(ታኀሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ)፡ በእንስሳት እና ዓሣ ልማት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት (LFSDP) በወተት ማቀነባበር ሥራ ላይ  የተደራጁ የህብራት ሥራ ማህበራት ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን የሲዳማ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ቢሮ  ም/ክ  ኃላፊ ዶ/ር  ሚሊዮን ማትያስ  ገለጹ።

የሲዳማ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ቢሮ  ም/ክ  ኃላፊ ዶ/ር  ሚሊዮን ማትያስ   የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት በክልላቸው ባለፉት አምስት ዓመታት በእንስሳት ዘርፍ ልማት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንደ ነበረው ገልጸዋል።

ከዚህ በፊት በዘርፉ ሲስተዋሉ የቆዩት ማነቆዎችን በመቅረፍ በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ በክልሉ እምርታዊ ለውጦች ማምጣት መቻሉን ያነሱት ዶ/ር ሚሊዮን በቀጣይም በክልሉ በሚገኙ ሌሎች ወረዳዎች አርሶ አደሩ በእንስሳት ልማት ዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ  እየተሰራ መሆኑን  አስረድተዋል፡፡

የሲዳማ ክልል የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ እያሱ ክፍሌ  በበኩላቸው በክልሉ ፕሮጀክቱ ጉልህ ፋይዳ እንዳበረከተ ተናግረዋል።

አስተባባሪው ይህን ያሉት በሲዳማ ክልል  በዳሌ ወረዳ በፕሮጀክቱ የታቀፉ ማህበራትን የስራ እንቅስቃሴ በተጎበኘበት ወቅት ነው።

በጉብኝቱ ወቅት ካነጋገርናቸው መካከል ወ/ሮ ስመኝ ደባልቄ አንዷ ናቸው። ከአሁን በፊት የሀገረሰብ የወተት ላሞችን እንደሚያረቡ የተናገሩት እማወራዋ በቀን አንድ ሊትር የማይሞላ ወተት ይገኙ ነበር።

በፕሮጀክቱ ከታቀፉ 2013 ጀምሮ ግን  በአማካኝ እስከ 24 ሊትር ድረስ ማግኘት ችለዋል።

በወረዳው እንደ ወ/ሮ ስመኝ ያሉ 86 እማወራዎች ከሚያረቧቸው የወተት ላሞች በቀን እስከ አንድ ሺህ ሊትር በመሰብሰብ ከምግብ ፍጆታቸው  የሚተርፈውን በቀን ከ500 እስከ 600 ሊትር በላይ ወተት ለአካባቢው ገበያ ያስረክባሉ። በዚህም በቀን ከፍተኛ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በዳሌ ወረዳ የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ የአቶ አሰፋ ዴሳ እንደገለጹት ባለፉት 5 ዓመታት ኘሮጀክቱ በወረዳቸው የበርካታ አርሶ አዳሮችን፣ ወጣቶችን እና የሴቶችን ህይወት ቀይሯል።

ከእንስሳት ልማት ዘርፍ የምግብ ዋስትናን ከማረገገጥ ባለፈ የአካባቢው አርሶአደሮች የዕለት ገቢያቸውንም እያሳደጉ መምጣታቸውን አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ  ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ብሔራዊ አስተባበሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት በበኩላቸው ባለፉት አምስት ዓመታት እየተተገበረ ያለው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

 

ዶክተር ቶማስ በተመረጡ አራቱ የእንስሳት ዕሴት ሰንሰለቶች ማለትም በወተት፣ በቀይ ስጋ፣ በዶሮ እርባታ እና በዓሣ ግብርና ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ የተናገሩ ሲሆን በአሁን ወቅት 10ሺህ 550 የጋራ ቡድኖች  ተደራጅተው ወደ ስራ መግባታቸውን ገልጸዋል።

በቀጣይም ኘሮጀክቱ በአገሪቱ በእንስሳት ልማት ዘርፍ ላይ የሚታዩትን ችግሮችን በመቅረፍ ትኩረት አድርጎ ይሰራል ብለዋል፡፡ ( Lfsdp .com )

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!