ከመጋቢት 6-8/2015 ዓ.ም. በአዳማ ከተማ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲካሄድ የቆየው የ2015 የ6ወር የፕሮጀክቱ አጠቃላይ ግምገማ ተካሂዷል፡፡
እንደ አ.እ.እ አቆጣጠር በ2018 በ6 ክልሎች በኦሮሚያ ፣ በአማራ ፣በደቡብ ብ/ብ /ሕ/ክ ፣ ቤንሻንጉል ፣ ጋምቤላ እና በትግራይ ክልሎች በ58 ወረዳዎች በ1755 ቀበሌዎች ላይ በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት በወተት ፣ በዶሮ ፣ በቀይ ስጋ እና በዓሣ ላይ ስራው የጀመረ ሲሆን ከ10ሺህ 450 የጋራ ፍላጎት ያላቸው ሲኤጂዎችን አደራጅተው ስራ የጀመረ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 10ሺህ 333 ወደ ተግባር በመግባታቸውና በአሁን ጊዜ 8450 በላይ ምርታቸውን ወደ ገቢያ በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ የኘሮጄክቱ ብሔራዊ አስተባባር ዶ/ር ቶማስ ቸርነት ተነግሮዋል ፡፡
በተለይም ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም ኘሮጄክት ወረዳዎች ከ10ሽህ በላይ የጋራ ፍለጎት ያላቸው ስራ አጥ ወጣቶች እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ያለቸው አርሶአደሮች በማደረጀት በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት እንድሰማሩ በማድረግ 120ሺህ በላይ ዜጎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ እየደረገ እንደሚገኝ ተጠቅሶል፡፡በአጠቃላይ የኘሮጄክቱ አስተባባርዎች የየክልላቸውን የ6ወር ሪፖርት በማቅረብ በጠንካራ እና ባጋጠማቸው ችግሮች ዙርያ እንዲሁም በቀጣይ እቅድ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት በማካሄድ በቀሪው ጊዜ አርሶአደሮቹ ከእንስሳት ምርት እና ምርታማነት የበለጠ ተጠቃሚ ለማደረግ እና ከእንስሳት ልማት ዘርፉ የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ እንዲችሉ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ከሰጡት አስተየያት ለማወቅ ተችዋሏል ፡፡
በተለይም በአሁን ጊዜ በዘርፉ ላይ የሚስተዋሉማነቆዎችን በመለየት በእንስሳት ጤና፣ዝርያን ማሻሻል ፣የእንስሳት ልማት ፣ የገቢያ ትስስር መፍጠር ላይ ኘሮጄክቱ የጀመረውን ድገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጦ ተለየይተዋል ።
+6
All reactions:
Melkamu Alemu, Awol Ibrahim and 2 others