በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ሀረርጌ የሐሮሚያ ወረዳ በእንስሳት እርባታ ላይ በጋራ ፍላጎት የተደረጁ አርሶአደሮች እና ወጣቶች ከእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ኘሮጀክት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን የወረዳው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ አስተወቁ፡፡

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በሀሮማያ ወራዳ የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር አሸናፊ ተስፋዩ በበኩላቸው የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት በወረዳቻው በ35 ቀበሌ ውስጥ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ መግባቱን በማስታወስ 213 የጋራ ፍላጎት ያላቸው አርሶ አደሮች እና ወጣቶች በተለያዩ የእንስሳት እርባተ እሴት ሰንሳለት ላይ ተደራጅተዋል ከዚህም መከካል 82 በዶሮ እርባታ፣ 23  በወተት እና 108 በቀይ ሥጋ ላይ የተደረጁ ሲሆን በአጠቃላይ 4159 ተጠቃሚዎች ሲሆን ከነዚህ መከካል 2290 ወንዶች ሲሆኑ 1869 ሴቶች መሆናቸውን በምስራቅ ሐራርጌ ዞን የሀሮማያ ወረዳ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር አሸናፊ ተስፋዬ ገልጸዋል፡

በወረዳው በተለየዩ ቀበሌ የሚገኙ እና በጋራ ፍላጎት የተደረጁ (በዶሮ እርባታ፤ በግ እና ፍየሎች አርባታ ላይ የተደረጁ  ወጣቶች በሰጡት አስተየያት ከዚህ በፊት ትምህርተቸውን  አጠናቀው ምንም ሥራ ያልነበራቸው ሲሆኑ ወጣቶቹ በተለያዩ ችግር ሲጋለጡ እንደ ነበረ የገለጹ ሲሆን ፤ ኘሮጄክቱ ወደ ወረዳው ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የወረዳውን ወጣቶች ከድህነት አላቆ ወደ ልማት ፊታቻውን እንዲያዞሩ አድርጓል ብለዋል ፡፡

በሀሮሚያ ወረዳ የሚገኘው ሀይቅ ወደ ቀድሞው ቦታ እየተመለሰ በመሆኑና የዓሣ ሀብት የሚያበረክተው ማህበረዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ቀላል የሚባል ስላልሆነ እንዲሁም በማህበረዊ አገልግሎቱም ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እንዲፈጥር ለማድረግ እና ከዚህ በተጨማርም በዓሣ ሀብት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ እንዲቻል የወረዳው እንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት በቀጣይ በወረዳው በሚገኘው የሀሮሚያ ሀይቅ ላይ ተጨማሪ የዓሣ እርባታ የጋራ ፍላጎት ቡድኖችን በማደረጀት ወደ ስራ ለማስገበት የተለየዩ እቅዶች እና ጥናቶች እየተሰሩ እንዳሚገኙ ዶ/ር አሸናፊ ጠቅሰዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!