Livestock and Fisheries Sector Development(LFSDP) MOA – in Ethiopia,
በሀገሪቱ ተግባራዊ እየተደረገ ባለው የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ፕሮጀክት/LFSDP/ እስካሁን 760 ሺህ ቤተሰቦች ተጠቃሚ ሆነዋል ተበለ፡፡
ሰሞኑን በሀዋሰ ስካሄድ የቆያው የኘሮጄክቱ የስድስት ወር አፋጸጸም ግምገማ ተጠነቆዋል፡፡
በሀገሪቱ በ176 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር እየተካሄደ ባለው የዓሳ እና የእንስሳት ዘርፍ ፕሮጀክት 760 ሺህ ቤተሰቦች ተጠቃሚ መሆናቸውን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
የፕሮጀክቱን እንቅስቃሴ ለመገምገም ለአራት ቀን የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ ተጠነቆዋል ።
በሚኒስቴሩ የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ሴክተር ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶክተር ቶማስ ቸርነት ለጋዜጣኞች እንደገለጹት የእንሰሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ በሚገባ ባለማደጉ ሀገሪቱ ከዘርፉ የሚገባትን ጥቅም ማግኘት አልተቻለም ብሏዋል፡፡
“ችግሩን ለመቅረፍና የእንስሳትና የዓሳሀብት ዘርፉን ለማልማት የሚያስችል ፕሮጀክት በ176 ሚለዮን የአሜሪካን ዶላር ተቀርጾ ወደ ሥራ ተገብቷል “ብለዋል።
እኤአ ከ2018 እስከ 2023 የሚቆየው ፕሮጀክት ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ደቡብ፣ ትግራይ፣ ቤኒሻንጉልና ጋምቤላ ክልሎች እየተተገበረ መሆኑን ጨምሮ ተናግረዋል።
የእንስሳት ዓሳ ሀብት ምርታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል” ብለዋል።
ፕሮጀክቱ በዋናነት በወተት፣ በዶሮ፣ በዓሣ እንዲሁም በቀይ በስጋ ላይ ትኩረት አድርጎ በክልሎቹ በተመረጡ 58 ወረዳዎችና በ1 ሺህ 755 ቀበሌዎች ላይ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ተግባራዊ እየተደረገ ባለው ፕሮጀክት የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎች፣ የመኖ ዘር፣ የአንድ ቀን ጫጩቶችና ሌሎች ግብዓቶች አቅርቦትና አስተማማኝ የገበያ ትስስር በመፍጠር በዘርፉ ልማት ላይ ትልቅ ለውጥ ለማስመዝገብ ግብ ይዞ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
በፕሮጀክቱ 1 ሚሊዮን 200 ሺህ የዓሳና እንስሳት አርቢዎችንና በቡድን የተደራጁ ሴቶችንና ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን አመልክተዋል።
እስካሁን በተደረገው የፕሮጀክት ትግበራ አርሶና አርብቶ አደሮችን እንዲሁም ወጣቶችና ሴቶችን በማደራጀትና የግብዓት ድጋፍ በማድረግ 760 ሺህ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስታውቀዋል።
በፕሮጀክቱ ለወጣቶችና አርሶ አደሮች ከሚያደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ለወረዳና ቀበሌ ሙያተኞች በስልጠናና በቁሳቁስ አቅርቦት አቅማቸውን የማጠናከር እንዲሁም የእንስሳት ጤና ክሊኒኮችን በህክምና ግብዓቶች የማሟላትና ሌሎችንም ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ተናግረዋል።
በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶክተር ደረጀ ጉደታ በሰጡት አስተያየት ፕሮጀክቱ የዘርፉን ልማት ለማዘመን ትልቅ አቅም እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
ከፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች መካከል 40 በመቶ የሚሸፍነው ክልሉ መሆኑን ጠቅሰው ባለፈው ዓመት ብቻ በ23 ወረዳዎች ውሰጥ በፕሮጀክቱ የታቀፉ ወጣቶችና አርሶ አደሮች በ2 ሺህ 70 ቡድኖች ተደራጅተው በበግና ፍየል ማድለብ እንዲሁም በወተት፣ በደሮና በዓሳ ሀብት ልማት ባካሄዱት እንቅስቃሴ 118 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘታቸውን ተናግረዋል ።
በፕሮጀክቱ ለእያንዳንዱ ቡድን በነፍስ ወከፍ 30 የእርቢ እንስሳት መሰጠቱን የጠቀሱት ኃላፊው በዚህ ዓመት 4 ሺህ 140 የልማት ቡድኖችን በማቋቋም ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉን አብራርተዋል።
ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ ባለፈው አመት 392 ሚሊዮንብር ስራ ላይ መዋሉንና ለዘንድሮ ዓመት 444 ሚሊዮን ብር መመደቡን ተናግረዋል።
በጋምቤላ ክልል ግብርና ቢሮ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ኡሞድ ኦኮንጎ በፕሮጀክቱ ለዓሳ አስጋሪዎች አስፈላጊውን ግብዓትና የቴክኒክ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል ።
የሎጂስቲክስ ችግሮችን በመቅረፍና የዓሳ ሀብት ልማትን ለማፋጠን የሚረዱ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አመልክተዋልክ፡፡
የደቡብ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶክተር አዲሱ ኢዮብ ፕሮጀክቱ የዘርፉን ልማትና ዕድገት ለማፋጠን በወተት፣በስጋ፣ በእንቁላል፣ በማርና ዓሳ ልማት አይነተኛ መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በተለይ ካለፉት ሁለት ዓመት ወዲህ ለአነስተኛ አርሶ አደሮች፣ ለሥራ አጥ ወጣቶችና ለሴቶች ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ማስገኘቱን አስታውቀዋል።
መድረኩ በግማሽ አመት አፈፃጸም የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ተለይተው በቀጣይ የተሻለ ስራ ለማከናወን አቅጣጫ የሚጠቀምበት በመሆኑ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን አስታውቀዋል። በማጨረሸም በኘሮጄክቱ የተከናዋኑት ስራዎችን በጌግዮ ወረዳ የተለየዩ ቀበሌዎች ተዘዋውሯው ጎብኝቶዋል ፡፡