ደቡብ ክልል (27/02/2014 ) አርሶ አደሮቹ ከሀገር በቀል የእንስሳት  ዝርያ በተሻሻሉ እንስሳት ዝርያ በማደቀል በቀን በአማካኝ እስከ 25 እስከ 36 ሊትር ወተት እያገኙ መሆናቸውን አስተወቁ ፡፡

በክልሉ ከ2011ዓ.ም ጀምሮ በ13 ወረዳዎች ውስጥ በእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት (LFSDP ከታቀፉት ውስጥ አንዱ  በጉራጌ ዞን የመስቃን  ወረዳ ሲሆን ከ2012/2013 ዓ.ም  ድረስ 1ሽህ 1 መቶ 07 ወንድ 9 መቶ 53 ሴቶች በአጠቃላይ 2ሽህ 60 ተጠቃሚዎች እና 1 መቶ 86 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች በመስቃን ወረዳ የተበን ቀበሌ  ከእንስሳት ምርት እና ምርታማነት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን የወረዳው የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት አስተባባሪ ተናግረዋል፡፡

የወረዳ የእንስሳት እና ዓሣ  ዛርፍ ልማት ኘሮጄክ አስተባባር አቶ ሰምሶን ዘርይሁን እንደገለጹት ኘሮጄክቱ 2012 ዓ.ም ጀምሮ  በወረዳ ካሉት ከ30 ቀበሌዎች ውስጥ በ17 ቀበሌዎች ውስጥ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን ከ1ሽህ 1 መቶ 62 አርሶአደሮችን  ውስጥ 8 መቶ 42 ወንድ ሲሆኑ 3 መቶ 23 ሴቶች  በአበለቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት  በወተት ፤ በቀይ ስጋ ፤ በዶሮ እርባታ ፤ እንደሁም በዓሣ ግብርና አርሶአደሩ ከእንስሳት ልማት ዘርፉ የምግብ ዋስትናቸውን እየረጋገጡ መሆናቸውን የወረዳው የኘሮጄክቱ አስተባባረፍ የሆኑት አቶ ሳምሶን ዛርሁን አስተውቀዋል ፡

 

እንደርሳቸው  ማብራሪያ በወረዳው በወተት ልማት 50  የተደረጁ ቡድኖች ሲሆን ከዚህ ውስጥ 5መቶ 44 ተጠቃሚ ሲሆኑ  ከነዚህ ውስጥ 2 መቶ  53 ወንዶች  ሲሆኑ 2 መቶ 91 ሴቶች መሆናቸውን እነ   በዶሮ እርባታም ከተደረጁት 22 ቡድን ውስጥ 58 ወንድ እና 1 መቶ 85 ሴቶች በቀይ ስጋ በግ እና ፍየል ከተደረጁት  1 በመቶ 14 ቡድኖች ውስጥ 7 መቶ 96 ወንድ እና 4 መቶ 77 ሴቶች  እንዳሚገኙ የወረዳው  የኘሮጄክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሳምሶን  ጨምሮ አስረድተዋል  ፡፡

በመስቃን ወረዳ ዘነብ ቀበሌ በኘሮጄክቱ ከተቀፉት ነዋሪዎች መካከል  አንዱ  የሆኑት አቶ ሁሴን አብሸ በሰጡት አስተየያት ቀደም ባሉት ጊዜያት በአግባቡ ሳይጠቀሙ በመቆየታቻው እንደ ቆጫቸው በመግለጽ   ኘሮጄክት ወደ ወረዳቸው ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ አስር አባላት በመሆን በጋራ ፍለጎት  በመደራጃት አገር በቀል  ላሞችን  በተሻሸሉ እንስሳት ዝርያ በማዳቀል  በአሁኑ ጊዜ 7 የተሻሻሉ የውጭ ዝርያ ያላቸው ላሞችን በማርባት በቀን ከአንዲት ላም በአማካይ  ከ25 እስከ 36 ሊትር በላይ  እንደሚያገኙ እና አንድ ሊትር እስከ 40 ብር በቀን ከወተት ሽያጭ እስከ 2600 ገቢ እንደሚያገኙ አቶ ሀሰን አብሽን ተናግረዋል  ፡፡

በደቡብ ክልል የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዪ በበኩላቸው ኘሮጄክቱ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በክልላቸው በ13 ወረዳዎች  ቀበሌ179 ውስጥ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማጠናቀቅ ክፍተቶችን በመለየት አምራቹ እና ገብያን በማተሳሰር እንዲሁም የፌዴራል ብሄራዊ ኘሮግራሞችን በማጠናከር ትስስርን በመፍጠር በመንግስት የተያዙትን የማስፈጸም ስራዎችን እያከናዋነ ይገኛል ብለዋል ፡፡

ይሁንእንጂ 2012 ጃምሮ በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት በወተት ፤በዶሮ ፤በቀይ ሥጋ በዓሣ ግብርና 2ሽህ 3 መቶ 40 የጋራ ቡድን ፍለጎትን በማቋቋሚ ከዚህ ውስጥ 41. ኘርሴንቱ ሴቶች ሲሆኑ በአጠቀለይ በአሁን ጊዜ ከ29ሽህ በላይ ተጠቃሚዎች እንደሚገኙ በተጨማርም ከእንስሳት እሴት ሰንሳለት አንጸር 1ሽህ 2 መቶ 70 በቀይ ስጋ ፤6 መቶ6 በወተት ልማት 4መቶ 16 በዶሮ ልማት ፤25 በዓሣ እርባታ  የሚሰተፉት የጋራ ፍለጎት ቡድን መሆናቸው  የደቡብ ክልል የእንስሳት ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት አስተባባሪ አቶ ሙሉጌታ ተስፋዪ ጨምሮ አስረድተዋል ፡፡

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት  ብሄራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት በኩላቸው ኘሮጄክቱ በ7 ክልሎች በ1755 ቀበሌዎች 10560 የጋራ ቡድን ፍላጎት  ሚገኙ ሲሆን ኘሮጄክቱ 15 ፒካፕ መኪና እና 300 የሞቶር ሳይክል በ500 ሽህ USD በመግዛት ለ6ቱ ክልሎች ርክክብ ያደረገ ሲሆን ለወደፊቱም ኘሮጄክቱ የታለመለት ዓላማ ግብ እስኪደርስ ድረስ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ዶ/ር ቶማስ ጠቁመዋለል ፡፡

ዶክተር ቶማስ በፕሮጀክቱ አማካኝነት ለክልሎች የተሰጡ ተሽከርካሪዎች ለታሰበላቸው አላማ ብቻ እንዲውሉ አሳስበዋል ::;

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!