በኦሮሚያ ክልል ከትልልቅ የውሃ አከላት እና ኩሬዎች የዓሣ ምርት እና ምርታማናት እየጨማረ መምጣቱ ተገለጸ ፡፡
በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን በአዳማ ወረዳ በቆቃ ግድብ በዓመት 1194 ቶን የዓሳ ምርት እንደ ሚመረት በምስራቅ ሸዋ ዞን በአዳማ ወረዳ የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ አስተዋቁ፡፡
የወረዳው የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት አስተባባሪ አቶ አቡ ያሹ እንደገለጹት ወረዳው ከሚሰራባቸው አራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ውስጥ አንዱ የዓሣ እርባታ ሲሆን በአሁን ጊዜ በአዳማ ወረዳ በዓሣ እርባታ ላይ ከተደረጁት ስምንት የጋራ ፍላጎት ቡድን/ሲኣይጂዎች (Comment interest group)ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ ሁለት ሲኣይጂ በዓሣ ማስገር ላይ የተደረጁ ሲሆን ቀሪው 6 በዓሣ ግብርና ላይ ተደረጅተው እየሰሩ መሆናቸው ተገልጾዋል፡:
በወራዳው 135 አባላት በዓሣ ልማት ላይ የተደረጁ ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 128 ወንዶች ሲሆኑ 5 ሴቶች መሆናቸውን የምስራቅ ሸዋ ዞን የአደማ ወረዳ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ አቶ አቡ ያሹ ተናግረዋል፡፡
በተለይም በባቲ ገርማማ ቀበሌ እና ቶኩማ እንዲሁም አብዲኬኛ 25 አባለት የሚሆኑ የጋራ ፍላጎት ያላቸው ወጣቶች በቀን ከ 40 እስከ 50 ኪሎ ግራም የዓሣ ምርት ከቆቃ ግድብ የሚያገኙ ሲሆን አንድ ኪሎ ግራም 100 እስከ 120 ብር ለገቢያ እንደሚሸጡ በዓሣ ማስገር ላይ የገኛናቸው ወጣቶች ተናግረዋል፡፡
በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል መንግስት ግብርና ቢሮ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ከፍተኛ የዓሣ ባለሙያ አቶ ቡልቡለ ራጋሳ በበኩላቻው የቆቃ ግድብ የውሃ አካል ስፋት 255 ኪ.ሜትር እስኩዪር ሲሆን 1ሺህ 194 ቶን ዓመታዊ የዓሣ ምርት የሚገኝ ሲሆን በግድቡ ላይ የተለየዩ የዓሣ ዝርዎች ይገኛሉ ከነዚህም ውስጥ የቆርሶ፣ አምባዛ፣ ብልጫ፣ ዱባ (አባሳሙኤል) የመሰሳሉት የዓሣ ዝርያዎች እንዳሚገኙ አቶ ቡልቡላ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም ኘሮጀክቱ በሐሮሚያ ሐይቅ እና በሌሎች ኦሮሚያ አከባቢ ሀይቆች እና ትልልቅ ወንዞች ላይ የዓሣ ምርት እና ምርታማናት ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ነው ያሉት አቶ ቡልቡላ፡፡
