(ታህሳስ 08 ቀን 2016ዓ.ም አዲስ አበባ (LFSDP)፡ ባለፉት አምስት ዓመታት የተተገበረው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉ ተገለጸ።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ብሄራዊ አስተባባሪ ቶማስ ቸርነት(ዶ/ር) ሰሞኑን በተካሄዳው  የኘሮጀክቱ 9ኛ ተልዕኮ ከክልሎች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር  በደረጉ የጋራ  የምክክር መድረክ ላይ እንደገለጹት የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት እ.አ.አ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ በደጋማው የኢትዮጵያ አካባቢ 7 ክልሎች በ58 ወረዳዎች በ1755 ቀበሌዎች ላይ  እየተተገበረ መሆኑን አብራርተዋል።

 

ዶክተር ቶማስ በተመረጡት በአራቱ የእንስሳት ዕሴት ሰንሰለት  በወተት፣ በቀይ ስጋ ፣ በዶሮ እርባታ እና በዓሣ ግብርና ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ  እንደሚገኝ የተናገሩ ሲሆን በአሁን ወቅት10ሺህ 550 የጋራ ቡድኖች  ተደራጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል።

 

በአሁኑ ወቅት 3 መቶ 94 መሰረታዊ ማህበራት  እና  43 ህብረት ስራ ዪኒየኖች  ወደ ሥራ መግባታቸውን ብሔራዊ አስተባባሪው ዶክተር ቶማስ ተናግረዋል ፡፡

 

በአጠቃላይ ኘሮጀክቱ ከተጀመረ  አምስት ዓመታት ከስድስት ወር ውስጥ  በአራቱ የእንስሳት ዕሴት ሰንሰለት በወተት ፣በቀይ ስጋ ፣ በዶሮ እርባታ እና  በዓሣ ግብርና  በቀጥታ እና ቀጥኛ ባልሆነ መንገድ ከ3 ሚሊዮን 235 ሺህ 648 ህብረተሰብ ተጠቃሚ ሆነዋል።

 

ይህ ፕሮጀክት ለበርካታ ሥራ አጥ ወጣቶች እና ሴቶች የስራ እድል መፍጠሩን  ዶ/ር ቶማስ  ጠቁመዋል።

 

የጋራ ፍላጎት ቡድኖች (CIGs) ትርፋማ በሆነ የንግድ ሥራ ምክንያት የአባወራዎች ገቢ 3.5 ቢሊዮን  ብር ጠቅላላ ትርፍ እና የህብረት ሥራ ማህበራት ደግሞ የተጣራ ትርፍ ወደ 280 ሚሊዮን ብር ገደማ  ማግኘታቸውን አስተባባሪው ገልጸዋል።

 

ኘሮጀክቱ የእንስሳት ብሄራዊ ተቋማት ኘሮግራሞችን በማጠናከር እነ የኢክስቴንሽን ስርዓቱን ለማሳላጥ ለመሥክ አገልግሎት የሚውሉ ለ250 ወረዳዎች እና ለ8472 ቀበሌዎች ልዩ ልዪ የክትባት እና የላብራቶር  የሕክምና መስጫ መሳሪያዎችን ገዝቶ መሰጠቱንም በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

በተጨማሪም ድንበር ተሻጋሪ የበጎች እና ፍየሎች በሽታን ለመቆጣጠር 46 ሚሊዮን 5 መቶ 6 ሺህ  በላይ በግና ፍየሎች ክትባት እንዲያገኙ  ማድረጉን  አብራርተዋል  ፡፡

ፕሮጀክቱ ተግባራትን ለማከናወን የሚረዱ 122 መኪኖችን ፣ከ350 በላይ ሞተርሳይክሎችን፣7 ማቀዝቀዣ የተገጠመላቸዉ 10’ሽህ ሊትር የሚሸከሙ የወተት መኪኖችን እንዲሁም 3 የዓሳ  ጫጩት ማመላለሻ መኪኖችን በመግዛት ለክልሎች መሰጠቱንም ዶክተር ቶማስ ተናግረዋል።

የመረጃ አሰባሰብ እና ትንተና ስርዓቶቹ በጠራ እና በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱም ተመላክቷል።

በቅርቡ  በክቡር የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ የተመራው ልዑክ በሲዳማ ክልሎች በሚገኙ የተለየዩ ወረዳዎች ባካሄደው የመስክ ምልከታም የፕሮጀክቱን ውጤታማነቱን አረጋግጠዋል፡፡

His Excellence  Minster , Ministry  of Agriculture  Girma Amente / PHD/  has conducted discussion on the implementation performance of LFSDP  with World Bank Group  at Hawassa

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!