በእንስሳት ልማት ዘርፍ በመደራጀት የተሻለ ገቢ ከማግኘት አልፈን ሌሎችንም ተጠቃሚ እያደረግን ነው፡፡

 

ታኅሳስ 07/04/2015) ( Lfsdp)በሲዳማ ክልል በአነስተኛ ገቢ ይተዳደሩ የነበሩና ሥራ አጥ ወጣቶች እና ሴቶች  በእንስሳት ልማት ተደራጅተው በመሥራት ከራሳቸው አልፎ ሌሎችንም ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን ገለጹ።

በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ አርሶ አደሮችና ወጣቶች ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ በማቅረብ የአካባቢውን ሕብረተሰብ ተጠቃሚ በማድረግ አርዓያነት ያለው ተግባር እየፈፀሙ መሆኑን የክልሉ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ፕሮጀክት አስታውቋል ።

 

በልማት ፕሮጀክቱ በርካታ አርሶ አደሮች በማህበር ተደራጅተው በመሥራት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ላይ የሚገኙ ሲሆን ከራሳቸው አልፎ ሌሎችንም ተጠቃሚ እያደረጉ መሆኑን  ያነጋገራቸው የማህበሩ አባላት ገልጸዋል።

አርሶ አደሮቹና ወጣቶቹ በተለያዩ የእንስሳት ልማትና ተዋፅኦ ውጤቶች የራሳቸውንና ቤተሰባቸውን ኑሮ በማሻሻል ሌሎችንም ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጸዋል።

በእንስሳት ማደለብ፣ በዶሮ እርባታና በወተት ልማት እንዲሁም ሌሎች ሥራዎች ስኬታማ ሆነናል ሲሉ ገልጸዋል።

የሀዋሳ ከተማ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት አስተባባሪ ደረጀ ሲመኖ እና የዳሌ ወረዳ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት አስተባባሪ አሰፋ ደሌ፤ የአርሶ አደሮቹ ተግባር ተጨባጭ ውጤት የታየበትና በህይወታቸውም ላይ ለውጥ ማምጣቱን ተናግረዋል።

በእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ እየተካሄደ የሚገኘው የልማት ሥራ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው አርሶ አደሮች፣ ሥራ አጥ ወጣቶች እና ሴቶችን ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን  ገልጸዋል።

የሲዳማ ክልል የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት አስተባባሪ እያሱ ክፍሌ፤ በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ተደራጅተው እየሰሩ ያሉ ወጣቶችና አርሶ አደሮች ከራሳቸውም ያለፈ ጥቅም እያስገኘ ነው ብለዋል።

 

በ2012/2013 ዓ.ም የጋራ ፍላጎት ያላቸውን ዜጎች በወተት፣ በሥጋ፣ በዶሮ እና ዓሳ ልማት እንዲደራጁ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲገቡ መደረጉን አስታውሰው፤ በሥራቸው ውጤታማ መሆናቸውን ተነግሮዋል ፡፡

 

በክልሉ ከተደራጁት 363 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች መካከል አራቱ ወደ ሕብረት ሥራ ማህበር መሸጋገራቸውና ከ4 ሺህ 700 በላይ ዜጎች የኑሮ ሁኔታቸው እንዲሻሻል በማድረግ ቀጥታ ተጠቃሚ አድርጓቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።

የፌደራል የእንስሳት ዓሳ ሃብት ልማት ፕሮጀክት ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ እ.አ.አ. ከ2018 ጀምሮ በተለያዩ ክልሎች በሚገኙ 58 ወረዳዎች በ1 ሺህ 755 ቀበሌዎች የአርሶ አደሩን የእንስሳት ልማት ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየሰራ ይገኛል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!