ብሔራዊ ደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች በሽታ (paste des petites ruminates-PPR) ማጥፋት ኘሮግራም አስመልክቶ በአዳማ ከተማ ለሁለት ቀናት የምክክር መድረክ ተከሂዷል ፡፡
በየዓመቱ 30 ሚሊዮን ያህል በበጎች እና ፍየሎች በሽታው ይጠቃሉ፡፡ በዓለም ላይ ከሚገኙ 70 አገራት ውስጥ 60 በመቶ የሚሆኑት የአፍርካ አገራ በበሽታው እንደሚጠቁ በመድረኩ ላይ ተገልጸል ፡፡
ደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች በሽታ በቫይረስ አማካኝነት የሚተላለፍ እና በዋነኝነት አነስተኛ አመንዠኪ እንስሳትን(small ruminant animals) የሚያጠቃ አደገኛና ድንበር ተሻጋሪ በሽታ መሆኑን ተገልጾል ፡፡
በግብር ሚኒስቴር የእንስሳት ጤና ልማት ዘርፍ አማካሪ ዶ/ር አለማየሁ መኮንን የምክክር መድረኩን ዓላማ አስመልክተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በየዓመቱ 30 ሚሊዮን እንስሳት በበሽታው ይጠቃሉ፡፡ በመሆኑም የዚህን በሽታ ስርጭት ለመግታት ከዚህ በፊት ከአጎራባች የምስራቅ አፍርካ ሀገራት ጋር የሁለትዮሽ ግንኙኙት (African regional integration) ለማጠናከር እና ወደ ላቀ ደረጀ ለማሸጋገር ጥረት ተደርጓል፡፡ በዚህም ጥረት ከሁሉም የምስራቅ አፍርካ በየነ መንግስታት IGAD ሀገራት ከኤርትራ በስተቀር ከኬንያ፤ ከጅቡት እና ከደቡብ ሱዳን ጋር የጋራ ስምምነት ላይ መድረስቻውን አማካሪው በመክፈቻ ንግግራቸው አስታውሰዋል፡፡
በመሆኑም በአለም አቀፍ የእንስሳት ጤና ድርጅት(OIE) እና በተባበሩት መንግስተት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO) በኩል እ.አ.አ በ2030 ከአለም በሽታውን ለማቆጣጠር ብሎም ለማጥፋት እየተሰራ ይገኛል፡፡ አገራችን ኢትዮጵያም ሶስት ዓመታት ቀድማ በሽታውን ለማጥፋት ብሔራዊ ስትራቴጂ አዘጋጅታ ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደምትገኝ ዶ/ር አለማየሁ ገልጾዋል፡፡ ከዚህ በፊት በሽታውን ለማጥፋት የአውሮፓ ህብረት / EU – Share/ ኘሮጄክት በአራት አርብቶ አደር ክልሎች ኦሮሚያ አርብቶ አደር አካባቢ፤ በሱማሌ፤ አፋር፤ ደቡብ ኦሞ፤ እንዲሁም አማራ ክልሎች ከ2015-2019 የትግበራ ስራዎችን አጠናቋዋል፡፡
በሽታው ተከስቶ በሚያውቅባቸው አባቢዎች በሚገኙ በጎች እና ፍየሎች ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት ወይም ሞት ከ 80-90 ፐርሰንት እንዲቀንስ አስችሏል፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የብሔራዊ ደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች በሽታ ማጥፋት ኘሮግራም መስተባበሪያ ጽ/ቤት እንደገለጸው እንደ እ.አ.አ በ2027 ኢትዮጵያ ከደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች በሽታ ነጸ ትሆናለች ተብሏል፡፡
በመሆኑም የተጀመሩትን ስራዎች ለማስቀጠል እና የብሔራዊ ደስታ መሰል የበጎችን ፍየሎች በሽታን ለማጥፋትና ኘሮግራሙን ለመደገፍ በግብርና ሚኒስቴር የሚገኘው በአለም ባንክ የሚደገፈው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት /LFSDP project/ 31 የመስክ መኪናዎችና 76 ሞቶር ሳይክሎች ለክልሎች እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባለፉት በጀት ዓመታት በተጨማሪ 46 ሚሊዮን ብር የበጀት ድጋፍ ማድረጉ እና በዘንድሮ በጀት ዓመትም 80 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ወደ ስራ እየገቡ እንደሆነ የብሔራዊ የኘሮጄክቱ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ተናግረዋል፡፡
ደስታ መሰል የበጎች እና ፍየሎች በሽታ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ መከሰቱ የተወቀው እ.አ.አ 1977 በአፋር ክልል በፍየሎች ላይ መሆኑን መረጀዎች ያመለክታሉ ፡፡