(አዲስ አበባ 19/09/2023 ዓ.ም LFSDP): የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት በክልሉ ካሉት 23ቱ ኘሮጄክት ወረዳዎች እና  ከባለ ድርሻ አካላት  ጋር በ2015 ዓ.ም ዕቅድ አፈጻጸም  እና ለ2016ዓ.ም  እቅድ ላይ በአዳማ ከተማ የጋራ መድረክ  ተካሂዷል፡፡

 

በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ብሄራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ደረጀ ጉደታ በውይይቱ ወቅት እንደገለጹት እንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት በክልሉ በ23 ወረዳዎች በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለትት ላይ 2551 የጋራ ፍላጎት አባላትን አደራጅቶ  ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ውስጥ በአሁኑ ጊዜ 1154 የሚሆኑት ወደ ማኀበራት ያደጉ ሲሆን በወተት 524፣በቀይ ስጋ 1617 በዶሮ እርባታ  382 በዓሳ ግብርና 28 ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 35 % በላይ   የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ገልፀዋል።

በክልሉ  በርካታ ችግሮች የነበሩ ቢሆንም ይህ ችግሮችን በመቋቋም ልክ እንደ በጋ የመስኖ ስንዴ በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት  ላይ   እምርታዊ ለውጦች መመዝገባቸውን  ተናግረዋል።

 በአሁን ጊዜ  የክልሉ አርሶ አደሮች ሴቶች እና ወጣቶች ከእንስሳት ልማት ዘርፍ ተጠቃሚነታቻውን በማረገገጥ ላይ እንደሚገኙ   ዶ/ር ደረጀ ገልፀዋል  ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ግብርና  ቢሮ  ም/ቢሮ  ሀላፊ እና የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ዋና አስተባባሪ አቶ ቶሌራ  ደበላ በበኩላቸው ኘሮጀክቱ በክልሉ ስራ ከጀመረ ጊዜ  አንስቶ  በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት በርካታ ስራዎች እንደተከነዋኑ  አብራርተዋል።

በተለይ በአሁኑ ወቅት  በአብዘኛው አርሶ አደሮች ከእንስሳት እና ዓሣ  ዘርፍ  ልማት ምርት እና ምርታማነትን በመጨመር ከዘርፉ የምግብ ዋስትናቸውን በማረገገጥ  እና  የአካባቢ የገበያ ሁኔታ በማረጋገት ላይ እንደሚገኙ አቶ ቶሌራ ገልፀዋል ፡፡

በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ  በ23ቱ ወረዳዎች ውስጥ 42 ሺህ 219 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች የሚገኙ ሲሆን ከዚህ ውስጥ ወደ መሠረታዊ የህብራት ስራ ማህበራት  ያደጉት 14 ሺህ 100 ሲሆኑ 713 ሺህ 621 ወደ  ህብረት ደረጀ ማደጋቸውን  ከኦሮሚያ ክልል እንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የተገኛ መረጃ ያመለክታል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!