(ሐምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ LFSDP)፡ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የበርካታ አርሶ አደሮችን ሕይወት እየቀየረ መሆኑን ገልጿል።

ክልሉ ይህን የገለጸው ሰሞኑን በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት(LFSDP) ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ፣በዓለም ባንክ  የፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ (Task Team Leader)  የተመራ ልዑክ ቡድን በክልሉ የፕሮጀክቱን አፈጻጸም በተመለከተ የመስክ ጉብኝት ባደረገበት ወቅት ነው።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር አስተባበሪ እና የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ክልሉ በእንስሳት ሀብት ዘርፍ ያለው አቅም ከፍተኛ መሆኑን አንስተው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ኡስማን በክልሉ የሚገኙ አርሶ አደሮች  በተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያ  ተጠቃሚነታቸው በየጊዜው እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

ኃላፊው በተለይ እንደ ክልል በአነስተኛ ማሳ ላይ ምርታማነትን ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን በቅድመ ጉብኝት ወቅት በተደረገ የጋራ መድረክ ምክክር ላይ አብራርተዋል።

አቶ ኡስማን በተለይ የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት በክልሉ ድጋፍ ማድረግ ከጀመረ ወዲህ አርሶ አደሮቹ ገቢያቸውን እያሳደጉ ነው ብለዋል።

አርሶ አደሮቹ የራሳቸውን ገቢ ከማሳደግ በተጨማሪ የወተት ልማትን በመሰሉ ተግባራት ምርታማነትን በማሳደግ በአካባቢው ያለውን የገበያ ሁኔታ እንዲረጋጋ በማደርግ ከፍተኛ ሚና እየተወጡ ነው ብለዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሮጀክቱ እየተተገበረባቸው በሚገኙ አካባቢዎች ተንቀሳቅሰው የመስክ ምልከታ ያደረጉት የፕሮጀክቱ ብሔራዊ አስተባባሪ  ዶክተር ቶማስ ቸርነት እና የዓለም ባንክ ተወካይ ( Task Team Leader,TTL)  ወ/ሮ ብሩክታዊት አሰፋ በፕሮጀክቱ አፈጻጸም መደሰታቸውን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት በክልሉ እና በሌሎች ክልሎችም ላይ ያለው የፕሮጀክቱ አፈጻፀም የተሻለ እና ውጤታማ መሆንን ገልጸዋል።

ቡድን መሪዋ በቀጣይም ከዚህ የበለጠ ለመስራት በፕሮጀክቱ ፍሬያማ ሆኖ እንዲቀጥል ሁሉም ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ተናግረዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ውስጥ የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ በበኩላቸው ክልሉ አዲስ የተዋቀር ከመሆኑ አኳያ የተለያዩ ክፍተቶች ቢኖሩም ፕሮጀክቱ በተገቢው ሁኔታ እንዲተገበር ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በተለይም በፕሮጀክቱ የወጣቶች እና ሴቶች ተጠቃሚነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ በመሆኑ ውጤት ማፍራት መጀመሩን አስረድተዋል።

አቶ ሙሉጌታ በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ በተለይ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ላይ ከፍተኛ ለውጥ መመዝገቡን አብራርተዋል።

አርሶአደሮቹም በአሁኑ ወቅት በአራቱ የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ዕሴት ሰንሰለት ተጠቃሚነታቸውን እያሳደጉ መምጣታቸውን አረጋግጠዋል።

የክልሎች የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት አስተባባሪዎች የተካተቱበት በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት(LFSDP) ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ እና በዓለም ባንክ  የፕሮጀክት ዋና አስተባባሪ (Task Team Leader)  የተመራው ልዑክ ቡድን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጨማሪ በሲዳማ ክልል እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎችም ተዘዋውሮ የፕሮጀክቱን አፈጻፀም ተመልክቷል።( ዘገበውLFSDP.COM) )

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!