በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በዓሣ ሀብት ልማት፤ በአካባቢ እና ማህበራዊ ደህንነት (Environmental and Social safeguard) ዙሪያ ላይ የሚያተኩር በክልሉ ለሚገኙት ከሁለት ወረዳ ለተውጣጡ ከጥቅምት 1- 3/2014 ባምበስ  ወረዳ  የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ስልጠናው በዓሣ ሀብት ልማት እና የአካባቢ ማህበራዊ ደህንነት ጥበቃ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል እና መፍትሄዎች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን ተገልጿል፡:

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት  አስተባባሪ የሆኑት አቶ ይርጋ ተስፋው በሰጡት አስተየያት ፕሮጀክቱ በክልሉ ከጥር 2011 ዓ.ም  ወደ ስራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በሁለት ወረዳ በ99 ቀበሌ 360 የጋራ ፍላጐት ያላቸው አርሶ አደሮችን በጋራ በማደራጀት፤ ግንዛቤን በመፍጠር በአሶሳ ወረዳ እና በቡልድግሉ ወረዳ  አጠቃላይ በ 99 ቀበሌ ውስጥ አደራጅተው ወደ ስራ ከገቡት ከ360 CIG ውስጥ 286 ቀይ ስጋ 60 በዶሮ እርባታ 13 በዓሣ እርባታ ሴቶች እና ስራ አጥ ወጣቶች በጋራ ፍላጎት በማደራጀት በእንስሳት ምርት እና ምርታማነት በማሻሻል ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ በማድረግ  በተለይ  የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ በቀይ ስጋ፤ በዶሮ እርባታ፤ በዓሣ ሀብት ትኩረት በማድረግ ክልሉ እየሰራ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ይርጋ ተስፋው አስታውቀዋል፡፡

እንድሁም በቀጣይ ወተት ልማት ዘርፍ ላይ የጋራ ፍላጎት ያላቸው አርሶ አደሮቹን በማደራጀት ግንዛቤን በመፍጠር ቅድመ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙ እና በአሁን ጊዜ የተለያዩ የተሻሻሉ የእንስሳት መኖ ዘር ልማት ሥራዎችን በማልማት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በተለይም የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት በክልሉ በሁለት ወረዳዎች እየተከናወነ ያለው ስራ ውጤቱ የሚያበረታታ መሆኑን እና በቀጣይም የክልሉ የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ለማሳለጥ ህብረተሰቡ እንደ ሌሎች ክልሎች ከዘርፉ ምርት እና ምርታማነት የበለጠ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ለማድረግ የባለሙያዎች የክህሎት ክፍተትን በመለየት፣ በማሰልጠን እና በማብቃት በዘርፉ ላይ የሚታዩት ችግሮች በአጭሩ መቅረፍ ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በቤኒሻንጉል ክልል ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት የእንስሳት መኖ ልማት እና ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ተወካይ የሆኑት አቶ አብድረህማን ኡስማን በበኩላቸው በሰጡት አስተየያት ፕሮጀክቱ በክልላቸው ሥራ ከጀመረበት ከጥር 2011 ዓ.ም. ጀምሮ በሁለቱ ወረዳዎች ቡልድግሉ ወረዳ እና በአሶሳ ወረዳ ዙሪያ በጋራ ፍላጎት ከተደራጁት ከ360 እማወራ እና አባወራዎች እንዲሁም ወጣቶች በአሁን ጊዜ ከሲአይጂ ወደ ኮኦፕሬቲቭ ደረጃ በማደግ ላይ እንደሚገኙ እና በክልሉ ኘሮጀክቱ በእንስሳት ዘርፉ ላይ ውጤታማ እመርታዊ ለውጦች እያስመዘገበ መምጣቱንና  ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን በተጨማሪም በአሁን ጊዜ በክልሉ የእንስሳት ልማት ዘርፉ ላይ እየታዩ የመጡ ለውጦች አርሶ አደሮቹ ከእንስሳት ምርት እና ምርታማነት ተጠቃሚነታቻው እየጨመረ መምጣቱ በዘርፉ እንዲሰማሩ ተነሳሽነታቸው እየጨመረ መምጣቱን የሚያሳይ ምልክት

