በእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ የተደረጁ ቡድኖችን ወደ ዩኒየን ለማሸጋገር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ ፡፡
—————————————————————-
በቡድን ለተደራጁ የማህበረሰብ ክፍሎች በነፍስ ወከፍ 8 ነጥብ 7 ቢሊዮን ድጋፍ በማድረግ እስከ ዩኒየን ደረጃ ለማሸጋገር እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር አስተዋቀ፡፡ በደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል ጌዲዮ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በኘሮጀክትና በመደበኛ እክስቴንሽን በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች የተለየዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የመስክ ምልከታ ጉብኝት ተደርጓል ፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ሀብት ዘርፍ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረገሳ በጉብኝቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ከዓለም ባንክ በተገኘ 176 ሚሊዮን የአሜርካን ዶላር ድጋፍ የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክቱ በተመረጡ ስድስት ክልሎች ተግበራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ እየተካሄደ ያለው ኘሮጀክት ዘርፉን ከማዘመን ባለፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ሲሆን እስከአሁን ባለው እንቅስቃሴ በተሻሻሉ የወተት ለሞች፤ በግ ማሞከት፤ የእንቁላል ዶሮ እርባታና የዓሣ ግብርና ልማት ላይ 10ሺህ በጋራ ፍለጎት የተደረጁ ቡድኖችን ወደ ሥራ ማስገባቱን ዶክተር ፍቅሩ ተናግረዋል፡፡ ኘሮጀክቱ በሚተገበርባቸው በኦሮሚያ፤ በአማራ፤ በደቡብ ብ/ብ/ህ፤ በትግራይ፣ በቤኒሻንጉልና በጋምቤላ ክልሎች ውስጥ በጋራ ፍላጎት የተደረጁ ቡድኖች ወደ ስራ በመግባታቻው በፕሮጀክቱ የተያዘው ግብ እየተሳካ መሆኑን ሚኒስቴር ዴኤታው ጠቅሰዋል፡፡
በተሻሻሉ የወተት ለሞች፤ በግ ማሞከት፤ የእንቁላል ዶሮ እርባታና የዓሣ ግብርና ልማት ዘርፎች ለተደረጁት ሴቶች፤ ወጣቶችና አርሶ አደሮችን የገንዘብና የዓይነት እንዲሁም የመስሪያ ቦታ ድጋፍ እንዲመቻችላቸው በማድረግ ወደ መሠረታዊ ህብረት ስራ ዩኒን እንዲሸጋገሩ በዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በፕሮጄክቱ አተገባባር ሂደት እየገጠሙ ያሉት የመሬት አቅርቦት ውስንነት፤ የእንስሳት መኖ፤ የዓሳ ማጥመጃ ግብዓት እጥረት መፍትሄ በማፈላለግ መፍታት እንዳለበት ሚኒስቴር ዴኤታው አቅጣጫ አስቀምጠዋል ፡፡
የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ዓለማው ዘርፉን በዘለቂነት በማዘመን በተመረጡ የእንስሳት ምርት እሴት ሰንሰለቶች የአምራቾችንና አቀናባሪዎችን ምርታማነት በማሳደግ ወደ ኮሜርሻላይዜሽን ማሰደግ ነው፡፡
በደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል በዲላ ዙሪያ ወረዳ ከኘሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ከሆኑት መካካል ወጣት ደሳለኝ ዳዮሰ በሰጠው አስተየያት 10 አባለት ሆነው ተደራጅተው ከኘሮጄክቱ ባገኙት 100ሽህ ብር የገንዘብና የግንባታ ቁሰቁሶች ድጋፍ ወደ ስራ በመሰማራታቸው በሁለት ዙር 40 በጎችን በማሞካት 30ሽህ ብር ትርፍ ማግኘታቸውን ጠቅሶ በአሁን ላይም በሦስተኛ ዙር 30 በጎችን እያሞከቱ እንደሚገኙ ገልጸዋል ፡፡
ፎቶ ወጠቱ ተጠቃሚ
በወረደው የሽጊዶ ቀበሌ አርሶአደር ዳንኤል ሽጣጦ በበኩላቸው በኘሮጄክቱ በደረገላቸው 6 ሽህ ብር የገንዘብ ድጋፍ የዓሳ ጫጩቶችን በማርባት ከምግብ ፍጆታ ባለፈ ለገበያ ለማቅረብ እየሰሩ መሆናቸው ተናግሮዋል፡፡ በአሁን ወቅትም በጓሯቸው በአዘጋጁትና በተከማቸ ውሃ ኩሬ ውስጥ ከ70ሽህ በላይ የዓሣ ጫጩቶችን በማርባት ለአካባቢው አርሶአደሮች በተማጣጣኝ ዋጋ ለማሰራጨት ማቀደቸውን አስረድተዋል ፡፡
በደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዪ እንደገለጹት ኘሮጄክቱ ወደ ስራ ከገባበት 2012 ዓ.ም ወዲህ 15 ሽህ ሴት አርሶአደሮችና ሥራ አጥ ወጣቶች በ 98 ሽህ በድኖች በማደረጀት ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ በተያዘው በጀት ዓመትም ለኘሮጄክቱ በተመደበው 225 ሚሊዪን ብር 1ሽህ 232 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ከአርሶአደሮች፤ ወጣቶችና ሴቶች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በተማሳፍ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ ተነግረዋል፡፡
ከአባለቱ ማከከልም ጠንከራ እንቅስቃሴ ያሰዩት 39 ቡድኖችን ወደ ህብረት ስራ ማህበራት ለማሸጋገር የምስክር ወረቀትና የመስሪያ ቦታ እንዲያገኙ መደረገጉንም ጨምሮ አስረድተዋል፡፡ አባላቱም ወደ ህብረት ስራ ማህበር ሲየድጉ 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ወደ ዩኒየን ሲሸጋገሩ ደግሞው 8 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ከኘሮጄክቱ ድገፍ እደሚየደርግለቸው አስተውቀዋል፡፡

       

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!