ሐምሌ 21 ቀን 2016 ዓ.ም.አዲስ አበባ:LFSDP):ቴክኖሎጂን በመጠቀም በግብርናው ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ ክቡር  ዶ/ር ግርማ አመንቴ  ገለፁ።

 

ክቡር ሚኒስትሩ ይህን የገለፁት የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል  ለአካባቢው ማኀበረሰብ ዝርያቸው የተሻሻለ 40 ጊደሮች እና 14 ወይፈኖችኝ ባስረከበበት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው።

ዶ/ር ግርማ አመንቴ በአገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ውስጥ አንዱ ትኩረት የተሰጠው ጉዳይ በግብርናውን ዘርፍ መዋቅራዊ ለውጥ ማምጣት መሆኑን ጠቅሰው፤ይህ ዕቅድ የሚሳካው ደግሞ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ነው ብለዋል።  ግብርና ሚኒስቴርም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ሥርዓትን የበለጠ ለማጠናከር የተለያዩ ተግባራትን እየከወነ መሆኑን ገልፀዋል።

እንደ ክቡር ሚኒስትሩ ማብራሪያ የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል እየሰራ ያለው የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው የቦረና ዝርያ ጊደሮችን እና ወይፈኖችን ለአካባቢው ማኀበረሰብ ማስረከቡ አንዱ የውጤቱ መገለጫ ነው ብለዋል።

በቀጣይም በአገር አቀፍ የሚገኙ የግብርና ምርምር ማዕከላት የራሳቸውን የውስጥ አቅም በማጠናከር በቴክኖሎጂ ፈጠራ እና ማሻሻያ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉ ነው ያሉት;;

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታው ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ በበኩላቸው ቴክኖሎጂን በመጠቀም የእንስሳት ሀብት ዘርፍ ምርትን በማሳደግ ከውጭ የሚገባውን ምርት ማስቀረት ይቻላል ነው ያሉት።

ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከውጭ የምታስገባውን የእንስሳት ተዋፅኦ ምርት የግብርና ምርምር ውጤቶችን በማስፋፋት መተካት እንደሚገባ ገልፀዋል። የሆለታ ግብርና ምርምር ማዕከል ሥራም አንዱ ማሳያ እንደሆነ አንስተዋል።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ በበኩላቸው እርሳቸው የሚመሩት ፕሮጀክት በግብርናው ዘርፍ መሠረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በተለይ በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ዙሪያ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስተባባሪው አረጋግጠዋል።

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!