( ሕዳር 03 ቀን 2016 ዓ/ም አዲስ አበባ)፡ በኦሮሚያ  ብሔራዊ ክልለዊ መንግስት  በምስራቅ ሐረሪጌ ዞን በኮምቦልቻ ወረዳ  አንድ ልዩ ትኩረት የሚስብ የሴቶች ማህበር ይገኛል።

ይህ ማሕበር በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት የሚደገፈው የቱላ የወተት አምራች ሴቶች ማህበር  ነው።ይህ ማህበር ከመመስረቱ በፊት የአባላቱ ሕይወት ከእጅ ወደ አፍ በሆን የኑሮ ዘይቤ የተሞላ ነበር። በወረዳው የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ፕሮጀክት መተግበር ከጀመረ ወዲህ ግን ከእንስሳት ምርት እና ምርታማነት የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ  ችለዋል።

የኮምቦልቻ የቱላ የወተት አምራች ሴቶች ማህበር አሁን ላይ  ሦስት ሚሊዮን ብር በላይ  ካፒታል ማስመዝገብ ችለዋል።ይህ ማህበር በኮምቦልቻ ወረዳ በጋራ ፍላጎት ከተደራጁት 172ቱ ውስጥ አንዱ ሲሆን የአባላቱ ቁጥር 90 ሲሆኑ በጋራ ፍላጎት ከማደራጀታቸው በፊት ከአንድ አገር በቀል ላም  ሲያገኑ  የነበረው  በቀን  አንድ ሊትር  ወተት ብቻ የነበረ ሲሆን  በአሁን ጊዜ እስከ 27 ሊትር በእጥፍ መጨመር መቻሉን የማህበሩ አመራሮች ተናግረዋል።

የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ወ/ሮ ፋጡማ አባስ እንደተናገሩት በቀን 500 ሊትር ከአባላቱ እንደሚሰበሰብ ገልጸዋል።

የኮምቦልቻ ወረዳ የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት አስተባባሪ አቶ አብዲ አሊ ማህበራቱ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ባለቤት መሆን  መቻላቸውን ገልፀ፡ይህ ፕሮጅክት ተግባራዊ በመሆኑ ከአሁን በፊት የነበረው የሴቶች ሕይወት ጫና እየተቃለለ እና ከጠባቂነት ተላቀው የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

በአጠቃላይ እንደ ወረዳው አሁን ላይ በአማካኝ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን ሊትር ወተት እየተመረተ መሆኑን አስተባባሪው ገልጸዋል።

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!