በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች የመስክ ምልከታ ተካሂደዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር በዓለም ባንክ የሚደገፈው እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት  አርሶ አደሩ ከእንስሳት ምርት እና ምርታማነት የምግብ ዋስትናቸውን እያረጋገጡ  መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ሰሞኑን የፕሮጀክቱ የ9 ወር የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ሂት ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ከሚመለከተው ባለድርሻ አካለት ጋር የመስክ ምልከታን ቅኝት ያካተተ ገምግመዋል፡፡    

ፕሮጀክቱ እንደ እ.አ.አ 2018  በ6 ክልሎች  በኦሮሚያ፤ በደቡብ፤ በአማራ፣ ቤኒሻንጉል፤ ጋምቤላና ትግራይ ክልሎች በ58 ወረዳዎች ስራ የጀመረ ሲሆን 10 ሽህ 4 መቶ 50 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች አደራጅተው ስራ የጀመረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 10 ሸህ 3 መቶ  33 ወደ ተግባር መግባታቸው እና በአሁን ጊዜ 9440 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች  ምርታቸውን  ወደ ገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡  ከዚህ ውስጥ ከቤተሰብ የምግብ ፍጆታ የተረፈ ምርታቻውን  ወደ ገበያ ካቀረቡት ውስጥ በጥቅሉ 2.2 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ ያገኙ ሲሆን  ከዚህ ውስጥ የተጣራ ትርፍ 940 ሚሊዮን 651 ሽህ 1መቶ 15 ማግኘታቸው የፕሮጀክቱ ብሄራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በ21 ወረዳዎች  ፕሮጀክቱ ከሚሠራባቸው አንዱ አካል የሆነው  የምስራቅ ሀረርጌ ኮምቦልቻ እና ሀሮሚያ ወረዳ አንዱ አካል ሲሆን  በኮምቦልቻ በወረዳው ከተደራጁት 172 ሲአይጂዎች ውስጥ በአሁን ጊዜ 58 አባላት የሚሆኑት ወደ ኮፖሬቲቭ ማደጋቸው እና ቀሪዎቹም በአሁን ጊዜ ወደ ኮፖሬቲቭ ለማደግ ከፍተኛ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ የወረዳው የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ በሀሮሚያ ወረዳ ካሉት 213 ሲአይጂዎች ውስጥ በአሁን ጊዜ 37 ሲአይጂ ወደ ኮፖሬቲቭ ማደጋቸው ከሁለት ጊዜ በላይ ምርታቸውን ለገቢያ ለማቅረብ መቻላቸውን አርሶአደሮቹ ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአገሪቱ በተከሰተው የተለያዩ ችግሮች ቢኖሩም የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ዘርፍ ለማሳለጥ ፕሮጀክቱ የነበረውን ችግር በማቋቋም  የእንስሳትን  ምርት እና ምርታማነት ላይ እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት  አርሶ እና አርብቶ አደሮችን ከእንስሳት ልማት ዘርፉ ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ከክልሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን በምስራቅ ሀረርጌ ቀርሳ ወረዳ እና ሀሮሚያ ወረዳ ተዘዋውሮ የመስክ ቅኝትና እና  ዳሰሳ ጥናት ያደረጉት  ባለሙያዎች ከሰጡት አስተያያት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት በወተት፤ ዶሮ እርባታ፤ በቀይ ስጋ እና በዓሣ ግብርና ልማት እየሰራ መሆኑን የፕሮጀክቱ ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት  ጠቁመው በቀጣይም በአገሪቱ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉ  ችግሮችን በየደረጃ በመለየት በተለይ በእንስሳት መኖ ልማት፤ በእንስሳት ጤና፤ በእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እንዲሁም በወተት ልማት ላይ የእንስሳት እና ዓሣ  ልማት ዘርፉን ለማጠናከር ፕሮጀክቱ ድጋፉን አጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን ዶ/ር ቶማስ  ተናግረዋል፡፡

በተለይም ፕሮጀክቱ ባለፈው ዓመት የእንስሳት ዝርያን በአገሪቱ የተሻለ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ  እየሰራ መቆየቱን እና  በተለይም የቦረና ዝርያ  ያላቸው ጊደሮችን በማስገባት በኦሮሚያ ክልል አዳ በርጋ፤ በደቡብ ክልል ወላይታ ሶዶ፤ በወልቂጤ በማስገባትና  በተሻሻሉ ዝርያዎች በማዳቀል በአሁን ጊዜ በርካታ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው ጥጆች እየተወለዱ መሆኑን ለማወቅ እንደተቻለ አስተባባሪው ዶ/ር ቶማስ አስታውቀዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር በዓለም ባንክ የሚደገፈው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት (LFSDP) በርካታ ስራዎችን ከክልሎች ጋር በቅንጅት እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ሰሞኑን  በ 12 ሚሊዮን ብር ወጭ ያደረገባቸውን የዓሣ ጫጩት ማጓጓዥ/ Live fish Carrier /ለሦስት ክልሎች ማበርከቱ የሚታወስ ነው፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!