(መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም :አዲስ አበባ LFSDP )፡ በግብርና ሚኒስቴር በእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት ( LFSDP ) በተደረገው  የገንዘብ ድጋፍ በሰብል ተረፈ ምርት አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ በአማራ ክልል  ከ6 ዞኖች ለተውጣጡ ባለሞያዎች የአሠልጣኞች ሥልጠና ተሰጥቷል።

በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳት  ዘርፍ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ  አቶ ግርማ ሙሉጌታ ባደረጉት ንግግር  ሥልጠናው በወሳኝ የአገሪቱ  የሰብል ተረፈ ምርት  አያያዝ እና አጠቃቀም ላይ ከፍተኛ ግንዛቤ የሚፈጥር  ነው ብለዋል።

በተለይም ከዚህ በፊት በእንስሳት መኖ ተረፈ  ምርት አያያዝ እና አጠቃቀም  በየክልሎቹ ያሉት አርሶ አደሮች ግንዘቤ አነስተኛ በመሆኑ  ይህን ክፍተት  በመቅረፍ ረገድ በየጊዜው እየተሰጠ ያለው ሥልጠናው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

ግብርና ሚኒስቴር  በ10 ዓመት ውስጥ ተግባራዊ የሚደረግ  የመኖ ልማት ስትራቴጂ ዕቅድ በመንደፍ  በአሁኑ ወቅት እየሠራ መሆኑንም ለሠልጣኞች ጠቁመዋል።

በአሁኑ ጊዜ በእንስሳት ልማት ዘርፍ ላይ እየታየ  ያለውን  ምርት እና ምርታማነት  እጥረት ለመቅረፍ    በእንስሳት ጤና፣ በዝርያ ማሻሻያ፣የተሻሻሉ መኖ ልማት ላይ እየተሰራ ነው ብለዋል።

አሠልጣኞች ወደ የመጡበት ዞን ሲመለሱም ያገኙትን እውቀት እና ልምድ እንደሚያካፍሉ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። አቶ ግርማ ሥልጠናው እስከ ቀበሌ ድረስ መውረድ እንዳለበት አሳስበዋል።

በግብርና ሚኒስቴር በእንስሳት ልማት ዘርፍ የመኖ ሀብት ልማት መሪ ስራ አስፈጸሚ አቶ አርአያ አብርሃም በበኩላቸው እንዲህ ዓይነቱ ስልጠና ከዚህ በፊት በትግራይ ክልል ፣ ኦሮሚያ ፣በደቡብ ኢትዮጵያ ፣ማዕከለዊ ኢትዮጵያ ፣  በሲዳማ፣ ሐረሪ ፣ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎችን ጨምሮ ለ8   ክልሎች ስልጠና መሠጠቱን አስታውሰዋል።

አቶ አርአያ  ማዕከለዊ ኢትዮጵያ ፣ ሲዳማ  እንደሁም ደቡብ ኢትዮጵያ በተሻሻሉት ማዕከለዊ ኢትዮጵያ በመኖ ልማት እና በሰብል ተረፈ ምርት አያያዝ እና አጠቃቃም  ላይ ለአገራችን ትልቅ ምሳሌ  የሚሆኑ እነ ከፍታኛ ለውጥ ማስመዝገባቸውን ጠቅሰዋል።

ከአማራ ክልል ከዋግኸምራ ዞን የመጡት ወ/ሮ ለምለም ማሞ  ዞናቸው በተደጋጋሚ  ድርቅ  የሚጎበኝው በመሆኑ ለመኖ ልማት እና ተረፈ ምርት አያያዝ ላይ ትኩረት ማድረጉ የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል።ለቀጠይም ሚኒስቴር መስሪቤቱ አሁን እየሰጠ ያለውን ሥልጠና አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በግብርና ሚኒስቴር በዓለም ባንክ የሚደገፈው የእንስሳት እና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት (LFSDP) በሚያደርገው የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ መሠረት በቀጣይም ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች ከአንድ ቀበሌ 20ዎቹ ተመርጦ በየገበሬ ማሠልጠኛ ማዕከል (FTC) ስልጠና ይዋስዳሉ ተብሎ  እንደሚጠበቅ የግብርና ሚኒስቴር ከመኖ ዳይሬክቶሬት የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

error: Content is protected !!