(ሕዳር 03 ቀን  2016 ዓ/ም አዲስ አበባ) ፡ አቶ የሱፍ አህመድ ይበላሉ። ነዋሪነታቻው በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሀረርጌ በሐረማያ ወረዳ  አወዳይ  ነው።እኝህ  የ90 ዓመት አዛውንት የ10 ቤተሰብ  አስተዳዳር ሲሆኑ ቀደም ሲል በአካባቢያቸው  የሚታወቁት በጥምር ግብርና የእርሻ ሥራ እና  በጫት አምራችነት ነበር።

እኝህ  የዕድሜ ባለፀጋ   የሚያከናውኑትን የእንስሳት እርባታ ከባህላዊ አረባብ  ዘዴ  በማላቀቅ ወደ ዘመናዊ የእርባታ ዘዴ ለመሸጋገር  ፍላጎት  ነበራቸው። በየጊዜውም የባለሙያዎች ምክር ሀሰብ ለማግኘት በአቅራቢያቸው በሚገኘው የሐረማያ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ከመመላለሥ አንድም ቀን  እንዳልቦዘኑ ይናገራሉ። የግብርና ባለሙያዎችም አቶ ዮሱፍን ከማገዝ  ወደ ወሗላ ያሉበት ጊዜ  የለም፡፡ በተለይም እሳቸው በሐረማያ ወረዳ አካባቢ ከጥምር ግብርና እርሻ ጎን ለጎን በጫት አምራችነት የሚታወቁ  በአዋዳይ አካባቢም በህብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ዝናን ያተረፉ ናቸው ።

ታዲያ እኝህ አዛውንት በሐረማያ ግብርና ጽ/ቤት   ከሚያቀኑባቸው ቀናት ውስጥ በአንደናኛዋ ቀን ውስጥ አንድ ትልቅ ሀሳብ ከእዕምሯቸው ፈለቀላቸው።ያ ሐሳብም  ያሏቸውን ሁለት ነባር ጊደሮች (ሀገር በቀል) የማዳቀል ጉዳይ ነበር። ይህ ሕልማቸውም በሐረማያ ግብርና ባለሞያዎች እና በእንስሳት አዳቃይ በቴክኒሺያኖች(Artificial Incrimination) ሙሉ ድጋፍ ማግኘት በመቻላቸው ተሳካ።

የማዳቀሉ ሥራ ለአቶ የሱፍ በግብርና ባለሞያዎች ድጋፍ ቀላል ቢሆንም አንድ ነገር ግን ከባድ ሆነባቸው። ያም በአካባቢያቸው ዝናን ያተረፈላቸው እና ለዓመታት ገቢ ሲያስገኝላቸው የነበረውን የጫት እርሻ ወደ እንስሳት መኖ ልማት የመቀየሩ ጉዳይ ከቤተሰባቸው ብቻ ሳይሆን በአካባቢው ዘንድም መገረምን እና አልፎ አለውፎም እንደ ሞኝነት ያስቆጥርባቸው ጀመረ።

አንዳንዶች እንደውም እኝህ አዛውንት በ ዕድሜ መግፋት ማሰብ ተሳናቸው  የሚሉም እንዳልጠፉ በወቅቱ የነበረውን ጫና አቶ የሱፍ አጫውተውናል። በእግጥ በጊዚያዊነት ለተመለከተ አንድ ግለሰብ በሥንት ጥረት በአራት ሄክታር   ላይ የለማን የጫት እርሻ ወደ ተሸሻሉ የእንስሳት መኖ ልማት የመቀየር  ውሳኔ ከፍተኛ ቁርጠኝነት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው።

በሐረሪጌ አካባቢ  አንድ ጫት ነቅሎ መጣል ማለት አንድ ሕጸን እንደ  ሞተ ይቆጠራል። ምክንያቱም  ጫቱ ከሚሰጠው ጠቀሜታ አኳያ ስለሚመዘን እንደሆነ ይነገራል።

ጫቱን  ተንከባክቦ  በማሳደግ ምርቱን ለገብያ ማቅረብ ትልቅ ዋጋ ፅናት ይጠይቃል፡፡ ይሁን እንጂ አቶ ዮሱፍ በርካታ ፈተናዎችን በመጋፈጥ በአሁን ጊዜ በሁለት አገር በቀል ግዳሮች የጀመሩት በአሁን ጊዜ ከ90 በላይ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸው ላሞችን በአራት ሄክታር መሬት ላይ በማርባት በቀን እስከ 300 ሊትር ወተት ከቤተሰብ ፍጆታ የተረፈ ለአዋዳይ አከባቢ እና ለሐረር ከተማ በማሰራጫት ከፍተኛ ገቢ እያገኙ ነው። በፈተና የፀና  ጀግና ነው እንዲሉ አበው አሁን ላይ የአንድ ሌትር ወተት በ80 ብር እያተሸጡ በቀን እስከ 24 ሺህ ብር ገቢ እንደሚያገኙ አቶ ዮሱፍ  ነግረውናል። አቶ ዮሱፍ በአሁን ጊዜ ሁለት ገልባጭ መኪናዎች፣ ሁለት የጭነት እና እንዲሁም በርካታ መኖሪያ ቤቶች   ለበርካታ የአካባቢው ወጣቶች የስራ እድል እንደፈጠሩም ተናግረዋል።

