ሰሞኑን ከ 85 በላይ ምርጥ የቦረና ዝርያ ያላቸው ጊደሮችን እና የኮርማ ፍላጎት ያሳዩት በሰው ሰራሽ የማዳቀል ዘዴ በሆሎታ ግብርና ምርምር በአደሃ በርጋ የምርምር ንዑስ ማዕከል እየተሄደ እንደሚገኝ ተገልጾዋል ፡፡
በሆሎታ ግብርና ምርምር ማዕከል ብሄራዊ የእንስሳት ምርምር ማሻሻያ ኘሮግራም አስተባባሪ ዶ/ር ኡልፍና ገልሜሳ እንደገለጹት በእንስሳት ልማት ዘርፍ ላይ ከሚስተዋሉት ዋና ዋና ችግሮች መካከል አንዱ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ሲሆን ይህ ችግር ለመቅረፍ በግብርና ሚኒቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት ፤ ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ፣ከብሔራዊ የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር በዘርፉ የሚተዩት ችግሮችን ለመቅረፍ ባለፉት ክረምት 200 የሚሆኑ ምርጥ የቦረና ዝርያ ያላቸው ጊደሮችን ገዝቶው በማስገባት በአሁን ጊዜ የኮርማ ፍለጎት ያሰዩት ጊደሮች ሰው ሰራሽ የማደቃል ዘዴ እየተከሄደ እንደሚገኝ እና እየተጠቀሙ ያለው አበለዘር/sexed semen / 98 ኘርሴንት ሴት ጥጆችን ልያስገኝ የሚችል መሆኑን ዶ/ር ኡልፍና ተናግረዋል ፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ብሄረዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት እንደገለጹት ከዚህ በፍት ከአንድ አገር በቀል ላም በቀን 1-3 ሊትር ወተት የሚገኝ ሲሆን አርሶ አደሩ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንደልነበረ ጠቁመዉ አሁን ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ችግሩን ለመቅረፍ አርሶ አደሩ ከእንስሳት ዘርፍ ልማት ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የዝርያ ማሻሻል ስራ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰረ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
በተለይ በአሁን ጊዜ በፕሮጄክቱ የታቀፉት እና የተሻሻሉ ዝርያ እየተጠቀሙ ያሉት አርሶ አደሮች በቀን በአማከይ 24 እስከ 36 ሊትር ወተት እያገኙ መሆኑን በደቡብ ክልል የከምባታ እና ጠምባሮ ቀድዳ ጋሜላ ወረዳን እንደ አብነት በመጥቀስ አብራረተዋለል ፡፡
በሆለታ ግብርና ምርምር አደዓ በርጋ ምርምር ንዑስ ማዕከል እየተከናወነ ያለዉን የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ስራ የግብርና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቐማት የተመራ ልዑክ የማዕከሉን እንቅስቃሴ ተዘዋዉሮ ጎብኝታዋል ፡፡