በምስራቅ ሸዋ ዞን የአዳማ ወረዳ የወንጅ ኩሩፍቱ ቀበሌ  የሚኖሩት  የአብድ ጉድና  የጋራ ፍላጎት የተደራጁ  አርሶ አደሮች  ከእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን የአዳማ ወረዳ የወንጅ  ኩሩፍቱ እና የጥዮ ቀበሌ በአራቱ እንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ በጋራ  ፍላጎት የተደራጁት አርሶ አደሮች ሰሞኑን ለመስክ  ምልከታ  ላደረጉት ከፌዴራል እና ከክልሉ ለተውጣጡት የኘሮጀክት  ባለሙያዎች በሰጡት  አስተያየት  እንደተናገሩት ከዚህ በፊት ስራ አጥ እና ከእጅ ወደ አፍ  ወይም ለእለት ጉርስ ይሁን እንጅ በዘለቂነት  መተዳደሪያ  የሌላቸው  ሲሆን  በአሁን ጊዜ  ኘሮጄክቱ ወደ ወረዳቸው ከመጣባት ጊዜ ጀምሮ በጋራ ፍላጎት ተደራጅተው አርሶ አደሮች በአሁን ጊዜ ከኘሮጄክቱ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ለአብነት የወንጅ ኩሩፍቱ  ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት እና ከዚህ በፊት በሀገር በቀሌ የእንስሳት እርባታ ሲተዳደሩ የነበሩ እና ኑሯቸውም ከእጅ ወደ አፍ ይኖሩ  ከነበሩት በጋራ ፍላጎት በእንስሳት ልማት  ዘርፍ ላይ  ከተደራጁት መካከል  ወ/ሮ መሪማ ከድር በሰጡት አስተያየት ከዚህ በፊት የሀገር በቀል የእንስሳት ዝርያን ለበርካታ ዓመታት ሲጠቀሙ እንደቆዩ እና  ከእንስሳቱም የሚገኘው የወተት  ምርት ውጤት አልባ  እንደ ነበረ እና ከአንዲት የአገር በቀል ዝርያ ያላቸው ላሞች በቀን ከ 1 ሊትር እና  እና ግማሽ ሊትር ያልበለጠ ሲሆን  ከትርፉ ጉዳቱ እንደሚያመዝን ለማረጋገጥ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡

ይሁን እንጅ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ዘርፍ ኘሮጀክት በዘርፉ ላይ የሚታዩትን ማነቆዎችን በመለየት ወደ ወረዳቸው ከመጣበት ቀን ጀምሮ ኘሮጄክቱ ባደረገላቸው ድጋፍ መሠረት በወተት ልማት ዘርፍ  ላይ ለመሳተፍ  የጋራ ፍላጎት ያላቸው አስር አባለት በማደራጀት  የተለያዩ ድጋፍ በማግኘት  የግንዛቤ የአቅም ግንባታ፤  የክህሎት ክፍተት በመለየት ፤ በማሰልጠን  ወደ ስራ በመግባት  የነበራቸውን  የአገር በቀል ዝርያ ላሞችን በተሻሻሉ ዝርያ  በማዳቀልና  በማሻሻል በአሁን ጊዜ ከአንድ ላም  በቀን  በአማካይ እስከ 32 ሊትር የወተት  ምርት እያገኙ ሲሆን  በቀን እስከ 45 ሊትር ወተት ለሽያጭ   ለአካባቢ ገበያ እንደሚያቀርብ እና አንድ ሊትር ወተት እስከ 27 ኢት. ብር ለአካባቢ ገበያ ለሽያጭ እንደሚያቀርቡ ወ/ሮ  መሪማ ከድር  ከሰጡት አስተያያት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በዚሁ ወረዳ በእንስሳት ልማት ዘርፍ  ላይ ከተደራጁት የ8 ቤተሰብ አባላት የሆኑት ወ/ሮ ንግስት ባልደ እንደተናገሩት  ቀደም ሲል የነበራቸውን የአገር በቀል እንስሳቶችን በቀን አንድ ሊትር  ከአንድ ላም እንደሚገኝ ጠቅሰው ከውጤቱ ይልቅ ድካም እንደሚበዛ ለበርካታ ዓመታት ለችግር ሲዳረጉ እንደ ነበረ ፕሮጀክቱ ወደ አዳማ ወረዳ ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ  ከወረዳ ባገኙት የተለያዩ  ድጋፍ ከ2012 ጀምሮ በጋራ ፍላጎት ተደራጅተው በፊት የነበራቸውን እንስሳት  በማደቀል ዝርያን  በማሻሻል በአሁን ጊዜ ከአንድ ላም  በቀን በአማካይ  ከ30 – 40 ሊትር ወተት ማግኘት የቻሉበት ጊዜ ላይ መድረሳቸው  እና አንድ ሊትር  27 ኢት – ብር ለአዳማ ከተማ ህብረተሰብ እንደሚያቀርቡ  በወረዳው በኘሮጄክቱ የታቀፉት  የጋራ ፍላጎት  ያላቸው አርሶ አደሮች  የወተት እና የወተት ተዋፅኦ  እጥረትን ለመቅረፍ አባላቱ የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ  ይገኛል ተብሏል፡፡

 

