አቶ ገረመው ጸጋዬ በሐዋሳ ዙርያ ቴሶ ቀበሌ ምስራቅ ክፍለ ከተማ ነዋሪ እና የ10 ቤተሰብ አባላት አስተዳዳሪ ናቸው:: እርሳቸው እንደሚናገሩት ከዚህ በፊት ከመንግስት ስራ ጀምሮ የልተሳተፉበት ስራ አልነበረም በተለይም ክልላቸውን በመወከል በእግር ኳስ ተጫዋችነት እና በተለያዩ ሙያ ዘርፍ ያገለገሉ ቢሆንም ባለፉት ዓመታት በብዙ ውጣ ውረድ እና ፈተናዎች ውስጥ ሕይወታቸውን እንደሳለፉ አጨውተውናል። በሕይወታቸው ውጣ ውረድ ከእንግልት መከራ በስተቀር እዚህ ግባ የሚባል  ለውጥ የለም ባይ ናቸው፡፡

አቶ ገረመው ጸገዬ ይሄ ሁሉ ጊዜ በከንቱ ጉልበታቸውን እና እውቀታቸውን በማባከናቸው ቁጭት እንደ ተሰማቸው በመጥቀስ ለሁሉም ጊዜ አለው ባይ ናቸው፡፡  በእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት (LFSDP)  እ.ኤ.አ በ2018 ጀምሮ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት መሰረት በክልሉ ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆን ከቻሉ እና ካረጋገጡ የጋራ ቡድን ፍላጎት አባላት ውስጥ አንዱ መሆናቸውን አጫውተውናል፡፡ እንዲሁም የእንስሳት ልማት ዘርፍ እንዲበለፅግ እና ይህንን ኘሮጀክት ቀርፀው ለኢትዮጵያ እንዲመጣ የበኩላቸውን ሚና ለተጨዋቱ የዘርፉ ምሁራን፣ ተዋናዮች እና ለባለ ድርሻ አካላት ምስገናቻውን አቅርበዋል፡፡

 

 

 

 

 

አቶ ገረመው ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በሐዋሰ ዙርያ ወረዳ በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ከተደራጁት ውስጥ እሳቸውም እንደ ¹ደኞቻቸው በወተት ልማት ላይ ከተደረጁት 10 አባላት ውስጥ አንዱ ሲሆን የማህበሩ አባላት የመተዳደርያ ሐሳብን በጸጋ የተቀበሉ እና ወደ ስራ የገቡ ናቸው አባላቱም የባንክ ቁጠባ በመክፋት በየወሩ ከ500 ብር ጀምሮ እና በየሁለት ሳምንት እስከ 10000 ብር ድረሰ በመቆጠብ ያላቸውን የአገር በቀል ዝርያ ላሞች በማዳቀል ወደ ተሻሻሉ ዝርያ በመቀየር ከራሳቻው እና ከአካባቢያቻው ላሞች ወተትን  በማሰባሰብ ከምግብ ፍጆታቸው የተረፈውን በቀን እስከ 20 ሊትር ድረስ ለማህበራት እንደሚያቀርቡ እና  ከእያንደንዱ አባላት በቀን በአማካኝ ከ10 እስከ 200 ሊትር ወተት እንደሚሰበስቡ የአንዱን ሊትር ወተት በ60 ብር እየሸጡ በ15 ቀን ውስጥ ከ25000  በወር እስከ 50000 ኢትዮጰያ ብር ከወተት ሽያጭ እንደሚያገኙ አጫውተውናል፡፡ አቶ ገረመው እንደሚናገሩት ማህበሩ ሲመሰረት ከአባላቱ የተሰበሰበ መነሻ ካፒታል 165 ሺህ ሲሆን ከአባላቱ የሚሰበሰበው ትኩስ ወተት በቀን እስከ 1000 ሊትር ነው፡፡ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት 1ሚሊዮን 5 መቶ 83 ሺህ ኢት ብር ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል፡፡

የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የተለየዩ ቁሳቁስ ግዥ ያደረገ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ለአብነት 225 ሲሲ የሶስት እግር ተሽከርካሪ በጃጅ ሞተር፣  1 የክሬም መናጫ፣ 50 ሊትር ወተት መያዝ የሚችል 2 ዲኘ ፍርጂ ፣ 10 ሊትር የሚይዝ የወተት መቀዝቀዣ እንዲሁም በ60 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ አራት ክፍል ቤት ገንብተው  ከተለየዩ ቁሳቁስ ድገፍ ጋር አሰረክቧል፡፡  ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ የመጀመሪያ ህብረት ስራ ማህበር ያደገው የላሜ ቦራ የወተት አምራቾች ህብራት ሥራ ማህበር በአሁን ጊዜ 70 አባለት የሉት ሲሆን ከዚህ ውስጥ 35 ሴቶች ሲሆኑ ቀሪው ወንዶች ናቸው፡፡

የላሜ ቦራ የህብረት ሥራ ማህበር አንደንድ አባላት በሰጡት አስተያየት ከዚህ በፊት ከነበራቸው አገር በቀል ዝርያ ላሞች የሚያገኙትን አነስተኛ ወተት ለገብያ ቢያቀርቡም ገንዘባቸውን በስርዓት እንደማይቆጥቡና በተበታተና ሁኔታ ጥቅም ላይ ሳይውል ሲባክንባቻው እንደ ነበረ አሁን ላይ ኘሮጀክቱ የቁጠባ ባህላቻውን ማዳበር እንዲችሉ እና ከወተት ሽየጭ የሚያገኙትን ገንዘብ በስርዓት መቆጠብ እንድችሉ ከማስተማሩ በተጨማሪም በተናጠል ስራ ላይ ከመስራት ተደረጅተው መስራት ውጤታማ እንዳደረጋቻው የራጋገጡበት መሆኑን መስክረዋል፡፡ የላሜ ቦራ የወተት አምራቾች የህብራት ስራ ማህበር በአሁን ጊዜ የአካባቢ ህብረተሰብን ወተት ፍላጎትን ከሟሟላት ባሻገር በአሁን ጊዜ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ከወተት ሽያጭ በባንክ ተቀማጭ ማኖራቻውን አረጋግጠዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!