ሀዋሳ / ደቡብ ክልል (27/02/14 ዓ.ም) በደቡብ ክልል ክልሉ የዓሣ ምርት እድገት ላይ በትኩረት እየተሰረ መሆኑን የክልሉ የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት/LFSDP/ አስተባባሪ አስተዋቁ ፡፡
የኘሮጄክቱ አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዪ እንደገለጹት የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት በክልሉ በ 13 ወረዳዎች ውስጥ ወደ ትግበራ ከገባባቸው በሁለት ዓመት ዉስጥ /2012-12013/ ዓ /ም ባለው ጊዜ ድረስ 25 የጋራ ቡድን ፍላጎት በዓሣ ምርት ልማት ላይ ተደራጅተዋል፡፡
ከተደረጁት ውስጥ 15 ቡድኖች በተፋጥሮ ውሃ አካላት ቀሪው 10 ቡድኖች በዓሣ ግብርና በጋራ ፍላጎት ተደረጅተው እየሰሩ መሆናቸውን አብራርተዋል፡፡
በተለይም በክልሉ የዓሣ ኩሬ እርባታ /pound fish farming /ውጤማ ለማድረግ ከሌሎች የግብርና ስራዎች ጋር የማቀናጀት ተግባራት እየተከናዋነ ይገኛል ብለዋል ፡፡
አርሶ አዳሩ ከዶሮ እርባታ ጋር የገቢ ምንጭ ለማስፋት እና ስርዓተ ምግብ ለማሻሻል የዓሣ እርባታ ስራዎች ከዶሮ እና ሌሎች የግብርና ሥራዎች ጋር በማቀናጀት ተጠቃሚውን በመርዳት የተለዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገልጾዋል ፡፡
የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት በክልሉ ከሚያከናዉናቸው ከአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ውስጥ አንዱ የዓሳ ግብርና ሲሆን ከ2012 – 2013 ዓ.ም ድረስ 7ሺህ 9 መቶ 63 ኪሎ ግራም የዓሣ ምርት የተገኛ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 5 ሽህ 7 መቶ 63 ኪሎ ግራም የቡድን አባለት ለሽያጭ በማቅረብ 32 ሽህ 8 መቶ 49 ብር በማሸጥ ገቢ የገኙ ሲሆን ቀሪው 2ሽህ 2 መቶ ኪሎ ግራም አባላቱ ለቤተሰብ ለምግብ ፍጆታ ማጠቀማቸው አቶ ሙሉጌታ ጨምሮ አስረግተዋል ፡፡
የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት ከተያዙት ተግባራት መካካል የዓሣ ምርት እና ምርታማነት መጨመር ፤በቤተሰብ ደረጃ አመጋገቢን መሻሻል ሲሆን ከዚህ አንዕር በክልሉ

ሁለት ጊዜ የዓሣ ምርት የሚመረት ሲሆን በተፈጥሮ ውሃ አካላት እና በዓሣ ግብርና ተጣቃሚዎች በማደረጃት ወደ ምርት እድገት የማስገባት ስራዎች ተሰርቷዋል ፡፡
የእንስሳት እና አሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ከስጋት የታደጋቸው የአርባምንጭ አሳ አስጋሪዎች
በአርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ በዓሣ ኩሬ ግብርና ከዶሮ እርባታ ጋር በማቀናጀት በጋራ ፍለጎት ከተደረጁት አባላት መካከል ከዚህ በፊት በሐይቅ ላይ ዓሣ በማስገር የሚታወቁት ከአዞ እና ከጉማሬ ጋር ለበርካታ ዓመታት ሲታገሉ በያጊዜ በስጋት ስራቸውን ሲከውኑ ከቆዩት መካከል አንዱ አቶ ቡንዳሶ ቡጃ እንደ ገለጹት በአሁን ጊዜ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው የዓሣ ዓይነቶች በዓሣ ኩሬ በመርባት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ዓመት 12 ኩንታል የዓሣ ምርት ማግኛታቸው እና 30 ኪሎግራም አባላቱ ለምግብ ፍጆታ ተጣቃሚ መሆናቻው እና ዓሣ መብላት በብልሃት መሆኑን የጋራ ፍለጎት ቡድን አባላቶች ለማረጋገጥ መቻላቸውን አረገግጠዋል ፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!