ታዲያ ከአዛውንቱ አቶ የሱፍ የስኬት ጎዳና   በስተጀርባ  ሁነኛ ሚና የሚጫወት እና እየተጫወተ ያለ ፕሮጀክት አለ። ለአቶ የሱፍ በእድሚያቸው ማምሻ ላይ ለጣቸው የእድገት ጨረቃ እንደ አውሮፓዉያኑ አቆጣጠር በ2017 በተግበር  የጀመረው በዓለም ባንክ ድጋፍ የሚደገፈው የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት (LFSDP) ሁለገብ ድጋፍ አለ። እኝህ የ90 ዓመት ዕድሜ ባለፀጋ በሐረማያ ወረዳ ውስጥ በዚህ ፕሮጀከት ከታቀፉት የማህበራት ውስጥ አንደኛው ተጠቃሚ ናቸው። ዛሬ ላይ ሆነው የፕሮጀክቱን ድጋፍ ሲያስታውሱ ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባሉ።

በሐረሚያ ወረዳ የእንስሳት አዳቀይ ከፍተኛ ቴክኒሽያን የሆኑት አቶ ወንድዬ ለሜቻ በበኩላቸው በወረዳው በዓመት ከ1ሺህ 800 በላይ በሰው ሰራሽ የማዳቀል ዘዴ ጥጆች እንደሚወለዱ ገልጸል። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ እና የአምበሳውን ድርሻ የያያዙት አቶ የሱፍ መሆናቸውን ባለሞያው ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።

እኝህ ሞዴል የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ  የባለሙያዎችን ምክር በቀላሉ ወደ ተግባር የመቀየር ፍላጎታቸው   እና ተነሳሽነታቸው ከፍተኛ እንደሆነም ባለሞያው ተናግረዋል።

ትናነት የተተቹት ተግባር አሁን ላይ በሐረሚያ ወረዳው የነጭ ፈሳሽ ወርቅ ባለቤት እየተባሉ ይሞገሱ ጀምረዋል። እንደ ምስራቁ  የነጭ ፈሳሽ ወርቅ ባለቤት  አቶ ዩሱፍ አህመድ  ሁሉ ሌሎች  በወረዳው  ሌሎች የዘርፉ ተጠቃሚዎች በርካቶች ናቸው።

በኦሮሚያ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ፕሮጅክት አስተባባሪ ዶክተር ደረጀ ጉደታም ይህን እውነታ ይጋራሉ። ክልሉ በቀንድ ከብት ለአገሪቱ ከ35 እስከ 45 በመቶ ድርሻ አበርክቶ እንዳለው ይናገራሉ። ግን ለዓመታት ክልሉ እንዳለው ሀብት ተገቢውን ገቢ ከዘርፉ ሳይጠቀም ቆይቷል ባይ ናቸው ዶክተር ደረጀ። ይህን ክፍተት በመለየት በአገር አቀፍ ደረጃ የእንስሳት ልማት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን ያስታወሱት አስተባባሪው ዓለም ባንክ የሚደገፈው ፕሮጀክትም አንዱ አካል መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ኦሮሚያ ክልል የፕሮጀክቱን የእስካሁን አተገባበር ወጤት ለመገምገም ታሳቢ ያደረገ  የዳሰሳ ጥናት መካሄዱን ያነሱት ዶክተር ደረጀ በዚህ መሠረት በአራቱ የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት የምርት ሰንሰለት በተናጥል የለየ መሆኑንም ገልፀዋል።

ለአብነትም ከወተት ምርት እና ምርታማነት አንጻር ፕሮጀክቱ ከመተግበሩ በፊት በአለባ ውስጥ የሚቆዩት በዓመት ውስጥ 180 ቀናት ውስጥ ነበር። ከፕሮጀክቱ መተግበር በኋላ  ግን  የላሞችን የአለባ ቀን ወደ 209 ቀን ደርሷል። በቀን የሚመረተውን ከአንድ ላም አንድ ነጥብ አምስት ሊትር ወተትም ወደ በአማካኝ ወደ ሁለት ነጥብ አምስት ሊትር መድረሱን አርጋግጠዋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!