የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የ2014 እቅድ አፈፃፀም እና በ2015 ዕቅድ ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት ማካሄዱ ተገልጿል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር እንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በ2014 የዕቅድ አፈፃፀም እና በ2015 ዕቅድ ከክልሎች እና ከባለድርሻዎች አካላት ጋር ለ 3 ቀናት ሲያካሂድ የቆየው ውይይት መጠናቀቁ ተገለጸ፡፡

የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ከ2010 ጀምሮ በ6 ክልሎች በ58 ወረደዎች 1 ሽህ 7 መቶ 55 ቀበሌዎች በደጋማ የአየር ንብረት አካባቢ በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ እየሰራ የሚገኝ ፕሮጀክት ሲሆን በአሁን ጊዜ 160 ሽህ 400 ተጠቃሚዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

 

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት በበኩላቸው ፕሮጀክቱ እንደ እ.አ.አ በ2018 በ6 ክልሎች  በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በአማራ በቤኒሻንጉል፣ በጋምቤላ፣ ትግራይ ክልሎች  በ58 ወረዳዎች ስራ የጀመረ ሲሆን 10ሽህ 4 መቶ 50 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ሲአይጂዎችን አደራጅቶ ስራ የጀመረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 10ሽህ 3 መቶ 33 ወደ ተግባር መግባታቸው እና በአሁን ጊዜ 9 ሽህ 4 መቶ 40 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች  ምርታቸውን  ወደ ገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙና ከዚህ ውስጥ ከቤተሰብ ምግብ የተረፈና ወደ ገበያ ከቀረቡት ውስጥ በጥቅሉ 2.2 ቢሊየን ብር በላይ ትርፍ ሲያገኙ ከዚህ ውስጥ የተጣራ ትርፍ 940 ቢሊየን 651ሽህ 1መቶ 15 ማግኘታቸውን የፕሮጀክቱ ብሄራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ገልፀዋል፡፡

ለአብነት በኦሮሚያ ክልል የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ደረጀ ጉደታ በክልላቸው የፕሮጀክት እንቅስቃሴን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት መሠረት በክልሉ በ18 ዞኖች  በ23 ወረዳዎች በ581 ቀበሌዎች ፕሮጀክቱ የሚሠራ ሲሆን 4ሽህ 1 መቶ 40 ሲአይጂ የሚገኙ ሲሆን 66 ሽህ በላይ ተጠቃሚዎች እንደሚገኙ በቀረቡት ርፖርት ለማወቅ ተችሏል፡፡

ይሁን እንጂ በአሁን ጊዜ 339 ሲአይጂ መካከል  59 የሚሆኑት ወደ ኮፕሬቲቭ  ያደጉ ሲሆን ከዚህ ውስጥ  በወተት 13፣ በዶሮ እርባታ 8፣ በቀይ ሥጋ 36፣ በዓሣ 2 ወደ ኮፕሬቲቭ  ማደጋቸውን  ዶ/ር ደረጀ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ በደቡብ ክልል የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ እንዳሉት በክልሉ በ 11  ወረዳዎች 3963 ተጠቃሚዎች የሚገኙ ሲሆን 1977 የጋራ ፍላጎት ከተደራጁት ውስጥ አርሶአደሮች  በአሁን ጊዜ 281 የሚሆኑት ወደ ኮፕሬቲቭ ያደጉ መሆናቸውን አቶ ሙሉጌታ ጠቁመው ባለፉት ሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ፕሮጀክቱ በክልሉ በተለያዩ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ሥራ ከጀመረ ወተት ምርት እና ምርታማነት መጨመር፤ አርሶ አደሩ የአመጋገብ ሥርዓትን ማሻሻል፤ የዶሮ ሞትን መቀነስ ፤ የተሻሻሉ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋት፤ ከእንስሳት ምርት እና ምርታማነት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የተቻለበት እና የአርሶ አደሮቹ ሕይወት በከፍተኛ ደረጃ እየተቀየረ እንደሚገኝ የኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ካቀረቡት ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል፡

የአማራ ክልል የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ዘሪሁን በበኩላቸው የፕሮጀክቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ አስመልክቶ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለፁት የእንስስስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልሉ ከ 2011 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በ 15 ወረዳዎች በ443 ቀበሌዎች በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት በወተት 1200፣ በዶሮ እርባታ 674፣ በቀይ ስጋ 784 እና በዓሣ ዘርፍ 42 በድምሩ 395 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖችን አደራጅቶ ወደ ስራ ከገቡት አርሶ አደሮች መካካል ውስጥ 30% ሴቶች ሲሆኑ 23% ወጣቶች  መሆናቸውን የክልሉ የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አስታውቀዋል፡፡

 

የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልሉ የእንስሳት ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ አርሶ አደሩን ከእንስሳት ምርቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቱ የአርሶ አደሮቹን ክፍተት በመለየት ከ10-25 አባላትን በማደራጀት 395 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ወደ ስራ በማስገባት  በአሁን ጊዜ 36,851 የሚሆኑት አባላት በክልሉ ከእንስሳት ምርትና ምርታማነት ተጠቃሚ እያደረገ  እንደሚገኝ ከክልሉ በቀረበው ሪፖርት ለማዋቅ ተችሏል፡፡ ይሁን እንጂ በክልሉ በ7 ወረዳዎች ውስጥ ባለፈው ዓመት በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ፕሮጀክቱ ከሚሰራባቸው የምስራቅ አማራ ውስጥ ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው እና  ለሚመለከተው አካላት ሪፖርት ማድረገቸውን ጠቁመው  ውጤቱንም በመጠባበቅ እና በቀጣይም መልሶ ለማቋቋም ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ የአማራ ክልል የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ዘሪሁን ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሠረት በክልሉ ፕሮጀክት ወረዳዎች የተደራጁ አርሶ አደሮች የእንስሳት ምርትና ምርታማነት ላይ የሚታዩ ማነቆዎችን በመለየት እና በውይይት በመፍታት ለአርሶ አደሮች የግንዛቤና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን በመስጠት ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍ ወደ ስራ በማስገባት ከእንስሳት ምርት እና ምርታማነት ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ተደርገዋል ነው ያሉት አቶ ሙሉቀን፡፡

ለአብነትም የተለያዩ በፕሮጀክት ወረዳዎች የተለያዩ መሠረተ ልማቶችን የገነቡ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የሰውና የእንስሳት መኖሪያን በመለየት የእንስሳት ጤና አጠባበቅ፣ የእንስሳት መኖ ልማት፤ እንዲሁም ዝርያ በማሻሻል ላይ የተለያዩ ስራዎች በክልል እየተከናወነ መሆኑን  ከሪፖርቱ ለማወቅ ተችሏል ነው ያሉት፡፡

በአሁን ጊዜ 395 የጋራ ፍላጎት ቡድን ውስጥ የፕሮጀክቱን መሰረታዊ መስፈርት ከሞሉት ውስጥ 78 የሚሆኑ ወደ ህብረት ስራ ማኅበር በመግባት ለእያንዳንዱ 1.5 ሚሊዮን ብር የዓይነት ድጋፍ ፕሮጄክቱ ማድረጉን ከክልሉ የፕሮጀክት አስተባባሪ ሪፖርት ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!