አርሶአደሩ  እንስሳትን በማድለብ ከዘርፉ የሚያገኘውን ጥቅም  ይበልጥ ማሳደግ እንደሚችል ተገለፀ ፡፡

አዳማ(18/ 06/ 2014 /ዓ.ም)_ የእንስሳት ምርት እና ምርታማነትን  ለማሻሻል ል አርሶ አደሩ ባለችው  ማሳ ለይ እንስሳትን  አስሮ በዘመናዊ አሰራር በማድለብ  ለገበያ ቢያቀርብ ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚሆን ተገልጿል።

በዘርፉ ላይ የተሰማሩት የፌዴራል ፣ክልሎች እና  ለዞን ባለሙያዎች የአሰልጠኞች ስልጠና በአዳማ  ከተማ ለሁለት ቀናት ተሰጥቷል።

በግብርና ሚኒስቴር የቆዳ እና ሌጦ ሀብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መላከ አሰፋ በበኩላቸው የስልጠናው አላማ   አርሶ አደሩ የእንስሳት ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ   የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ እንዲችሉ እንስሳትን  በልቅ ግጦሽ  ከማሰማራት ይልቅ   እንስሳቶቹን ባለችው እርሻ  ቦታ በማሳቸው  ላይ አስሮ ማደለብ  እንደላባቸው  እና ይህን አሰራር በተግባር ካዋሉት ይበልጥ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል  ብለዋል፡፡

ይህ የአሰልጣኞች ስልጠናም በዳልጋ ከብት የማደለብ ስርዓት፣ በበግ እና ፍየል ማሞከት፣ ላይ እንዲሁም የክትትል እና ግምገማ ወቅት የሚስተዋሉ  ዘርፈ ብዙ ችግሮችን እንደ ሚቀርፍ ይጠበቀል ተብሏል ፡፡ ይህ  የአሰልጠኞች ስልጠና ሁለት  አደዲስ ክልሎችን ጨምሮ በአጠቀለይ ከ6 ክልሎች ኦሮሚያ፤ ደቡብ፤ አማራ፤ ሲዳማ ፤ ቤንሻንጉል  ጉምዝ እንድሁም  ደቡብ ምዕራብ ኢትዪጵያ  ክልሎች ለተወጠጡ ከ 30 በለይ የአሰልጠኞች ስልጠና  ተሰጥቷል።

አቶ መላከ ሰልጣኞቹ ወደ የመጡበት ክልል ሲመለሱ በቲዎሪና በተግባር  የተማሩትን ሥልጠና እስከ ታች ቀበሌ ድረስ ወርደው አርሶ አደሮቹን በማሰልጠንና በማብቃት ከእንስሳት ሀብቱ ምርት እና ምርታማነት  ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እንዲሰሩ  አሳስበዋል ፡፡  በቀጣይ ሚኒስቴር መስሪያቤቱ በከፍተኛ ትኩረት ሰተው ከሚሰራባቸው ስራዎች መካከል  በሥጋ ሀብቱ ላይ የሚሰተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ አርሶ አደሩም ከእንስሳት ምርቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ በተለይም በ10 ዓመታት ውስጥ  በግብርና ሚ/ት የትኩረት አቅጣጫ ከሆኑት ውስጥ ( 10 in 10 National Agricultural Program) የቀይ ስጋ ምርት በየዓማቱ በ 7.3 ፐርሰንት በማሳደግ በ10ኛው ዓመት መጨረሻ የአንድ ሰው ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ የቀይ ስጋ ምገባ ምጣኔ 10 ኪሎግራም ለማድረስ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን አቶ መላከ ጨምረው  አስረድተዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት/ LFSDP/ ብሔራዊ አስተባባሪ  ዶ/ር ቶማስ ቸርነት በበኩላቸው ኘሮጄክቱ በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት በወተት ፤ በቀይ ስጋ ፤ በዶሮ እርባታ እና በዓሣ ግብርና  እ.አ.አ 2017 ጀምሮ በ 7 በክልሎች እንደሁም በ58 ወረደዎች በ1755 ቀበሌዎች  ከ10ሽህ 4 መቶ 50  የጋራ ፍለጎት ያላቸውን አርሶ አደሮች አደረጅተው ወደ ስራ የገባ ሲሆን  ከነዚህ ውስጥ 10ሽህ 3 መቶ 33 ወደ ተግበር መግባታቸው ከነዚህ ውስጥ 8ሽህ 4 መቶ 50 የሚሆኑት አርሶአደሮች ምርታቸውን ወደ ገቢያ በማቅረብ  ተጠቃሚ መሆን እየቻሉ መሆናቸው ለቀጠይም ኘሮጄክቱ የእንስሳት ልማት ዘርፉን ለማጠነከር  አርሶ አደሮች ከእንስሳት ምርት እና ምርታማናት የበለጠ ተጠቃሚ እንድሆኑ ለማስቻል የበኩሉን   ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዶ/ር ቶማስ ተናግረዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!