በአሁን ጊዜ 5500 የ8 ቀን ጫጩቶችን ከኢትዮ-ችክን አስገብተው በዘመናዊ የዶሮ እርባታ መንደር ማዕከል ውስጥ ይገኛሉ፡፡ እስከ አሁን ድረስ 49 ሺህ በላይ  የሚሆኑ ጫጩቶች አስገብተው ከ45 ቀን በኃላ  ለአካባቢ ዶሮ አርቢ አርሶ አደሮች እና ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍል በግዥ መልክ አሰረጭተዋል ፡

የ30 ዓመት ወጣት እና ከሐዋሰ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋ እና ስነ ጹሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪውን 2013 ዓ.ም  ያጠናቀቀው ወጣት እያሱ ከዪሳ በዶሬ ባፈና 01 ቀበሌ ነዋሪ ነው፡፡ ወጣቱ ትምህርቱን እንደ ጨረሰ ብዙም የመንግስት ስራ ፍለጋ ላይ ጊዜውን አላባከነም ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ብዛታቸው 30 የሚሆኑ እንደ እሱ በተለየዩ ሙያ ዘርፍ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ 30 የሚሆኑ ወጣቶች ውስጥ 25 ወንድ እና 5 ሴቶች በኬሚስትሪ፣ በባዮሎጂ፣ በእንስሳት ሳይንስ ፣ በኢኮኖሚክስ ፣ በአካውንቲንግ፣ በቋንቋ እና ስና ጹሑፍ ከተለየዩ ዩንቨርሲቲ ያመጀማሪያ  ድግር  ምሩቋን ናቸው።

እነዚህ ወጣቶች ከቤተሰብ ጥገኝናት ለመላቀቅ እና ድህነትን ለማሸነፍ ከተዋያዩበት በኃለ በጋራ ፍላጎት ከ2014 ጀምሮ ተደረጅ~ው  በሥጋ  ዶሮ እርባታ እና የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ  እንድሁም በዘመናዊ የዶሮ መኖ በማቀናባበርያ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡  ለአብነት ያህል ዙርያ በሀዋሳ ወረዳ  የዶሬ በፈና ያአንድ ቀን ጫጮቶች ማሳደግያ እና በዘመናዊ የዶሮ መኖ ማቀነባበርያ ሥራ ላይ የተሰማሩት ከነዚህ  ወጣቶች መካካል አንዱ ወጣት እያሱ ከዪሳ በሰጡት አስተየያት የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት በርካታ አነስተኛ ገቢ ያላቻው  አርሶ አሮች እንዲሁም  ወጣቶች  እና ሴቶችን ህይወት መቀየሩን ይናገራል፡፡ የዶሬ በፋና ዘማናዊ የዶሮ መንዳር እና የዶሮ መኖ ማቀናባበሪያ  ለማጀመሪያ ጊዜ 6600 የአንድ ቀን ጫጮቶችን አስገብተው ከ45 ቀን በኃለ  ለአከባቢ ዶሮ አርቢ ገበሬዎች በግዥ መልክ ያቀረበ ሲሆን በአሁን ጊዜ 5500 የ8  ጫጩቶች የሚገኙ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ለ8ኛ ዙር 5500 የአንድቀን ጫቾቶችን ያስገቡ ሲሆን በዘመናዊ የዶሮ መንደር ውስጥ ከ49ሺህ በላይ የስጋ እና የእንቁለል ጣይ ዶሮዎች አስገብተው ከ45 ቀን ቦኃለ ለአካባቢ  ዶሮ አርቢዎች አሰራጭተዋል ፡፡ በአሁን ጊዜ በዘመናዊ የዶሮ እርባታ መንደር ውስጥ የሚገኙት ጫጮቶችን ጨምሮ ካፒታላቸው 700 ሽህ ብር በላይ መድረሱን ወጣት እያሱ ተናግሮዋል ፡፡

በዶሬ በፋና ዘመናዊ ዶሮ መንደር መኖ ማቀነባበርያ ውስጥ 7 የተለያዩ ዓይነት የዶሮ መኖ የሚመረት ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በቆሎ፣ ኑግ፣ ፋጉሎ፣ ፍርሽካ ፣ የተካካ የኖራ ድንገይ፣ የተፋጨ አጥንት፣ ሳይሳን የመሳሰሉትን በማምረት ለራሳቸው እየተጠቀሙ ለአከባቢው ዶሮ አርቢ ማህበረተሰብ በግዥ መልክ እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

በሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አቶ ደረጀ ስማኖ እንደ ሚናገሩት ኘሮጀክቱ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን አርሶ አዳሮች እና አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ወጣቶች እና ሴቶች በመለየት በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ወደ ስራ ከገቡት 180 የጋራ ፍላጎት ቡድን ውስጥ  በአሁን ጊዜ ሁሉም ወደ ኮፒሬትቨ ደረጀ የተሻጋገሩ ሲሆን  ከዚህ በፍት  በተናጠል እና በዘልማድ እንደሁም፣ በባህላዊ መንገድ ሲሰሩ የቆትን እና ወደ ዘመናዊነት እንዲቀይሩ በማድረግ አባላቱ በተለያዩ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ  ተደራጅተው ከመስራት በሻገር በየ¹ሮአቸው ምጥን መኖ በማምረት የነበራቸውን የአገር በቀል ላሞችን በማዳቀል ወደ ተሻሻሉ ዝርያ በመቀየር ንጹህ ወተት ለራሳቸው እና  ለአካባቢ ህብረተሰብ በማሳራጨት  ከእንስሳት ምርት እና ምርታማናት የምግብ ዋስትና እና ስርዓተ ምግብን ለማረጋገጥ የቸሉበት ደረጀ ላይ  መድረሳቻውን በሲዳማ ክልል የሐዋሳ ዙሪያ ወረዳ  የኘሮጀክት አስተባባሪ አቶ ደረጄ ስማኖ ገልጸዋል ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር በእንስሳት ዓሳ ዘርፍ ልማት ኘሮጀከት ብሔራዊ አስተባባር ዶ/ር ቶማስ ቸርነት በበኩላቸው  የኘሮጀክቱ 27 ሞዴል የዶሮ መንደር ከአስገነባቸው አምስት ክልሎች ውሰጥ ኦሮሚያ፣ አማራ ፣ ሲዳማ፣ ማዕካለዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ምዕራብ  ሲሆኑ  በአጠቃላይ በ33 ሚልዮን  ብር ወጪ በተደረገበት 27 ዘመናዊ የዶሮ መንደሮችን ግንባታውን አጠነቆው በአሁን ጊዜ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ዶ/ር ቶማስ ተናግረዋል፡፡

ይህ ሞዴል የዶሮ መንደር ዋና ዓላማው መንግስት ስራ አጥነትን ለመቀነስ ከተለየዩ ዩኒቨርሲት ትምህርታቸውን አጠነቀው ያለስራ የተቀመጡት ወጣቶችን በጋራ ፍላጎት አደረጅተው በተለያዩ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ ለማሰማራት ታሰቦ የታለመ ነው ብሏዋል፡፡ እነዚህ ወጣቶች ከቤተሰብ ጥገኝነት ተላቀው ራሰቻውን እና የአከባቢ ህብረተሰብን  መደገፍ እንዲችሉ መሆኑን በግብርና ሚኒስቴር የኘሮጀክቱ ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት  ጨምሮው አስረድተዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!