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ እንዲችሉ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም ሥልጠናው በቀጣይም በ6ቱ ፕሮጀክት ክልሎች በአማራ፣ በደቡብ፣ በትግራይ፣ በጋምቤላ እና በቤኒሻንጉል ክልሎች በተደራጁ የጋራ ፍላጐት ባላቸው ወጣቶች እና ሴቶችን የማሰልጠን ሂደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከፕሮጀክቱ ፌደራል ማስተባበሪያ ዩኒት የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!