ሰሞኑን በክልሉ በባህር ዳር ዙሪያና አካባቢ በሚገኙት ወረዳዎች በእንሰሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን የመስክ ምልከታ ተደርገዋል
የአማራ ክልል የእንሰሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ዘሪሁን የፕሮጀክቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ አስመልክቶ በጽ/ቤታቸው እንደገፁት የእንሰሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልሉ ከ 2011ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በ 15 ወረዳዎች በ443 ቀበሌዎች በአራቱ የእንሰሳት እሴት ሰንሰለት በወተት 1200 ፣ በዶሮ እርባታ 674 ፣ በቀይ ስጋ 784 እና በዓሣ ዘርፍ 42 በድምሩ 2700 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖችን አደራጅቶ ወደ ስራ ገብቷል ከተደራጁ አርሶ አደሮች ውስጥ 30% ሴቶች ሲሆኑ 23% ወጣቶች መሆናቸውን የክልሉ የእንሰሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት አስተባባሪ አስታውቋል ፡፡
የእንሰሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልሉ የእንሰሳት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አርሶ አደሩ ከእንሰሳት ምርቱ ተጠቃሚ ለማድግ ፕሮጀክቱ የአርሶ አደሮቹን ክፍተት በመለየት ከ 10-25 ዓባላትን በማደራጀት 2700 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ወደ ስራ ገብተዋል በአሁን ጊዜ 36,851 ያሚሆኑት አባላት በክልሉ ከእንሰሳት ምርትና ምርታማነት ተጠቃሚ በመሆን ላይ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል በክልሉ ከ15 ወረዳዎች ውስጥ ባለፈው ዓመት በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ፕሮጀክቱ ከሚሰራባቸው የምስራቅ አማራ 7 ወረዳዎች ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት እንደ ደረሰባቸው እና ለሚመለከተው አከላት ሪፖርት ማድረገቸውን ጠቁመዋል ውጤቱንም በማጠባባቅ ላይ እንደሚገኙ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አስታውቀዋል ፡፡
አቶ ሙሉቀን ዘርሁን የአማራ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት አስተባባር
በዚህም መሰረት በክልሉ ፕሮጀክት ወረዳዎች የተደራጁ አርሶ አደሮች የእንሰሳት ምርትና ምርታማነት እየታየ ያለው ተጽዕኖ እና ማነቆዎችን በመለየት ለአርሶ አደሮች የግንዛቤና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ችግሮችን በመቅረፍ ወደ ስራ በማስገባት እንዲሁም የእንስሳት ምርታማና ምርታማነት ለማሳደግ እንዲችሉ የተለያዩ መሰረተ ልማቶችን ተገንብተዋል፤ ተጨማሪ ስራዎችም የሰውና የእንሰሳት መኖሪያ መለየት ላይ፣ የእንሰሳት ጤና አጠባበቅ ፣ የእንስሳት መኖ ልማት፤ እንዲሁም ዝርያ ማሻሻል ላይ የተለያዩ ስራዎች ተሰርተዋል በዚህም በክልሉ 36851 የሚሆኑ ስራአጥ ወጣቶች እና ሴቶች ከእንሰሳት ልማት ዘርፍ ተጠሚዎች መሆናቸውን ኙ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
በሌላ በኩልም ከ2700 የጋራ ፍላጎት ቡድን የፕሮጀክቱን መሰረታዊ መስፈርት ያሟሉ 48 የሚሆኑ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ወደ ህብረት ስራ ማኅበር/ኮፒሬቲቭ አድገዋል ከነዚህም ውስጥ 33 (በወተት ልማት ላይ 24፣ በዶሮ እርባታ 4 እና በቀይ ስጋ 5) የሚሆኑት በአሁን ጊዜ ወደ ስራ ገብተዋል ለእያንዳንዱ ህብረት ስራ ማህበር 1.5 ሚሊዮን ብር የዓይነት ድጋፍ ኘሮጄክቱ ማድረጉን ከክልሉ ፕሮጀክት አስተባባሪ ጽ/ቤት የተገኘ መረጃ ያመለክታል፡፡