(ነሐሴ 11 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ LFSDP) በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ፕሮጀክት የ2015 በጀት አመት 7ኛ ስትሪንግ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በሃዋሳ ከተማ   አካሂዷል።

በስብሰባውም  የ2015 በጀት ዓመት አፈፃጸም እና የ2016 በጀት አመትን ዕቅድ ገምግሞ  አፅድቋል።

ከስብሰባው ማጠቃለያ በኋላ በግብርና ሚኒስቴር በእንስሳት እና ዓሣ  ዘርፍ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ በክቡር ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ የተመራ ልዑክ በሲዳማ ክልል  በእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ዙሪያ የተከናወኑ ተግባራትን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

 

በጉብኝቱም በክልሉ በሚገኙት  በዳሌ ወረዳ እና በሀዋሳ ዙርያ ወረዳ  ሲሆን በወተት ልማት፣  በቀይ ስጋ እንዲሁም በዘመናዊ የዶሮ እርባታ አረባብ  ላይ የተሰማሩት አርሶአሮች እና በጋራ ፍላጎት የተደራጁ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክቷል።

በዚህ ወቅት የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ፍቅሩ ረጋሳ እንደ አገር በተያዘው እቅድ መሠረት ክልሎች በየጊዜው የሚስተዋለውን የወጣቶች ሥራ አጥነት ቁጥር ለመቀነስ ከፍተኛ ገቢ በሚያስገኙ የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ላይ እንዲሰማሩ በማድረግ ልዩ ትኩረት ሰጥተው መስራት እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

ዶክተር ፍቅሩ በአሁን ጊዜ የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እንደ መንግስት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ገልጸዋል።

በሌማት ትሩፋት ኘሮግራም የወተት መንደር በመመስረትና ለትግበራውም አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር የዝርያ ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ የሰው ሰራሽ ማዳቀል አገልግሎት በስፋት በወተት መንደር የታቀፉ አርቢዎችን በማሰልጠን አዳቃይ ቴክኒሻኖችን ክሎት እንዲያዳብሩ እየተደረገ እንደሚገኝም አስረድተዋል ፡፡

ባለፉት አራት ዓመታት የተለያዩ ተግዳሮቶች ቢኖሩም በሲዳማ ክልል በእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት እየተመዘገበ ያለው ስራ ከፍተኛ ውጤት መመዝገብ መቻሉን ከተለያዩ ክልሎች የመጡ  የቢሮ ሃላፊዎች እና የኘሮጀክቱ ሲትሪንግ ኮሚቴዎች ገልጸዋል ፡፡

የሲዳማ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ሃለፍ አቶ ታክሌ ጆምባ ባበኩለቻው   በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጡት ፕሮጀክቱ ከመጀመሩ አስቀድሞ ምንም አይነት ገቢ ያልነበራቸው ወጣቶች እና ሴቶች አሁን በወተት ፣በቀይ ስጋ ፣ በዓሳ እና በዶሮ እርባታ ላይ በመሰማራታቸው ከፍተኛ ተጠቃሚ እያሆኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

በአሁኑ ጊዜ በሁለቱ ወረዳዎች 10 ማህበራት እንደሚገኙ የገለጹት አስተባባተሪው እንደማሳያ በማለት በአንድ የጋራ ፍላጎት ላይ የተሰማሩ ሴቶች  በተለይ በወተት ልማት በቀን እስከ አንድ ሺህ ሊትር ለገበያ እያቀረቡ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።

እስካሁን ድረስ በዘርፉ  በማህበራት ያተደራጁ ወጣቶች ከዘርፉ ከ168 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ እንዳገኙ አስተባባሪው በጉብኝቱ ወቅት ገልጸዋል።

የልዑካን ቡድኑ የክልል ግብርና ቢሮዎች እና የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ሲትሪንግ ኮሚቴ አባላት ያካተተ ነው ዘጋባው Lfsdp.com ነው ።

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!