በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ሮቤ ወረዳ በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የተደራጁ አርሶ አደሮች ከእንስሳት ምርት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን አስተዋቁ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት በኩል በተደረገላቸው ድጋፍ መሠረት በአሁን ጊዜ ከ 21 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች 580 የደለቡ ሙክት በጎችን ለገና ገብያ ለማቅረብ ቅድመ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡

ከዚህ በፊትም በ2012 ዓ.ም 74 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች/ CIG ለ6ተኛ ጊዜ በጎች እና ፍየሎችን አደልበው ለሽያጭ ማቅረባቸውን የአርሲ ሮቤ ወረዳ የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ አስታወቁ፡፡

የአርሲ ሮቤ ወረዳ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አስናቀ እንደ ገለጹት ኘሮጀክቱ በወረዳው ከ2013 ዓ.ም ጃምሮ በቀይ ስጋ ከተደረጁ 58 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች /CIG   ውስጥ 49 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች እስከ አሁን ድረስ በወረዳው 6438 በጎች እና ፍየሎች  አደልበዋል ከዚህም ውስጥ 6259 በጎች እና ፍየሎች ተሸጠዋል፡፡ በአሁን ጊዜም ለጋና በዓል ከ21 ሲአይጂዎች ውስጥ 580 በጎች እና ፍየሎችን ለሽያጭ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ የወረዳው የኘሮጀክቱ አስተበባር አቶ ተስፋዬ አስናቀ አብረርተው የአንዱ በግ ዋጋም 2800 እስከ 4500 ይሸጣል ተብሎው ይጠበቃል ተብሏዋል ፡፡

በወረዳው በአጠቃላይ  209 የጋራ ፍላጎት ቡድን የሉ ሲሆን ከነዚህ መካካል በወተት ልማት 57  በቀይ ስጋ 132 እና በዶሮ እርባታ 20 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች  የሚገኙ ሲሆን  በአጠቃለይ 2500 የተለየዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ኘሮጀክቱ ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ እና  ከነዚህም ውስጥ 30 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ ቀሪው 20 በመቶ ወጣቶች እንዲሁም ከእጅ ወደ አፍ የሚኖሩ አርሶ አደሮች እንድሆኑ በወረዳው የኘሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ተስፋዬ አስናቀ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በአሁን ጊዜ በወረዳው ለሚገኙ ባለሙያዎች በእንስሳት ጤና፣ በዶሮ እርባታ ፣ በወተት ልማት፣ በቀይ ሥጋ እንዲሁም በዓሣ ግብርና ላይ የተለየዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እየተሰጠ እንደሚገኝና ኘሮጀክቱ በቀጣይ የአካባቢውን ህብረተሰብ ባገናዘበ መልኩ ድጋፉን አጠነክሮ እንደሚቀጥል አስተባባሪው ጨምሮ አስረድተዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!