(ጥቅምት 13 ቀን 2014 ዓ/ም) በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት በኦሮሚያ ክልል በቦራና ዞን በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደረገበት የእንስሳት መኖ በመግዛት ለኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ርክክብ አደረገ፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ በርክክቡ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በቦረና ዞን የዝናብ እጥረት ሳይኖር ጥሩ መኖ የሚገኝበት አካባቢ ቢሆንም አልፎ አልፎ በሚከሰተው ድርቅ እንስሳት እንደሚጎዱ ተናግረዋል።
ችግሩን አስቀድሞ ለመከላከል በአካባቢው በቂ የውሃ ሀብት ልማት እንዲኖር ከማድረግ ባለፈ በቂ መኖ የማከማቸት ሥራ ላይ ትኩረት ተደርጎ መስራት አለብን ብለዋል።አሁን ከሚወሰደው ጊዚያዊ መፍትሄ ባሻገር ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት አነስተኛ፣መካክለኛና ትላልቅ የመጠጥና መስኖ ግድቦችን ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ከእንስሳት መኖ ድጋፍ በተጨማሪ 15 የውሃ ማመላለሻ ቦቴዎች በማሰማራት ለህዝቡና ለእንስሳቱ የመጠጥ ውሃ እንዲያቀርቡ እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል
በአሁን ጊዜ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ወደ ስፍራው የተለያዩ ባለሙያዎቹን በመላክ የመልሶ መቋቋሚያ ሥራዎችን በማከናዋን ላይ ይገኘሉ ብለዋል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ዘርፍ ልማት ኘሮጁክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ ር ቶማስ ቸርነት በበኩላቸው እንስሳት እና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ስራውን ከሚሰራባቸው 6 ክልሎች ውስጥ አንዱ በኦሮሚያ ክልል በ23 ወረዳዎች ውስጥ ሲሆን በቦረና ዞን በ11 ወረዳዎች ውስጥ ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ የተነሳ በአሁን ጊዜ በ11 ወረዳዎች ውስጥ ድርቅ በመከሰቱ በርካታ እንስሳቶች የድርቅ ተገላጭ በመሆናቸው ችግሩን ለመቅረፍ የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት በ18 ሚሊዮን ብር ወጭ በማድረግ 77 ሽህ የእንስሳት መኖ ቤልት በመግዛት ለኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ ርክክብ ማደረጉን ተናገረዋል፡፡ዶክተር ቶማስ ለወፊቱም ድጋፉ ተጠናክሮ እደሚቀጥል አብራርተዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የእንስሳት መኖ ርክክብ ያደረጉት አቶ ቶሌራ ደበላ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ችግሩን በዘላቂነት ለመቅረፍ በበጋ ወቅት በመስኖ መኖን ማልማት በሚቻል እና የግጦሽ መሬትን በማልማት Range Land management ላይ በትኩረት ለመስራት በአሁን ጊዜ ድርቁ በተከሰተባቸው ወረዳዎች ላይ ባለሙያዎችን በማሰመራት የተለየዩ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል ፡፡