በደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል በጋራ ፍላጎት ቡድን የተደረጁ እማወራ እና አባወራ አርሶአዳሮች  ከእንስሳት ልማት ዘርፍ  ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

———————————————————————————————-

በዓለም ባንክ ድጋፍ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት/LFSDP/ በእንስሳት ሀብት ልማት በወተት፤ በዓሳ፤ በዶሮ እና በስጋ ምርት የእሴት ሰንሰለቶች ላይ የልማት ስራዎችን እያከናወነ እንዳለ ይታወሳል፡፡ የልማት ስራዎች ከሚከናወንባቸው የጋምቤላ፤ የቤኒሻንጉል፤ የአማራ፤ የኦሮሚያና የትግራይ ክልሎች በተጨማሪ የደቡብ ብ/ብ/ህ ክልል አንዱ ነው፡፡

በደቡብ ክልል በካምባታ ጣምባሮ ዞን ቀድዳ ገሜላ ወረዳ በእንስሳት እና ዓሣ ልማት ዘርፍ ኘሮጄክት የተቀፉት እማወራ አርሶአደሮች በተለያዩ የእንስሳት እሴት ሰንሰለቶች በበጋራ ፍላጎት ቡድን በመታቀፍ  ከእንስሳት ምርት ገቢ በማግኘት በኑሮአቸው ላይ ለውጥ እያመጡ እንደሆነ  አባላት ተናግረዋል፡፡

               

በፌደራልና በክልሉ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ፕሮጀክት ባለሙያዎች  በሲዳማ ዳሌ ወረዳ፤ ጌዲዩን ከንባታ ጠንባሮ ቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ ባደረጉት የመስክ ምልከታ በተሸሻለ የወተት ላሞች እርባታ፤ በበግና ፍየል ማሞከት፤ በዓሣ ሀብት ልማት ስራ ላይ በቡድን ተደራጅተው እየሰሩ ያሉትን አርሶ አደሮች የመስክ ቅኝት ተደርጓል፡፡ ጉብኝት በተደረገባቸው የከንባታ ጥንባሮ ዞን ቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ በዜና በናር ቀበሌ አንዱ ነው፡፡

በቀበሌው በተሻሻሉ የወተት ላም ዝርዎች እርባታ ላይ ተደራጅተው የልማት ስራ ተጠቃሚ ከሆኑት አስር ሴት አርሶ አደሮች መካከል ወ/ሮ ታደለች በርሶ አንደኛዋ ናቸው፡፡ ወይዘሮዋ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትዳር የገቡ እና  በቅቤ ንግድ እና በአገር በቀል ዝርያ እንስሳት እርባታ ላይ ተሰማርተው የሚተዳደሩ ሲሆን  ባለቤተቸውም  በአካባቢው ባለ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምህርነት ስራ ተሰማርተዋል፡፡

 

ወይዘሮ ታደለች በጋራ ፍላጎት በቡድን ከመደራጀታቸው ቀድም ብሎ ኑሯቸው ከእጅ ወደ አፍ  እንደነበር ከያዟቸው የአካባቢ ዝርያ ላሞች በቀን ስምንት ሌትር ብቻ እንደሚያገኙ ይናገራሉ፡፡ ነገር ግን የእንሣስሳትና ዐሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ወደ ሚኖሩብቸው ወረዳ ከሌሎች እሳቸውን መሰል ሴቶች ጋር በጋራ ፍላጎት በቡድን ውስጥ እንዲደራጁ ሲጠየቁ ያለማቅማማት በቡድኑ ውስጥ አስር አባላት ሆነው እንደ አንድ አባል ተደራጁ፡፡ ዛሬ በእጃቸው ያሉትን በመጠቀም ከተሻሻሉ ዝርያ ካላቸው እንስሳት መኖዎችን በማምረት ለእንስሳት ምኖ በመጠቀም ከተሻሻሉ ዝርያ ካላቸው እንስሳት በቀን ከ18 እስከ 25ሌትር ወተት በማግኘት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከቤተሰባቸው ፍጆታ የሚተርፋቸውን በቀን 10 ሌትር ወተት ወደ ገበያ በማውጣት አንድ ሌትር በ27 ብር በመሸት እስከ 270 ብር ገቢ በቅን ያገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ አንድ ኪሎ ቅቤ በየሳምንቱ በማምረት እስከ 350 ብር ይሸጣሉ፡፡

 

በሌላ በኩል ከዚህ በፊት በእርሻ ስራ ይተደደሩ የነበሩ በኘሮጄክቱ በደረገለቻው 100ሽህ ብር ድገፍ በአሁን ጊዜ ከእርሸ ስራ ጎን ለጎን በጋራ ፍላጎት ቡድን ውስጥ ስምንት 8 ወንዶች እና ሁለት ሴቶች በመሆን በዶሮ እርባታ ልማት ላይ አርሶአዳሮች መከከል 57 ዓመት እድሜ ባለጸጋ የሆኑት አቶ ማርቆስ ሰደንጎ 2012 ወደ 3000 45 ቀን ጨጮቶችን በማስጋበት ለሶስት ወር የህል በመቀለብ 297 ዶሮዎች ለገቢያ አንዱን ዶሮ bዝቅተኛ ዋጋ 75 ብር የተሸጠ ሲሆን ከፍተኘው እስከ 300 ብር በአጠቀለይ 6100 ብር ገቢ በማህበሩ አበለት በጋራ በከፈቱት የበንክ አከውንት ገቢ ተቀማጭ አድርጎዋል ፡፡ በአሁን ጊዜም ለውጦች እያተዩ በመምጠተቻውን በሁለተኛ ዙር 3000 የአርባ አምስት ቀን የሥጋ ዶሮ ጨጮቶች አስገብተው ከሦስት ወር ቦኃለ ለገቢያ እንደሚያቀርቡና ትርፋማ መሆናቸውን አረገግጠዋል ፡፡

በአጠቃለይ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ፕሮጀክት በደቡብ ብ//ህ ክልል እያደረገ ያለውን ድጋፍ የአርሶ አደሮችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ከላይ በተጠቀሱት የእንስሳት ሀብት የእሴት ሰንሰለቶች ላይ በመስራት ከምርቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ስራዎችን እንደሚሰራ የፌደራል ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ገልጠዋል፡፡

By admin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!