(ሕዳር 17 ቀን 2016 ዓ/ም):  በግብርና  ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ግርማ አመንቴ የተመራ ልዑክ እና ከዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ አስተባባሪ ጋር በመሆን በሲዳማ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች  በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት የተከናወኑ ሥራዎችን ተዘዋውሮ ጎብኝቷል።

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በግብርና ሚኒስቴር  በዓለም ባንክ የሚደገፈው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ባለፉት ስድስት ዓመታት በክልሉ  በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን ለመመልከት እና ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ነው።

በክልሉ በፕሮጀክቱ ድጋፍ   በአራቱ የእንስሳት እሴት ሰንሰለት  ላይ በወተት ፣ በዶሮ እርባታ  በዓሣ ግብርና ፣ እንድሁም በቀይ ሥጋ ላይ  የተከናወኑ ተግባራት እና የተመዘገቡ ውጤቶች አመርቂ መሆናቸው በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።

 

አርሶ አደሮች ከጋራ ፍላጎት አደረጃጀት (CIG) ወደ ህብረት ስራ ማህበራት ት ማደጋቻው እና በእንስሳት ልማት ዘርፉ ላይ እያስመዘገቡት ያለው እምርታዊ ለውጦችን መታየት መጀመራቸውን በጉብኝቱ ወቅት መመልከት ተችሏል።

አርሶ አደሩ ከተረጅነት ተላቆ ከእንስሳት ልማት ዘርፍ  የምግብ ዋስትናቸውን ማረጋገጥ መቻላቸውን  በመስክ ጉብኝቱ መመልከት ተችሏል።

ከመስክ ጉብኝቱ በኋላ በተደረገ ውይይት  ክቡር የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በፕሮጀክቱ የተመዘገበውን ውጤት አድንቀዋል። በቀጣይም በዘርፉ ላይ የሚደረገው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

የዓለም ባንክ የምስራቅ አፍሪካ አስተባባሪ በበኩላቸው በመስክ ምልከታው ላይ በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮችን በስፋት ማየታቸው እንዳስደሰታቸው በውይይቱ ላይ ገልፀዋል። በቀጣይም የዓለም ባንክ በግብርናው ዘርፍ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!