በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ልማት ፕሮጀክት የ2015 በጀት አመት 7ኛ ስትሪንግ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን በሃዋሳ ከተማ ጀምሯል፡፡ የስብሰባውም ዋና አጀንዳ የ2015 በጀት ዓመት አፈፃጸም እና የ2016 በጀት አመትን ገምግሞ ማፅደቅ ሲሆን የስትሪንግ ኮሚቴ አባላቶቹም ከፌደራል እንዲሁም ከክልል የሚመለከታቸው አባላት በስብሰባው ላይ ተካፍለዋል ፡፡በመጨረሻም ውይይቱ ከተካሄደ በኋላ የ2016 በጀት አመት አመታው እቅድን በመገምገም እንዲሁም ሃሳቦችን በማንሸራሸር በጀቱን ባልተለያየ ድምፅ አፅድቀዋል፡፡ የክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊዎችም በሲዳማ ክልል በተለየዩ ወረዳዎች የፕሮጀክቱን ትግበራት በነገው ዕለት ተዘዋውረዉ ይጎበኛሉ፡፡