በተጨማሪም በአሁን ጊዜ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎች ኘሮጀክቱ የዓሳ ምርት እና ምርታማነትን በማሰደግ የህብረተሰቡ ተጣቃሚነት ለማረጋገጥ የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ዝርፍ ኘሮጀክት የተለየዩ የግብዓት አቅርቦቶች ማለትም የዓሳ ማጥማጃ መረብ፣የዓሣ የማጥማጃ ጃልባ፣ የምርት መያዥ ሳጥኖች ኘሮጀክቱ በማቅረቡ በተለይ በ2013 የአብዲ ቶኩማ እና አብዲኬኛ አባላት አምባዛ እና ቆሮሶ ዓሣ በማምረት ፍሌቶ በማዘጋጃት በቀን ከ80 እስከ 130 ኪሎ ድረሰ በመሸጥ ከሶሰት መቶ ሰላሳዘጠኝ ሺህ አንድ መቶ ሀምሳ /339150 ብር ከዓሣ ምርት ገቢ ማግኘታቸውን ከኦሮሚያ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት /LFSDP/ ኘሮጀክት የተገኘ መረጃ ያስረዳል፡፡
ውሃ የምድራችን 71 በመቶ ወይም ሶስት አራተኛውን ይሸፍናል፡፡ የምድር ገጽ ላይ ካለው የውሃ ሽፋን 97.5 በመቶው ጨዋማናት ያለው ሲሆን 2.5 በመቶው ብቻ ከጨው ነጸ ነው፡፡ 98.8 በመቶ ውሃ የሚገኛው በበረዶ እና በከርሰ ምድር ሲሆን 0.3 በመቶ በታች የሚሆነው ውሃ በወንዞች እና ሀይቆች ይገኛል፡፡ በኢትዮጵያ የዚህን ዕምቅ ሀብት ይዞታ ስንመለከት 7400 ካሬ ኪሎ ሜትር የሚጠጉ ሀይቆችና ግድቦች 250 ካሬ ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍኑ ትንንሽ ግድቦችና ኩሬች እንድሁም 7000 ኪ/ሜትር በሀገር ውስጥ ርዝማኔ ያለቸው የውሃ አላለት ይገኛሉ፡፡ በዓለም ከሚመረተው የዓሣ ምርት የአፍርካ አገራት 2.1 ቶን በማምረት ከዓለም 24 በመቶውን ድርሻ እንደሚሸፍኑ ይገመታል፡፡ የዓሣ እርባታ ስራ ለአገር ኢኮኖሚ የለውን አስተዋጾዎ ስንመለት 1 በመቶ ብቻ ድርሻ ያለው ሲሆን በዓመት 51 ሺህ ቶን በላይ ዓሣ በሀገሪቱ ይመረታል፡፡ እስከ አሁን ያለው የዓሣ ሀብት አጠቃቀም በውል ባይተወቅም ግርድፍ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በዓሣ ዘርፍ ላይ የተሰሩት ዓለም አቀፍ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት እና እንደተነበዩት እ.አ.አ. በ2014 ዓ.ም በአለም አቀፍ ደረጃ የዓሣ ፍለጎት 40 ሚሊዮን ቶን እንደሚደርስ ያስያል፡፡ በግንቦት 2014 ዓ.ም በአፍርካ ህብረት በዓሣ እና በባህር ውስጥ እንስሳት ላይ ያተኮረ አዲስ የፖሊስ እስትራቴጅ እና የድርጊት መርሀ ግብር ከአዲስ አጋርነት ለአፍርካ ልማት / NPAD/ ጋር በመተበባር መውጣቱ ይታወሳል፡፡ በዚህ እስትራቴጅ አገርቱዋ ዘርፉን የተሸለ ደረጃ ለማድረስ በሁለት መንጋዶች ላይ አተኩራ እንድትሰራ አማራጭች መንጋዶች ተቀምጠዋል፡፡ ቀዳሚ የሚሆናው ዓሣ ማሰገሩን ሥራ በዘመናዊ ኢኮኖሚ መተግባር እና የገቢያ ትስስሩን የተሻለ ማድረግ ሲሆን በሁለተኛው ደራጃ እንደ ዋና የግብ መለኪያ ሆኖ የተቀመጠው በዘርፉ ላይ የተሻለ ኢንቨስትመንት እንዲከሄድ አገራትም ለአለም አቀፍ ገቢያ የሚያቀርቡትን የዓሣ ምርት እና ፍላጎት እንዲጣጣሙ ማድረግ ነው፡፡ የዓሣ ሀብት በአሁን ወቅት በአፍሪካ ማህበረዊ እና በስነ ምግብ ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጨዋተ ይገኛል በተለይም በአፍሪካ ውስጥ የሚስተዋለውን የምግብ ወስትናን ለማረጋገጥ በተለይም በገጠራማ የአፍርካ ክፍል ከድህነት ወለል በታች የሚገኙ ዜጎችን ለማሳደግ የዓሣ ሀብት ከፍተኛ ድርሻ አለው ስለዚህ ዓሣን መብላት በብሃት ፡፡