ግብርና ሚኒስቴር ከሁሉም ክልሎች ከተውጣጡ ከባለድርሻ አካላት ጋር የዘጠኝ ወር ደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች በሽታ /pesti des petites Ruminates /PPR/ ስርጭት እና ቁጥጥር ግምገማ  በአዳማ ከተማ ለሶስት ቀናት ከ4-6 /09/ 2014 ተካሂዷል፡፡

በሽታው በቫይረስ አማካይነት የሚተላለፍ እና አነስተኛ አመንዣኪ እንስሳቶችን የሚያጠቃ አደገኛ እና ተላላፊ ድንበር ተሻጋሪ በሽታ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ የሆኑት በዕለቱ  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ግርማ ሙሉጌታ በበኩላቸው ደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች መሰል በሽታ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰቱ የታወቀው እንደ አ.አ.አ በ1977  በአፋር ክልል በፍየሎች ላይ መሆኑን ጠቁመው በዚሁ መሠረት በበሽታ የሚሞቱ ከፍተኛ እንስሳት ቁጥር መሆናቸውን በተለይም አነስተኛ አመንዣኪ እንስሳቶች ላይ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ይህን ድንበር ተሻጋሪ የእንስሳት በሽታዎች ችግር ለመቅረፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከክልሎች እና ከጎረቤት አገሮች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አቶ ግርማ ጨምረው አስረድተዋል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር  በእንስሳት ሀብት  ዘርፍ  የበጎች እና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ቁጥጥር እና ስርጭት ብሄራዊ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር አስማማው ዱሬሳ በበኩላቸው በየዓመቱ  በአገራችን 30 ሚሊዮን እንስሳት በበሽታ እንደሚጠቁ እና በሽታው ከሚገኝበቸው ከ70 በለይ የዓለማችን አገራት 60 በመቶ የሚገኙት በአፍሪካ ውስጥ መሆኑን ጦቅሰው  በአለማችን ካለው ህዝብ ውስጥ በከፍተኛ ድህነት የሚኖረው 330 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ በአፍሪካ መካከለኛ ምስራቅ እና በእስያ የሚገኝ ሲሆን ኑሯቸውን የሚመሩት በአነስተኛ አመንዣኪ እንስሳት ከሚያገኙት ገቢ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ዶ/ር አስማማው ጨምረው አስረድተዋል፡፡ ይሁን እንጂ በየዓመቱ ከ1.2 እስከ 1.7 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር በበሽታ ምክንያት ኪሰራ እንደሚደርስም ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በተለይም በአገራችን ኢትዮጵያ 85 ፐርሰንት በግብርና ሥራ የሚተዳደሩ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ የእለት ተእለት ኑሮውን የሚመራው በእንስሳት ህልውና ላይ የተጣለ ሲሆን ይሁን እንጂ ሰፊው የአገራችን አርብቶ አደር በአነስተኛ አመንዣኪ እንስሳት የእለት ተእለት ኑሮውን የሚመራው ቤተሰቦቹን የሚያስተዳድረውን በአመንዣኪ እንስሳት ስለሆነ  ይህን  ደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች  በሽታን ለመከላካል እና ለመቆጣጠር የሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ይጠይቃል ብለዋል ዶ/ር አስማማው፡፡

በመሆኑ በሽታውን  ለመቆጣጠር ብሎም ለማጥፋት በአለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት እንዲሁም በተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (OIE and FAO) በኩል እ.አ.አ በ2030 በሽታውን ከአለም ለማጥፋት ሰፊ ሥራ በግብርና ሚኒስቴር የብሔራዊ ደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች በሽታ ማጥፋት ፕሮግራም ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰፊ ሥራ እየተሰራ የሚገኝ ሲሆን በኢትዮጵያ እ.አ.አ  በ2027 ከደስታ መሰል በሽታ ነጸ ትሆናለች ተብሎ ይገመታል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ብሔራዊ የኘሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት በበኩላቸው ፕሮጀክቱ እስከሁን ድረስ ለደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች በሽታ /Pesti Des Petites Ruminates /PPR/ ስርጭት እና ቁጥጥር የተለያዩ ድጋፎች መደረጉን ጠቅሰው ከነዚህ ውስጥ 31 ደብል ፒክአፕ መኪናዎችን ገዝተው ለክልሎች መሠራጨቱን እና እንዲሁም ለተለያዩ መድሃኒቶች ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ መደረጉንና ለወደፊቱም ድጋፉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ዶ/ር ቶማስ ተናግረዋል፡፡

አገራችን ኢትዮጵያ ከዓለም በ3 ዓመታት ቀድማ በሽታውን ለማጥፋት ብሔራዊ ስትራቴጂ አዘጋጅታ ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደምትገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!