(07/03/2017 ዓ.ም: (LFSDP) ፡ የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የበርካታ አርሶ አደሮችን እና ወጣቶችን ሕይወት እየቀየረ ነው ። ወጣት አቦወርቅ ጎሳ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ አዳማ ወረዳ ቀጨማ ቀበሌ ኗሪ ነው። በ2005 ዓ.ም. የ10ኛ ክፍል ትምርቱን እንደ አጠናቀቀ ከሌሎች 10 የቀበሌዋ ወጣቶች ጋር በመሆን በጋራ ፍላጎት በመደራጀት የክልሉ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት(LFSDP)በአደረገላቸው ድጋፍ በዶሮ እርባታ ላይ በመሠማራት ለመጀመሪያ ጊዜ 400 የአንድ ቀን ጫጩት ዶሮችን አስገብተው ከሁለት ወር በኋላ ለገበያ በማቅረብ ከ80ሺህ እስከ 9ዐሺህ ብር የተጠራ ትርፍ ማግኘት እንደቻሉ ይናገራሉ።
እነዚህ ወጣቶች በዓመት 3 ጊዜ የአንድ ቀን ጫጮት ዶሮችን አስገብተው ከ45 ቀን በኋለ ለገበያ የሚያቀርቡ ሲሆን ከወጭ ቀሪ ከ200 ሺህ እስከ 270 ሺህ ብር በዓመት የተጣረ ትርፍ እንደሚያገኙ ወጣት አቦወርቅ ጎሳ አስረድቷዋል ፡፡
በቀጨማ ቀበሌ በጋራ ፍላጎት የተደረጁት ወጣቶች በአሁን ጊዜ የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ ህብረተሰቡ ከዶሮ እርባታ የስርዓተ ምግብ ዋስትና ተጠቃሚነቱን እያረጋገጡ እንደሚገኙ እና ወረዳው የመኖ አቅርቦት፣ መድኃኒት ፣ ከክትባት እና መሰል የተለያየ ድጋፍ እና ክትትል እንደሚያረግላቸው ወጣቶቹ ገልጸዋል። ወጣት አቦወርቅ ለወደፊቱም ከዶሮ እርባታ ጎን ለጎን በጎች እና ፍየሎችን በማሞከት ላይ ትኩረት አድርጎ ለመስራት ዕቅድ ያለው ሲሆን የወረዳው የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ከዚህ በፊት ሲያደርግላቸው የነበረውን የተለመደ ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቋል።
በዚህ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ እና ቀደም ሲል በግ እና ፍየል በመሞኮት ላይ የተሠመሩት ከሁለት ጊዜ በላይ ለገበያ ካቀረቡት አባለቶች መካከል አንዷ የሆኑት ወ/ሮ እመቤት ብርሃኑ በሰጡት አስተያየት ከዚህ በፊት በጎች እና ፍየሎች በመሞከት በተለየዩ ጊዜ ለገበያ ሲያቀርቡ እንደቆዩ ጠቅሰው በአሁኑ ጊዜ የገበያ አዋጭነቱን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት 50 አባለት በጋራ በመደራጀት በዕውቀት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር እየተጠቀሙ ወይፈኖቹ እያደለቡ ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በአዳማ ወረዳ በቆቃ ግድብ ላይ በዓሣ እርባታ ላይ ከተሰማሩት ወጣቶች መካካል የ25 ዓመቱ ወጣት ጋሻው አጎናፍር ከ2014 ዓ.ም 11 የጋራ ቡድን ፍላጎት( CIG) አባላት ተደራጅተው በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ሁለት ጀልባ ፣ አንድ መረብ፣ አንድ ፍሪጂ ተገዝቶላቸው ወደ ስራ የገቡት ሲሆን በአሁን ጊዜ ከተረጂነት ተላቀውበቀን ከ36 እስከ 40 ኪሎ ግራም የዓሳ ምርት እንደሚሰበስቡ እና ከሚጠቀሙት የቤት ውስጥ ፍጆታ ውጭ በቀን 30 ኪሎ ለአዳማ ከተማ እና ለተለየዩ አካባቢ ህብረተሰብ አንድ ኪሎ በ250 ብር በመሸጥ በቀን 4500 የኢት ብር ከዓሣ ምርት ሽያጭ የሚያገኙ እና በወር 135 ሺህ ብር እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡
የአዳማ ወረዳ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ(LFSDP) አቶ አቡ የሹ በወረዳው ኘሮጀክቱ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በ37 ቀበሌ ውስጥ በ220 የጋራ ፍላጎት ቡድን የተደራጁ ወጣቶች ሥራ መጀመሩን ገልጸዋል። አስተባባሪው እንደሚናገሩት አሁን ላይ አጠቃላይ 2488 ተጠቃሚዎች እንዳሉ እና ከዚህ ውስጥ 1193 ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። ኘሮጀክቱ ከዚህ በተጨማሪ በወረዳው ውስጥ የሚገኙትን የገበሬዎች ማሰልጠኛ ማዕከል (FTC ) በማደስ እና በመጠገን አርሶ አደሮቹ የቴክኖሎጂ ሽግግር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከፍተኛ ጥረ እየተደረገ መሆኑንም አስተባባሪው ጨምረው አብራርተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ደረጀ ጉደታ በበኩላቸው ኘሮጀክቱ በክልሉ በ23 ወረዳዎች በ 581 ቀበሌዎች በ4140 የጋራ ቡድን ፍላጎት ያላቸዉ አርሶ አደሮችን አደራጅቶ ወደ ስራ ያስገባ መሆኑን ጠቅሰዋል። በአሁኑ ወቅትም 1330 ከ CIG ወደ ህብረት ስራ ማህበራት ያደጉ መሆናቸውን የገለጹት ዶ/ር ደረጀ በክልሉ ከ70ሺህ በላይ አርሶአደሮች የኘሮጀክቱ ተጠቃሚዎች መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።