LFSDP PROJECT
ግብርና ሚኒስቴር እንደ ስንዴ ሰብል ምርት በተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያ ላይ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ አስተዋወቀ፡፡
የቦራና ዝርያ ያለቸው በቅርቡ ግብርና ሚኒስቴር የስገበቸው ግደሮች በከፍል
ሰሞኑን 2 መቶ የሚሆኑ የቦረና ዝርያ ያላቸው ጊደሮች 4.6 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጭ በመግዛት በሆሎታ ግብርና ምርምር በአዳአ በርጋ የወተት ከብቶች ንዑስ ማዕከል ማስገባታቸው ተገልጿል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ብሔሄራዊ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ቶማስ ቸርነት እንደ ስተዋቁት
በቀጣይ ጊዜም ፕሮጀክቱ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደ ስንዴ ሰብል ምርት በእንስሳት ልማት ዘርፍ ላይ የያዘውን የ10 ዓመት እቅድ ግብ ለማሳካት ኘሮጀክቱ በከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰራ እንዲሁም በቀጣይም 2 መቶ 50 የሚሆኑ የውጭ ሀገር ዝርያ ያላቸው ጊደሮችን በማስገባት አርሶአደሩ እና አርብቶ አደሩን ከእንስሳት ምርት እና ምርታማነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የፕሮጀክቱ ብሔራዊ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ተናግረዋል፡፡
የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በ 7 ክልሎች 58 ወረዳዎች 1755 ቀበሌዎች በአራት እንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ በወተት፤ በዓሣ፤ በቀይ ሥጋ እንዲሁም በዶሮ እርባታ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ሲሆን በአሁን ጊዜ ፕሮጀክቱ 1 ሽህ 5 መቶ 60 በጋራ ፍላጎት የተደራጁ CIG (እማወራ እና አባወራዎች እንዲሁም ወጣቶችን ተጠቃሚ እያደረገ ያለው ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 60 ፐርሰንት ወንዶች ሲሆኑ ቀሪው 40 ፐርሰንቱ ሴቶች መሆናቸውን ከፕሮጀክቱ ኘላን ክትትልና ግምገማ የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