በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ላይ እየተመዘገቡ ያሉ መልካም ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ መቀጠል  እንደ ሚገባ ተገለፀ ::

የካቲት(9/06/2014ዓ/ም:አዲስ አበባ – በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት የሦስት ዓመት አጠቃለይ የኘሮጄክት አፋጻጸም ከባለድርሻ አካላት ጋር  ግምገማ ተካሂዷል።

የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት ከ2010 ጀምሮ በ6 ክልሎች ውስጥ በሚገኙ  58 ወረዳዎች  ውስጥ ባሉ 1 ሺህ 7 መቶ 55 ቀበሌዎች  በደጋማ የአየር ንብረት አካባቢ በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ እየሠራ ሚገኝ ኘሮጄክት ነው።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት  ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት ብሔራዊ አስተባባሪ  ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ኘሮጄክቱ  በአውሮፓውያኑ 2018 በኦሮሚያ፤ በደቡብ ፤ በአማራ  ፣ቤኒሻንጉል ጉምዝ ፣ጋምቤላ እና ትግራይ ስራ  መጀመሩን እና አስታውሰዋል።

እንደ ዶ/ር ቶማስ ማብራሪያ አሁን ላይ በፕሮጄክቱ ስር  10ሺህ 4 መቶ 50 የጋራ ፍላጎት ያላቸው(CIG)  ተደራጅተው  ስራ የጀመሩ መሆናቸውን እና  ከነዚህ ውስጥ 10ሺህ 3 መቶ  33 ወደ ተግባር ገብተዋል።

በአሁን ላይ  8 ሺህ  4 መቶ 50 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች  ምርታቸውን  ወደ ገበያ  በማቅረብ  ለይ እንደሚገኙ የኘሮጄክቱ አስተበባበሪ ቶማስ ቸርነት(ዶ/ር) ገልጸዋል።

በግምገማው ላይ ተሳታፊ የሆኑት የኦሮሚያ ክልል የኘሮጄክቱ አስተበባሪ  ዶ/ር ደረጀ ጉደታ  በክልላቸው  የኘሮጄክቱ እንቅስቃሴ እና አፈጻጸምን አስመልክተው  ገለጻ አድርገዋል ።

እንደ ዶክተር ደረጀ ማብራሪያ በክልሉ 18 ዞኖች  በ23 ወረዳዎች በ581 ቀበሌዎች ኘሮጄክቱ የሚሰራ ሲሆን በዘርፉ ላይም  4ሺህ 1 መቶ 40 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች(CIG)  እንደሚገኙ  ተናግረዋል ።በዚህም  ከ66 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች እንደሚገኙ ተናግረዋል ፡፡

በደቡብ ክልል የኘሮጄክቱ አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ  በበኩላቸው በክልሉ በ 13 ወረዳዎች 463 ቀበሌዎች 2,340 የጋራ ፍላጎት ያላቸው  የተደረጁ አርሶአደሮች የሚገኙ ሲሆን 27,563 ተጠቃሚዎች ውስጥ 15,749 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎች 11,778 ሴቶች መሆናቸውን  አብራርተዋል ።

በአጠቃላይ ይህ ፕሮጄክት በተጀመረባቸው ክልሎች ባለፉት ሦስት ዓመት  የወተት ምርት እና ምርታማነት መጨመር፤የአርሶ አደሩ የአማጋገብ ሥርዓትን ማሻሻል ፤ የዶሮ ሞትን መቀነስ ፤ የተሻሻሉ አሰራሮችን መስፋት ፤ ከእንስሳት ምርት እና ምርታማናት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የተቻለበት እና የአርሶ አደሮቹ ሕይወት በከፍተኛ ደረጀ እየተቀየሠ እንደሚገኝ በግምገማው ላይ የተሳተፉ  የኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች የኘሮጄክቱ አስተባባሪዎች አስረድተዋል ፡፡

በአጠቀላይ ባለፉት ሦስት ዓመታት ውስጥ በርካታ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ችግሮች ቢኖሩም ኘሮጄክቱ የነበረውን ችግሮች በማቋቋም በርካታ ስራዎችን በመስራት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ ውጤታማ ስራዎች  ተመዝግበዋል ነው የተባለው ።

የፕሮጄክቱ ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ይህ በርካታ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ያለው ፕሮጄክት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት በከፍተኛ ጥንቃቄ ሀብት እና ገንዘብ ሳይባክን መሠራት እንዳለበት አሳስበዋል ።በቀጣይ የተሻለ ሥራ በመሥራት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ይኖርብናል ነው ያሉት።

ከሶስት ቀን የኘሮጄክቱ ግምገማ በኋላ በመሬት ላይ የሚታዩ ሥራዎች በሶስት ክልሎች ኦሮሚያ ፤ ደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች በተለየዩ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ  በቀይ ስጋ ፤ በወተት ልማት ፤ በዶሮ እርባታ እንዱሁም  በዓሣ ፤ግብርና እና የእንስሳት ጤና ማዕከል ፥ በወላይታ እና ሆለታ  የሚገኙት የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ማዕከላትን ተዘዋውሮ በመጎብኘት  የታዩ ክፍተቶች እና መልካም ተሞክሮዎች ላይ ሰፉ ያለ ውይይት ተካሄዷዋል ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!