በተመሳሳይ  በዚሁ ወረዳ በጥዮ ቀበሌ ቀደም ሲል  ስራ አጥ ወጣቶች የነበሩ እና በ2012 አስር አባላት ሆኖ በጋራ ፍላጎት በዶሮ እርባታ ላይ  ከተደራጁት መካከል ወ/ት አበዙ አበበ እንደ ገለጹት ከዚህ በፊት ምንም ያልነበራቸው እና ሥራ አጥ እንደነበሩ ለተለያዩ ችግሮች ሲጋለጡ እንደ ነበሩ እና የእለት ጉርስ ለማግኘት በርካታ ውጣ  ውረዶች ሲያጋጥማቸው እንደ ነበሩ ያስታውሳሉ፡፡

 

ይሁን እንጂ በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት  በወረዳቸው  ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ ተመሳሳይ የጋራ ፍላጎት ያላቸው ሥራ አጥ ወጣቶች አስር አባላት በጋራ ተደራጅተው በአሁን ጊዜ  ለሶስተኛ 200 የእንቁለል ዶሮዎችን በማርባት ላይ ይገኛሉ ፡፡

በአሁን ጊዜ በቀን ከ95 እስከ 200 እንቁላል የሚያገኙ ሲሆን በየ 3 ቀን  ልዩነት ከስምንት እስከ 800 እንቁላል  ለአካባቢ ገበያ እንደሚያቀርቡ አንድ እንቁላል 6 ኢት  ብር  እንደሚሸጡ በአሁን ጊዜ አባላቱ ከ50 ሽህ ብር በላይ በባንክ እንዳላቸው ከአባላቱ   ተወካይ ከሰጡት አስተያየት ለማወቅ ተችሏል፡፡

በምስራቅ ሸዋ ዞን የአዳማ ወረዳ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ አቡ አሹ  በበኩላቸው የአዳማ ወረዳ ከአዲስ ኣባባ 99 ኪሎ ሜትር በስተምስራቅ ኢትዮጵያ እና በሀረር እና በጅቡቲ በስማር በስምጥ ሸለቆ የምትገኝ ወረዳ ስትሆን  ከ 1400-2300 ከፍታ ላይ የምትገኝ ዓመታዊ የዝናብ መጠኑም 600- 1150 ይደርሳል ያሉት የወረዳው  አስተባባሪ  ከኘሮጄክቱ ከ2012 ዓ.ም በርከታ ስራዎችን ያከናወነ ሲሆን በተለይም  በዶሮ እርባታ፤ ወተት ልማት፤ በዓሣ ግብርና ላይ ከፍተኛ እምርታዊ ለውጦች በወረዳው እየታየ መምጣቱ በተለይም በሶስት እንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ ከ 2 ሽህ 4 መቶ 58  ከእጅ ወደ አፍ የሚኖሩት ገበሬዎች ፤ ሴቶች እና ወጣቶችን  ከኘሮጄክቱ ተጠቃሚ መሆን መቻላቸው የአዳማ ወረዳ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጄክት አስተባባሪ አቶ አቡ አሹ  ጨምሮ አስረድተዋል ፡፡ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በግብርና ቢሮ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ደረጄ ጉደታ በበኩላቸው ኘሮጄክቱ በክልሉ ከ2012 ጀምሮ በ18 ዞን በ23 ወረዳዎች በአራቱ እንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን በእንስሳት እርባታ ፤ በዶሮ እርባታ ፤ በቀይ ስጋ ፤እና በዓሣ ግብርና ላይ በኘሮጄክቱ ወረዳዎች ውስጥ እምርታዊ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን ዶ/ር ደረጄ ጦቅሰው  በ2012/13 ዓ.ም ከ4140  ሲአይጂ /የጋራ ፍለጎት/  ያላቸው ሲሆን  በአሁን ጊዜ ከ60 ሽህ  የክልሉ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን 36 ፐርሰንት ሴቶችን እና 20 ፐርሰንት ወጣቶች  መሆናቸው እና 300 ወደ ኮፕሬቲቭ ማደጋቸው የኦሮሚያ ክልል የፕሮጄክቱ አስተባባሪ ደረጄ ጉዳታ ጨምሮ አስረድተዋል፡፡ በተለይ በአሁን ጊዜ አርሶ አደሩ ከእንስሳት ምርት እና  የምግብ ዋስትናቸውን ምርታማነትን በማረጋገጥ  እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን አንዱ የኘሮጄክቱ ግብዓት ማሳያ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል ነው ያሉት ዶ/ር ደረጄ ጉዳታ

ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ወረዳ ፤ ሐረርጌ ጡሎ ወረዳ ፤ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን የተለያዩ  ወረዳ እንዲሁም  በአርሲ ሮቤ ወረዳዎች  ከፌዴራል ኘሮጄክት ባለሙያዎች እና ክልሎች ጋር የተደረገ የመስክ ምልከታ  በሁሉም ወረዳዎች  በኦሮሚያ ክልል እንደ  በጋ መስኖ  ስንዴ አርሶ አደሩ በተሻሻሉ እንስሳት ዝርያ ላይ ትኩረት አድርጎ ከተሰራ በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ላይ እየታየ ያለው ምርጥ ተሞክሮዎች ከክልሉ አልፎ ለሌሎች  ለአደጉት አገሮች ምሳሌ ሊሆን እንደሚችል ማሳያ መሆኑን  ለማወቅ ተችሏል፡፡

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!