በሀገር ዓቀፍ ደረጃ የወተት  ከብቶች ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና በሚጫወተው   የባዮቴክኖሎጂ አተገባበር መመሪያ ላይ  ውይይት ተካሄደ።

( Octo /10/2023 እንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ) በግብርና ሚኒስቴር እንስሳት እና  ዓሣ  ዘርፍ ልማት ድጋፍ  በአገር አቀፍ ደረጃ በወተት ከብቶች የሥነ- ተዋልዶ ባዮቴክኖሎጂ ዘዴዎች አተገባበር መመሪያ ላይ በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ  ከ21/ እስከ 22/01//2016 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የጋራ ውይይት መድረክ  ተጠናቀቀ፡፡

የባዮቴክኖሎጂ ዘዴዎች አተገባበር መመሪያ የተዘጋጀው ሰነድ ከዚህ በፊት በእንስሳት ልማት ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ በዝርያ ማሻሻል ፣በመኖ ልማት፣በእንስሳት ጤና እና  የአዳቀይ ቴክንኒሸያን  ችግሮችን  ለመቅረፍ ይረዳል ተብሏል።

 

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ከሁለት ዞን አራት ወረዳ ፣ከደቡብ ኢትዮጵያ አንድ ዞን 2 ወረዳ እንዲሁም ከማዕካላዊ ኢትዮጵያ ክልል አንድ  ዞን እና ሁለት  ወረዳዎች የተውጣጡ የወተት እርባታ ፣የእንስሳት ጤና  ባለሙያ፣ የአዳቃይ ቴክኒሸያን ፣ የመኖ ልማት ባለሙያዎች በአጠቃላይ 80 የሚሆኑት ተሳታፊዎች በሰነዱ ላይ ውይይት  ማድረጋቸውን  በሚኒስቴሩ  የወተት ሀብት ልማት ዴስክ ሀላፊ    አቶ ለማ ገመዳ ገልፀዋል።

የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ  ዘርፍ ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ አማካሪ አቶ ግርማ ሙሉጌታ  በበኩላቸው  በአሁኑ ጊዜ የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻል እንደ መንግስት ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ  ነው ብለዋል።

በሌማት ትሩፋት ኘሮግራም የወተት መንደር በመመስረትና ለትግበራውም አመቺ ሁኔታዎችን በመፍጠር የዝርያ ማሻሻያ ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ የሰው ሰራሽ ማዳቀል አገልግሎት በስፋት እተሰራበት ነው ብለዋል። በወተት መንደር የታቀፉ አርቢዎችን በማሰልጠንና አዳቃይ ቴክኒሺያኖችን ክሎት እንዲያዳብሩ እየተደረገ እንደሚገኝም አንስተዋል ::

 

በግብርና ሚኒስቴር በእንስሳት እና ዓሣ   ዘርፍ ልማት  መሪ ስራ አስፋጻሚ  ወ/ሮ  ፅጌረዳ   ፍቃዱ  የወተት ከብቶች የሥነ ተዋልዶ ባዮ-ቴክኖሎጂ በዋናነት የሚያተኩረው በሰው ሰራሽን የማዳቀል የኮርማ ፍለጎት ማመሳሰል የፅንስ ሽግግር ቴክኖሎጂ የእርግዝና ምርምር ተያያዥ ሂደቶች ላይ  መሆኑን ጠቅሶዋል ።

ዝርያን በማሻሻል ተላላፊ በሽታዎችን ለመቀነስ የወተት ምርት እና ምርታማነትን ለማሰደግ የሚረደ መሆኑንም መሪ ስራ አስፈጻሚዋ አስረድተዋል ፡፡

በውይይቱ ላይ የተሳተፉ  የዘርፉ ምሁራን እና  ከ3ቱ ክልሎች ከተለያዩ  ዞኖች የመጡት ባለሙያዎች መንግስት ለእንስሳት ልማት ዘርፉ ትኩረት መስጠት እንዳለበት አንስተዋል ።

 

አርሶ አደሮቹ  ከባህላዊ የአረባብ ዘዴ ተላቀው በዘመናዊ የአረባብ ዘዴ እንዲከተሉ  ማድረግ እና   ከእንስሳቱ ምርት እና ምርታማነት  የበለጠ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል ይገባል ነው ያሉት።

ከማዕካለዊ ኢትዮጵያ ክልል ከምባታ ዞን የመጡት አቶ አወቀ ታገሰ በሰጡት አስተየያት የእንስሳት ዝርያን ማሻሻል  ከመኖ ልማት ስራ ጋር በዞናቸው በቁርኝት እየተሰራ  እንደሚገኝ  ገልፀዋል።

በዞኑ ካሉት 119 ቀበሌዎች የእንስሳት ኤክስቴንሽን ተጠቃሚ  ውስጥ 82 በመቶ  የተሻሻሉ ዝርያ ከተሻሻሉ መኖ ልማት ጋር ጎን ለጎን  እያተሰረ መሆኑን  ጠቁመዋል።

በዚህ ሥራም  ከፍተኛ የወተት ምርት እንደሚገኝ  ከአንድት ለም በቀን 39 ሊትር በዓመት በአጠቀለይ 152 ሽህ 7መቶ ሊትር በላይ ከዞኑ ከተሻሻሉ  የወተት ላሞች   እንደ ሚሰበሰብ  ተናግረዋል።

የሆለታ ግብርና ምርምር ተመራማሪ   ዶ/ር ዲርባ ሁንዴ በበኩላቸው የወተት ከብቶች ዝርያ ማሻሻያ የስነ -ተዋልዶ ቴክኖሎጂ ያለው አስተዋጾ እነ የእርግዝና ምርመራ በሚል ባቀረቡት ጽሑፍ  የስነ- ተወልዶ ቴክኖሎጂን የወተት ከብቶች ዝርያን  ማሻሻያ ላይ የጎላ ሚና እንደሚኖረው በመገንዘብ  በበቂ ሁኔታ ስራ ላይ በማዋል እና የባለሞያዎችንን  እና የተጠቃሚዎችን እውቀት እና ክህሎት  ማሳደግ ላይ ትኩረት መሰጠት እንዳለበት አስገነሰዝበዋል።

በግብርና ሚኒስቴር በዓለም ባንክ ኘሮጀክት የሚደገፋው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት  ዘርፉን ወደ ተሻላ ደረጃ ለማድረስ ድገፉን አጠነክሮ እንደሚቀጥል ከእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የተገኛ መረጀ የማለክታል ዘገበው (LFSDP.Com ) ነው ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!