(ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ፡አዲስ አበባ)፡ የአርባ ምንጭ ዓሳ ጫጩት ብዜት ማዕከል በጋሞ ዞን የሚገኙ የኅብረሰብ ክፍሎችን በአሳ ምርት ተጠቃሚ እያደረገ ነው። ይህ ማዕከል የአሳ ሀብትን ከሀይቆች ወደ አርሶ አደሮች ጓሮ በማስፋት እየሰራ ይገኛል። በጋሞ ዞን የላንቴ ዓሳ እርባታ ማሕበር በዚህ ረገድ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል አንዱ ነው።
አርሶ አደር አቶ ባሶ ባጆ የእድሜያቸውን አብዛኛውን ጊዜ በጋሞ ዞን በሚገኙት አባያ እና ጫሞ ሐይቆች በመንሳፈፍ በአሳ ማስገር እንዳሳለፉ ይናገራሉ። እርግጥ ለአርባ ምንጭ ከተማ ዝነኛ አሳ ቤቶች የሀይቁ በረከቶች ቢያበረክቱም ህይወታቸውን በውሃው ላይ ፈተና እንደነበረው ይናገራሉ። በተላይ ከጉማሬ እና አዞ ጋር ከፍተኛ ፈተና ደቅነውብኝ ነበር ይላሉ ።
አሁን ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለዓሳ ሀበት የተሰጠው ትኩረት አቶ ባሶን ወደ አባይ እና ጫሞ ሀይቆች ሳይሆን በጓሯቸው ዘጠኝ ትላልቅ ኩሬዎችን አዘጋጅተዋል። በግብርና ሚኒስቴር ስር በዓለም ባንክ የሚደገፈው የእንስሳት እና አሳ ሀብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ባገኙት ድጋፍ ከአርባ ምንጭ ዓሳ ብዜት ማዕከል የዓሳ ጫጩቶችን በማምጣት በኩሬው ያራባሉ።
እርሳቸው እና ጓደኞቻቸው አሁን ሀይቅ አስሶ ክንድን አዝሎ ዓሳ ከመፈለግ ይልቅ በጓሯቸው በቀላሉ የደረሰ ዓሳ ለይቶ ወደ ማውጣት ተሸጋግረዋል ። በአካባቢ ለሚገኙ ሆቴሎች ሳይቀር የዓሳ ምርት እያቀረቡ መሆናቸውን ተናገርዋል።
በስፍራው ተገኝተን ባደረግነው ቅኝት እንዳስተዋልነው በእነ አቶ ባሶ ማህበር አሳ ማብሰያ እና ማጠራቀሚያ ቁሳቁሶች እንድሁም መንገደኞች አሳ ይመገባሉ ። የዓሳ ሾርባም ይጠጣሉ ።
የአርባ ምንጭ አሳ ጫጩት ማባዣ ማዕከል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ እህት በቀለ ማዕከሉ በስድስት ዓመታት የምስረታ ጊዜው በአርሶ አደሮች በኩል ከፍተኛ የአሳ ጫጩት ፍላጎት ጥያቄ እየቀረበለት መሆኑን ገልጠዋል። እንደ ደቡብ ክልል አንድ መሆኑን ተናገረው፡ በሚቀርበው ፍላጎት መሠረት እያባዙ እንደሚያሰራጩ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ህብረተሰቡ ስለ ዓሳ እርባታ ያለው ግንዛቤ ከፍተኛ ደረጃ እያደገ መሆኑን ጠቁመዋል። ማዕከሉ በዓመት ከ400 ሺህ በላይ የዓሳ ጫጩቶችን እያባዛ በማሰራጨት ላይ ይገኛል።
ክልሉ በርካታ የውሃ ሀብት ያለው ነው የሚሉት በደቡብ ክልል የእንስሳት እና አሳ ዘርፍ ልማት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ በክልሉ 18 ሺህ ቶን ምርት የማምረት አቅም እንዳለው ይገልጻሉ። ይሁን እና ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ግን ከ20 እስከ 30 በመቶ ያልዘለለ ነው ብለዋል። አሁን ላይ ግን ዓሳ ሀብቱ በጥምር ግብርና ኩሬ ላይ ጭምር በሚሰራ ስራ ተስፋ ሰጭ ምርት እየታየ ነው ብለዋል።
በቀጣይም በክልሉ የዓሳ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ ድጋፋችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት። በደቡብ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወተት፣ከአሳ፣ዶሮ እና ቀይ ስጋ ዘርፍ ላይ በተሰማሩ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ ሦስት ቡድኖችና ማህበራት በኩል በተከናወን ተግባር ከ285 ሚሊን ብር በላይ ትርፍ ተገኝቷል። ይህም ማህበራቱ የራሳቸውን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ አልፈው በፕሮጅክቱ በሚደረግላቸው ዘርፈ ብዙ ድጋፍና ጠንካራ የገበያ ትስስር ወደ አካባቢ ሆቴሎች እና ከተሞች ለተጠቃሚዎች ጥራቱን የተበቀ ዓሳ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ ።