(ሰኔ 05 ቀን 2016 ዓ.ም አዲስ አበባ) LFSDP/ በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት የተሠማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ገቢያቸው እያደገ መምጣቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገለፀ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ ወ/ሮ አያልነሽ መለስ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሴክተር ልማት ፕሮጀክት ተሳታፊ የሆኑ የሕብረተሰብ ክፍሎች ገቢያቸው እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
በተመረጡ በአራት ዕሴት ሰንሰለቶች ማለትም በወተት፣ በዶሮ ፣በቀይ ስጋ እና በዓሳ ልማት ስራ ላይ በመሠማራት ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መጥተዋል።
እንደ አስተባባሪዋ ገለጻ በክልሉ በአጠቃላይ እስከ አሁን 63,760 (39% ሴት) አ/አደሮች እና ስራ አጥ ወጣቶችን (26%) ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡
ወ/ሮ አያልነሽ በደረጃ አንድ 862 የጋራ ፍላጎት ቡድን በማደራጀት ወደ ትግበራ የገቡ መሆናቸውን አንስተው ከዚህ ውስጥ 293 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች መስፈርቱን አማልተዉ ወደ ደረጃ 2 የተሸጋገሩ ሲሆን በስራ ላይ ያሉ 519 CIG ከተመረተ ምርት በዘጠኝ ወር ውስጥ 16.6 ሚሊየን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘት መቻላቸውን አብራርተዋል።
አስተባባሪዋ በደረጃ ሁለት ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ 35 ህ/ስ/ማህበራት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ 9.5 ሚሊየን ብር የተጣራ ትርፍ በማግኘት የተጠቃሚዎችን ኑሮ ማሻሻል ችለዋል፡፡
በደረጃ ሶስት 3 ነባር ዩኒየኖች ማለትም ዓሳ፣ በእንስሳት መኖ ማቀነባበር ስራ እንዲሁም በእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ላይ በማሰማራት ለእያንዳንዳቸው 11.5 ሚሊየን ብር በድምሩ 34.7 ሚሊዬን ብር በላይ በመመደብ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ የማስገባት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በያዝነው ዓመትም በክልሉ 8 ሕብረት ስራ ማህበራትን ወደ ትግበራ በማስገባት ስራ የተሰራ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በተሰማሩበት እሴት ሰንሰለት ምርት በማምረት ሂደት ላይ የሚገኙ ሲሆን በተመሳሳይ 2 ስፔሻላዝድ ህ/ስራ ማህበር ወደ ድጋፍ ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተጠናቀቀ ይገኛል፡፡( ምንጭ ደቡብ ኢትዮጵያ እ/ዓ/ሀ/ሴ/ል/ፕ )

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!