Sorry, you are not allowed to access this page. በአማራ ክልል በእንስሳት እና ዓሣ  ዘርፍ ኘሮጀክት በ15 ወረዳዎች ውስጥ 36,851 ተጠቃሚዎች ዉስጥ 8578 የሚሆኑት ወጣቶች ነቸው ተበለ ፡፡ -

 

የክልሉ እንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ ሰሞኑን  በአዳማ ከተማ ከመጋቢት  6-8/07/15 ዓ.ም  በተካሄደው 2014/2015 ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈጸጸም በቅረቡት የክልሉ ሪፖርት ላይ  እንደ ተገለጸው  ኘሮጀክቱ ከ2011 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ በክልሉ ካሉት 183 ወረዳዎች ውስጥ በ15 ወረዳዎች፣ በ475 ቀበሌዎች  ውስጥ በወተት 1200፣ በዶሮ እርባታ 674፣ በቀይ ስጋ 784 እና በዓሣ ዘርፍ ልማት 42 በድምሩ 2700 ከተደራጁ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ውስጥ 30 በመቶ ሴቶች ሲሆኑ 23 በመቶ ወጣቶች መሆናቸውን በአማራ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን አስታውቀዋል፡፡

በተለይም በምስራቅ አማራ ካሉት  7 ወረዳዎች ዉስጥ 5ቱ ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ የኘሮጀክቱ  ስራዎች በወቅቱ በነበረው ጦርነት ምክንያት  የወደሙ ሲሆን ሀገሪቷ ከተረጋጋች በኋላ በአሁን ጊዜ  የመልሶ ማልማት ስራዎችን በማከናወን የተጎዱ የኘሮጀክት ወረዳዎችን ወደ ቀድሞው  ልማት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡

እንዲሁም በርካታ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች (ከሲአይጂ) ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህባራት  እንድሁም ወደ  ዩኒን  እያደጉ መምጣተቻውን የክልሉ የኘሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ዘሪሁን ጨምረው አስረድተዋል፡፡ በተለይም በክልሉ በ2012/2013 ዓ.ም ከተደራጁ 2700 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ውስጥ በወተት 50፣ በዶሮ እርባታ  17፣ በቀይ ስጋ 34 እና በዓሳ 2  በአጠቀለይ በአሁን ጊዜ  103  የሚሆኑት ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት በማሳደግ በፕሮጀክቱ በደረጃ ሁለት ድጋፍ እየተደረገላቸዉ ያሉ ሲሆን በደረጃ ሶስት/ዩኔኖች ደግሞ በመኖ ማቀነባበር 4 ፣ በአሳ ማምረት 1 ፤ በወተት ማቀነባበር 5 ማደጋቸውን እና በፕሮጀክቱ ድጋፍ እየተደረገላቸዉ ያሉ መሆናቸዉን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!