በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት  እና World Bank Group እንዲሁም ከክልል ኘሮጀክቶች አስተባባሪዎች ጋር  ሲካሄድ የነበረ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ6ወር የኘሮጀክቱ ስራ አፈጻጸም ግምገማ  ተጠነቋል፡፡

ኘሮጀክቱ እኤአ በ2017 ትግራይ ክልልን ጨምሮ በዳጋመው በአገርቱ በ7 ክልሎች ስራውን የጀመረ ሲሆን እስከ አሁን ድራስ ኘሮጀክቱ ከ1ሚሊዩን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው ።

ባለፉት ዓመታት በአገሪቱ በተከሰተው Covid-19 እንዲሁም በተለያዩ ቦታ የተከሰቱ ግጭቶች በነበሩበት ወቅት ችግሮቹን በመቋቋም የተመዘገቡ ሥራዎች እጅግ የሚያበረታታ እና አርሶ አደሮች ከእንስሳት ምርት እና ምርታማነትን ተጠቃሚ ከመሆን አልፈው ከእንስሳት ዘርፉ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ መቻላቸውን  እንዲሁም ለስራ አጥ ወጣቶች የስራ ዕድል እንዲፈጠር እና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ መደረጉን በግብርና ሚኒስቴር የኘሮጀክቱ ብሔራዊ  አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ገልጸዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!