የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. LFSDP  /9-03/2024  )፡  የግብርና ሚኒስቴር ለእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት(LFSDP ) ላይ ከፍተኛ ዓሻራ ላሳረፉት እና ለ23 ዓመታት በግብርና ምጣኔ ሀብት ከፍተኛ ባለሞያነት ላገለገሉት  አቶ አሳዬ  ለገሰ የክብር ሽኝት  አድርጎላቸዋል።

የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት እና ዓሣ ሀብት ዘርፍ  ልማት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ  እና  FPCU እና  የክልል ኘሮጀክት አስተባባሪዎች በተገኙበት ለአቶ አሳየ ለገሰ የክብር አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል ፡፡

አቶ አሰዬ ለገሰ  ከ23 ዓመት  በላይ በኢትዮጵያ በዓለም ባንክ በተለየዩ ቦታ አገራቸውን በግብርና ምጣኔ ሀብት  የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ አገልግለዋል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፍቅሩ በሽኝቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር አቶ አሳዬ ለአገራቸው በተለይም   በግብርና  ዘርፍ በእንስሳት ልማት  ላይ የሚስተዋሉት ዘርፈ ብዙ ችግሮችን በመለየት  ዘርፉ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር  በዓለም ባንክ  የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክቱ በመቅረጽ  የጎላ ድርሻ ነበራቸው ብለዋል።

በኢትዮጵያ በተለይም  በደጋማ የአገሪቱ አካባቢ  በ58 ወረዳዎች የሚተገበር ፕሮጀክት ወደ ስራ እንዲገባ  በማድረግ በርካታ አርሶአደሮች ተጣቃሚ መሆን እንዲችሉ  ከመጀመሪያው ጀምሮ የአቶ አሳዬ ድጋፍ እና ክትትል የጎላ እንደነበር አንስተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ቀሪው የሕይወት ዘመናቸው ያማረ እንዲሆን መልካም ምኞት ተመኝተውላቸዋል።

የክብር ሽኝት የተደረገላቸው አቶ አሳዬ ለገሰ በበኩላቸው ለተሰጣቸው ክብር እና ምስጋና አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ዘገበው LFSDP.Com)

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!