(ኀዳር 28 ቀን 2017 ዓ.ም.አዲስ አበባ:እንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት (LFSDP): ባለፉት ስድስት ዓመታት የተተገበረው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ገቢያቸውን እንዳሳደገላቸው የሲዳማ ክልል ሀዋሳ ዙርያ ወረዳ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች ገልጸዋል።
በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሀዋሳ ዙርያ ወረዳ የቡርቂቶ የወተት መሰብሰቢያ እና ማምራቻ መሰረታዊ የህብረት ሥራ ማህበራት ተወካይ ወ/ሮ አዳናች አታሮ እንደነገሩን የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት (LFSDP) የበርካታ አርሶ አደሮችን ሕይወት እየቀየረ ነው። ወ/ሮ አዳናች በሐዋሳ ከተማ የቱላ 01 ቀበሌ ነዋሪ ባለትዳር እና የ3 ልጆች እናት ናቸው ፡፡ እርሳቸው በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ከመደራጀታቻው በፊት ለ15 ዓመት በማስተማር በርካታ ዜጎችን አፍርተዋል። ፕሮጀክቱ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ መተግበር ሲጀምር ደግሞ ከሌሎች የቀበሌው ነዋሪዎች ጋር በተመሳሳይ ፍላጎት በመደራጀት በወተት ላሞች እርባታ ላይ ተሠማርተው ይገኛሉ።
በእነዚህ 5 ዓመታት ውስጥ ውስጥ የዕለት ጉርሳቸውን ከመሸፈን አልፈው የተሻለ ገቢ ማፍራት እያስቻላለቸው መሆኑን በኩራት ይናገራሉ። እርሳቸው ለዚህ ውጤት የበቁት ፕሮጀክቱ የፈጠረላቸውን ዕድል በመጠቀም እና ጊዚያቸውን ሳያባክኑ በፕሮግራም በመንቀሳቀሳቸው ነው። በ2012 ዓ.ም. የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት በሲአይጂ በጋራ ቡድን ፍላጎት መደረጀተቻው ትክክለኛ ውሳኔ እና ወቅቱን ያገናዘበ እንደነበር ወደ ኋላ በማስታወስ ይናገራሉ።
አሁን ላይ የእርሳቸው እና ቤተሰቦቻቸው ሕይወት በእንስሳት እና ዓሣ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ እየተለወጠ ነው። ያኑሮ ዘይቤያቸውም የተሳካ እና ውጤታማ ሆኗል፡፡ ወ/ሮ አዳነች እንደሚናገሩት እያንደንዱ በጋራ ፍላጎት የተደራጁ አባላት እንደየ አቅማቸው የአገር በቀል ላሞች እና ዝርያቸው የተሻሻሉ ከ3-5 ላሞች አሏቸው። የወረዳው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ በሚያደርግላቸው ድጋፍ እና ክትትል መሠረት የነበራቸውን የአገር በቀል ላሞችን በ(AI) በማዳቃል ወደ ተሻሻሉ ዝርያ በመቀየር በየቀኑ ከዕለት ጉርሳቸው የተረፈውን በቀን እስከ 7 ሌትር ለቡርቂቶ የወተት ማሰባሰቢያ መሰረታዊ ህብራት ሥራ ማህበር ያቀርባሉ። አባላቱ በቀን በአማካይ ከ25-30 ሊትር የሚያቀርቡ ሲሆን በወር እስከ 210 ሊትር እንደሚያቀርቡ እና አንድ ሊትር እስከ 30 ብር በመሸጥ በወር 6300 ብር የተጣራ ትርፍ እያገኙ መሆኑን የማኀበሩ ተወካይ ወ/ሮ አዳነች አታሮ ገልጸዋል። አባላቱ በአሁን ጊዜ የዕለት ኑሮአቸው እተሻሻለ በመምጣቱ የወር ወጪያቸውን፣ የዕድር፣ የዕቁብ ጨምሮ እንደሁም የማኀበራዊ ኑሯቸውን በተሳካ ሁኔታ በመምራት በወር እስከ 6000 ብር ቁጠባ ባንክ እያስቀመጡ ነው። በአሁኑ ጊዜ በአጠቃላይ የማህበሩ አባላት ከ4.7 ሚሊዮን ብር ካፒታል ማስመዝገብ ችለዋል
በተመሳሳይ በዚሁ በሐዋሳ ወረዳ የቴሶ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት የላሜ ቦራ አባለት እና ለ40 ዓመታት የመንግሥት ሥራ በኋላ በጡረታ ላይ የሚገኙ የአራት ቤተሰብ አስተዳደር የሆኑት አቶ ታፈሰ ጉራቻ ከ2013 ዓ.ም. ጀምሮ ከተደራጁት ተመሳሳይ ዓላማ እና በዝቅተኛ ገቢ ከተደረጁ ውስጥ 70 አባለት ውስጥ አንዱ ሲሆኑ እሳቸውም እንደሌሎች ባልደረቦቻቸው የተለያዩ ሥልጠና እና ምክር በማግኘት ወደ ሥራ በመግባት ያላቸውን የአገር በቀል ላሞች በሰው ሰራሽ የማደቃል ዘዴ በመጠቀም በአሁን ጊዜ 3 የወተት ላሞች 2 ጊደሮች እና ሁለት ጥጆች የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው በማርባት ከሚታለቡት ሁለት ላሞች በቀን ከሚያገኙት 20 ሊትር ወተት 10 ሌትር ለማህበሩ 5 ሊትር ለአካባቢ ህብረተሰብ 5 ሊትር ለቤት ውስጥ ፍጆታ እየተጠቀሙ በወር ለማህበሩ 150 ሊትር ወተት 1 ሊትር በ60 ብር እየሸጡ በወር 9000 ኢት ብር ያገኛሉ
የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት (LFSDP) የቁጠባን ምንነት በተግባር የተረዱት ቁጠባን የጀመሩት በላሜ ቦራ የወተት አምራቾች የህብረት ስራ ዩኒን በእንስሳት ዓሳ ዘርፍ ልማት ከተደረጁ በኋላ ዛሬ ላይ ከሚሸጡት ወተት ከ15ሺህ ብር በላይ በባንክ መቆጠብ ጀምረዋል ። የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በእርግጥ ሕይወታቸውን የቀየረው የወ/ሮ አዳነች እና አቶ ታፈሰን ብቻ አይደለም። ይህ ፕሮጀክት ከተጀመረ ጀምሮ ባለፉት ስድስት ዓመታት በሰባት ክልሎች ውስጥ የሚገኙ በርካታ ሚሊዮን አርሶ አደሮችን የዕለት ጉርስ ከማሻሻልም ባለፈ የቁጠባ በዓላቸውን በማሳደግ የተደራጀ ማኀበራዊ ሕይወት እንዲመሩ አስችሏቸዋል። የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ከዚህም በተጨማሪ እንደ አገር በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ይፋ የተደረገውን የሌማት ቱሩፋት በማሳካት ረገድም ጉልህ ሚና በመጫወት ላይ ይገኛል።