ግብርና ሚኒስቴር በአለም ባንክ ባገኘው የበጀት ድጋፍ አማካይነት የአገሪቱን የ10 ዓመታት (2014 እስክ 2034 እ ኤ አ) የዓሣ ሀብት ልማት ማስተር ፕላን በአገር ውስጥ በመስኩ ከፍተኛ እውቀት ያላቸውን ባለሙያዎች ያካተተ የውጭ ተቋራጭ አማካይነት ተጠንቶ በዛሬው ዕለት በአዳማ ከተማ ዶ /ር ዩሐንስ ግርማ የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ሚኒስተር ዴኤታ አማካሪ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ፀድቋል፡፡
የክብር እንግዳው በንግግራቸው የዓሣ ሀብት ስትራቴጂክ ፕላን ለጀመርነው የሌማት ትሩፋት በቀጣይ ለምናካሂዳቸው ተግባራትና እንደ መሪ አቅጣጫ አመልካች እንደሚሆንና ክልሎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም በስትራቴጂክ ዶክሜንቱ የተቀመጡ ተግባራትን በቅደም ተከተል በመተግባር የዓሣ ሀብት ልማቱ ለአገሪቱ የምግብ ዋስትና መረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካትና የሥራ እድል በመፍጠር የሚያደርገውን አስተዋጽኦ ከፍ ለማድረግ መስራት እንደሚያስፈልግ አስቀምጠዋል፡፡
የእንስሳትና ዓሣ ሴክተር ልማት ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት በሚመሩት ፕሮጀክት አማካይነት የ10 ዓመታት የዓሣ ሀብት ልማት ስትራቴጂክ ፕላን መዘጋጀቱ በጣም እንዳስደሰታቸውና የተቀመጡ የትግበራ አቅጣጫዎች በሁለተኛው ዙር የእንስሳትና ዓሣ ሴክተር ልማት ፕሮጀክት ውስጥ በማካተት እንደሚተገበሩ አመላክተዋል፡፡
የዓሣ ሀብት ልማት ዴስክ ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ፋሲል ዳዊት ይህ የ10 ዓመታት መሪ ዕቅድ በየአመቱ እየመነዘርንና እየተገበርን የተቀመጠውን ዉጤት ለማምጣት በልዩ ትኩረት በተለይም የአገሪቱን የምግብ ዋስተና መረጋገጥና በሥርዓተ ምግብ መሻሻል ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ከውጭ የሚገባውን የዓሣ ምርት በመተካት የውጭ ምንዛሬን ለማዳንና ለወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ጠንክረው እንደሚሰሩ አመልክተዋ፡፡
በአገረችን ሀይቆችና ወንዞች ወደ 200 የሚደርሱ የዓሳ ዝርያዎች እንደሚገኙ የተለየዩ ጥነቶች የሚያሳዩ ቢሆንም ከነዚህ ውስጥ ከ190 የማያንሱ ሀገር በቀል ዝርያዎች ሲሆኑ 40 የሚጠጉት በአገረችን ብቻ የሚገኙ የዓሳ ዝርያዎች እና 11 ከውጭ ሀገር የገቡ መሆነቸው አንደንድ ጥነቶች ያማለክታሉ ዘገበው (LFSDP.COM )