በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ከሚያከናውናቸው ከ4ቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ውስጥ ባለፉት 3 ዓመታት ውስጥ ከወተት ምርት 2.2 ሚሊዮን ትርፍ ማግኘተቻው ተገለጸ፡፡
በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ብሔረዊ አስተባባር የሆኑት ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል አዘጋጅነት በአዳማ ከተማ በተካሄደው ዘመናዊ የዳታ ቤዝ ስልጠና ላይ እንደ ተናገሩት በአውሮፓውያኑ ዘመን 2018 በኦሮሚያ፣ በደቡብ ፣ በአማራ ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ፣ጋምቤላ እና ትግራይ ኘሮጄክቱ ስራ ማስጀመሩን አስታውሰዋል።
አሁን ላይ በፕሮጀክቱ 10450 የጋራ ፍላጎት ያላቸው(CIG) ተደራጅተው ስራ የጀመሩ መሆናቸውን እና ከነዚህ ውስጥ 10333 ወደ ተግባር ገብተዋል ነው ያሉት ።
ይሁን እንጅ አሁን ላይ 8450 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ቡድኖች ምርታቸውን ወደ ገበያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ የኘሮጀክቱ አስተባባሪ ቶማስ ቸርነት (ዶ/ር) ገልጸዋል። በተለይም በኘሮጀክቱ በአራቱ እንስሳት እሴት ሰንሰለት በወተት፣ በቀይ ሥጋ፣ በዶሮ እርባታና በዓሣ ግብርና ከሚሰራቸው ውስጥ እስከ አሁን ባለው ጊዜ 2.2 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ገቢ ከተገኘው ውስጥ የአምበሳውን ድርሻ የያዘው የወተት ልማት ዘርፉ መሆኑን ዶ/ር ቶማስ ጠቅሰዋል ፡፡ ለአብነት በደቡብ ክልል በከማባታ ጣምበሮ ዞን ቀዲዳ ጋሜላ ወረዳ እና በኦሮሚያ ክልል በምስረቅ ሸዋ ዞን የወንጂ ኩሪፍቱ የወተት አምራች ሴቶችን ለመጥቀስ ተችሏዋል ፡፡
በኦሮሚያ ግብርና ቢሮ የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባተር ዶ/ር ዳረጀ ጉደታ በበኩላቸው ኘሮጀክቱ በክልሉ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በ18 ዞን በ23 ወረዳዎች በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ሲሆን በእንስሳት እርባታ፣ በዶሮ እርባታ፣ በቀይ ስጋ እና በዓሣ ግብርና ላይ በ18 ዞኖች እና በ23 ወረዳዎች ውስጥ እምርታዊ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን ዶ/ር ደረጀ ጠቅሰው በ2012/13 ዓ.ም ጀምሮ ከ 4140 ሲአይጂ /የጋራ ፍላጎት ቡድን/ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ በአሁን ጊዜ ከ6000 በላይ የክልሉ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆናቸው እና ከነዚህ ውስጥ 36 ኘርሰንቱ ሴቶችን እና ቀሪው 20 ኘርሰንት ወጣቶች መሆናቸው እና በአጠቀላይ በአሁን ጊዜ 300 የሚሆኑት ወደ ኮፖሬቲቭ ማደጋቸውን የኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ ደረጀ ጉዳታ ጨምረው አስረድተዋል ፡፡
በተለይ በአሁን ጊዜ አርሶ አደሩ ከእንስሳት ምርት እና ምርታማናት የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ እንዲችሉ እና የቴክኖሎጂ ሽግግርን ተጠቃሚ መሆን መቻላቸውን አንዱ የኘሮጀክቱ ግብዓት ማሳያ መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል ነው ያሉት ዶ/ር ደረጀ ጉዳታ ፡፡
ለዚህም ሰሞኑን የክልሉ ባለሙያዎችን ጨምሮ ከ18 ዞኖች እና ከ 23 የኘሮጀክት ወረዳ ለተወጡ ከ90 በላይ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ውጤት ተኮር የዳታ ቤዝ አሰባሰብ እና ትንተና ይዘት ከዚህ በፊት የነበሩ ችግሮችን ይቀርፋል ተብሎ ይታመናል ተብሏል፡፡
ከጅማ ዞን ቀርሰ ወረዳ የመጡት ወ/ሮ አለምነሽ ሹጉጤ በዞናቸው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት የኘሮጀክቱን እንቅስቃሴ አስመልክተው በሰጡት አስተየያት ኘሮጀክቱ በክልላቸው ስራ ከጀማረበት ጊዜ ጀምሮ በአካባባው ህብራተሰብ ከፍተኛ እምርታዊ ለውጦችን አስማዝቧል ለአብነትም ያህል አርሶ አደሮቹ የዕለት ገቢውያቸውን ለማሸሻል ችለዋል፤ ለወጣቶች የሥራ ዕድል ተፋጥሯል ፤በተለይም ሴቶች ወጣቶች ተደረጅተው ወደ ሥራ ከገቡበት ጊዜ ጀምሮ የዕለት ገቢያቸውን ለማሻሻል ተችሏል ፤ እንደሁም በዓልን ጠብቆው ሥጋ እና እንቁለል የሚመገቡት አርሶአደሮቹ በአሁን ጊዜ ሥርዓታ ምግባቸውን ለማሻሻል ተችሏል፤ በአጠቃላይ በወረዳ ውስጥ የሚገኙት አካል ጉዳተኞች በሦስት ሲአይጂ ተደረጅተው በአሁን ጊዜ ከልመና ተላቀው በምግብ ሰብል ራሳቸውን እየቻሉ መሆናቸውን ከጅማ ዞን ቀርሳ ወረዳ የመጡት ወ/ሮ አለምነሽ ሽጉጤ ተናግረዋል ፡፡
ከሌሎች ኦሮሚያ ዞኖች ከምስራቅ ሐረርጌ፣ ከምዕራብ ሐረርጌ ፣ ከምስራቅ ሸዋ ዞን እና ከአርሲ ሮቤ ዲንሾ ወረዳ የመጡት የኘሮጀክቱ አስተባባሪዎች በበኩላቸው ኘሮጀክቱ የአካባቢውን ማህበረሰብ ህይዋት በመቀየር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተየ ያለው እምርታዊ ለውጥ አበራታች ከመሆኑም በተጨማሪም ከእንስሳት ምርት የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ መቻላቸውን የኘሮጀክት አስተባባሪዎች ከሰጡት አስተያየት ለማዋቅ ተችሏል፡፡