ነው ተብሏል፡፡

እንደ ክልሉ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት የእንስሳት መኖ ልማት ኤክስቴንሽን አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የእንስሳት ዘርፍ ተወካይ የሆኑት አብዱራህማን ኡስማን ጨምረው እንዳስረዱት በክልሉ በእንስሳት ልማት ዘርፍ ላይ የተለያዩ ችግሮች የሚስተዋሉ ቢሆንም ከነዚህ ውስጥ  ከፍተኛ የገንዲ በሽታ፤ አካባቢው ከሱዳን ጋር አዋሳኝ በመሆኑ ድንበር ተሻጋሪ የበጎች እና ፍየሎች በሽታ፤ የክትባት አቅርቦት አለመመጣጠን እንዲሁም የመድሀኒት አቅርቦት እጥረት፤ በእንስሳት ዘርፍ ላይ የሚሰሩት ፕሮጀክቶች በብዛት ባለመኖራቸው የእንስሳት ልማት ዘርፉን ወደሚፈለገው ለማሳለጥ ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረባቸው አቶ አብዱረህማን ኡስማን ጨምረው አስረድተዋል፡፡ በክልሉ በአሶሳ  ወረዳ በጋራ ፍላጎት የተደራጁት አርሶ አደሮች እና ወጣቶች በሰጡት አስተየያት በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልሉ በሁለት ወረዳዎች በአሁን ጊዜ በቀይ ስጋ፤ በዶሮ እርባታ፤ በዓሣ ዘርፍ  ልማት እየታየ ያለው መልካም ተሞክሮዎች የሚደነቅ መሆኑን አርሶ አደሮቹ ከባህላዊ የእንስሳት አረባብ ዘዴ ወደተሻሻሉ የእንስሳት እርባታ ተደራጅተው መስራታቸው ከዘርፉ ውጤታማ እየሆኑ መምጣታቸውን ማሳያና አመላካች መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይም ከበግ 1000 እስከ 2500 ብር ድረስ ትርፍ እያገኙ በመሆኑ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ገበያ በማቅረብ 140ሽህ ብር ከወጭ ትርፋማ መሆናቸውን በጋራ ፍላጎት ተደራጅተው ወደ ሥራ መግባታቸው አዋጭ መሆኑን እና መንግስት የገበያ ትስስሩን እንዲፈጥርላቸው እና አንዳንድ የመሠረተ ልማት ስራዎችን እንዲስተካከልላቸው ከተደራጁት ከቡድኑ አባላት አርሶ አደሮች እና ወጣቶች ከሰጡት አስተየያት ለማዋቅ ተችሏዋል፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ የሰብል ምርት የሚመረትበት ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በቆሎ፣ማሽላ፣ አኩሪ አተር፣ ጤፍ፣ ሰሊጥ፣ ኑግ፣ ለውዝ፣ በቆሎ፣ ጥጥ፣ በርበሬ ሲሆን  2.94 ሚሊዮን ሄክታር በደን እንደተሸፈነና በዓመት 2400 ቶን የዓሣ ምርት ሊመረት እንደሚችል አቶ አብድረህማን ጠቅሰዋል፡፡ ለወደፊቱም በክልሉ ትልቅ ተስፋ የተጣለበትን የህዳሴ ግድብ ሲጠናቀቅ ለኤሌክትሪክ ማመንጫ፣ ለመስኖ እርሻ፣ ለዓሣ ዘርፍ ልማት ምርትና ከቱሪዝም ዘርፍ አገሪቱ  የምታገኘው ጠቀሜታ ከፍተኛ ድርሻ መኖሩን ከክልሉ የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!