ሰኔ 19 ቀን 2016 ዓ.ም.አዲስ አበባ LFSDP):ግብርና ሚኒስቴር ከ25ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን ለዓሣ ልማት ዘርፍ የሚውሉ ጀልባዎችን፣የዓሣ ማምረቻ መረቦችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን ለ9 ክልሎች አስረከበ።
ሚኒስቴሩ 8 Fiber glass ጀልባዎችና 8 ባለ 25 የፈረስ ጉለበት የጀልባ ሞተር ፣6 በአየር የሚነፉ የፕላስቲቸ ጀልባዎችና 6 ባለ 15 የፈረስ ጉለበት ሞተር ፣50 የዓሣ ጫጩት፣ ወላድና ለምርት የደረሱ የኩሬ ዓሣዎችን መሰብሰቢያ መረቦች ፣400 ዓሣ ማቆያና ማዋለጃ የመረብ ኬጆች ፣300 ኬጅ ዓሣ እርባታ የሚዉል የመረብ ኬጆች፣25 ዉሃ ዳርቻ መንቀሳቀሻ የፕላስቲክ ልብስ ገዝቶ ለክልሎችና ለማዕከላት ድጋፍ አድርጓል።
የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ በርክክቡ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ እንዳላት የውኃ ሀብት መጠን የዓሣ ልማት ላይ ገና ብዙ መሥራት ይጠበቅባታል ብለዋል።
ሚኒስትር ዴኤታው ሚኒስቴሩ በ10 ዓመት የዘርፉ የልማት ፍኖተ ካርታ ላይ 550 ሺህ ቶን ዓሣ ምርት ለማምረት ማቀዱን አስታውሰው አሁን ላይ ገና ወደ 200ሺህ ቶን እየተገባ መሆኑን ገልፀዋል።
የዘመናዊ ጀልባዎች ፣ዘመናዊ የዓሣ ማስገሪያ መረቦች እና ሌሎች ቁሳቁሶች ድጋፍም በዘርፉ መንግስት የሰጠውን ልዩ ትኩረት ያመለክታል ብለዋል።
በአገር አቀፍ ደረጃ መተግበር ላይ ያለው የሌማት ቱርፋት ውስጥ ከታቀፉ አራት ዘርፎች አንድ የዓሣ ልማት በመሆኑ የበለጠ ምርታማነትን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት ይገባዋል ነው ያሉት።
አሁን ላይ በዓሣ ልማት ላይ የግሉ ባለ ሀብት እና ወጣቶች በመደራጀት መሳተፍ መጀመራቸው አበረታች ገፅታ ያለው ነው ብለዋል ዶ/ር ፍቅሩ
በቀጣይ መንግሥት ዘርፉ የሚጠይቀውን ድጋፍ አጠናክሮ ለመቀጠልም ቁርጠኛ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው አስገንዝበዋል።
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ልማት ዘርፍ ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት በበኩላቸው በዓለም ባንክ የሚደገፈው ፕሮጀክት ባለፉት ዓመታት ለክልሎች ሲያደርገው የቆየውን ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ድጋፍ የተደረገላቸው የክልል አስተባባሪዎች በበኩላቸው ድጋፉ በዘርፉ ያለውን ምርታማነት ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።